ና፣ ጌታ የሱስ ሆይ፣ ና

ለተገፉና ላዘኑ
ዕረፍት አጥተው ለባከኑ
ሰብሳቢ ላጡ ሕፃናት
ለሚማቅቁ እንስሣት
ስለ ሢቃ
ስለ ብዙ ሰልፍ
አንዱ ባንዱ ላይ ግፍ
“ፍጥረት ሁሉ ይናፍቃል
ይቃትታል … ይጠብቃል
እጅግ ደክሟል”
ስለሚል ቃል
ጸሎታችን መደምደሚያው
ይኸ ይሁን --

ና፣ ጌታ ሆይ፣ ና

 

©ምትኩ አዲሱ፣ 1980