የ
“ዳቪንቺ ኰድ” ፍቺና
የዘመኑ መንፈስ
በምትኩ
አዲሱ
መግቢያ
የ
“ዳቪንቺ ኰድ” ዳን
ብራውን በተሰኘ የ 42
ዓመት አሜሪካዊ
የተደረሰ ታሪክ-ቀመስ
ልብ ወለድ መጽሐፍ
ነው። እንደ ፈረንጆች
አቆጣጠር (እ.ፈ.አ.) በ 2003
የመጀመሪያው እትም
ገበያ ላይ ከዋለ
ጀምሮ ከስድሣ ሚሊዮን
በላይ ኰፒ በዓለም
ዙሪያ ተሽጧል። ወደ
አርባ በሚጠጉ ቋንቋዎች
ተተርጉሟል። ቢያንስ
አንድ መቶ ሚሊዮን
ሰዎች አንብበውታል። ከነዚህም
ሲሦው ያህሉ
ታሪካዊነቱን
ሳይጠራጠሩ
ተቀብለውታል። በፊልም
ተቀርጿል።
ለደራሲውና
ለሚመለከታቸው ደግሞ
በመቶዎች ሚሊዮን ዶላር
የሚቆጠር ገቢ
አስገኝቷል።
እንግዲህ ምን
እንበል? የመጽሐፉ
ዕውቅና ማግኘት
የእውነት ሚዛን
ይደረግን?
ሐተታው
ባጭሩ
ጸሐፊው
እንደሚያትተው
ከሆነ፦ ከሐዲስ ሌላ
የኢየሱስን ማንነት
የሚያስረዳ ስውር
ሰነድ አለ፤ ይህን
ሰነድ ካቶሊካዊት ቤተ
ክርስቲያን ሥልጣኗን
ለማስከበርያ
በምሥጢር ይዛዋለች፤
ምሥጢሩን
የሚያውቁትን ግለ ሰቦች
ደግሞ ታሳድዳለች፣
ታስወግዳለች፣
ይለናል። አራት መቶ
በሚያህሉ ገጾች
ይህንኑ መነሻ አሳብ
የሚያጸድቁ
መጻሕፍትና ፎቶግራፎችን
እየጠቀሰ አንባቢውን
ለማዝናናትና
ለማሳመን ይጥራል።
አመሳክሬ ደርሼበታለሁ
ከሚለው ምሥጢር ውስጥ
ለምሳሌ ሁለቱን
እንመልከት፣
·
መግደላዊት
ማርያም እንጂ
ሐዋርያው ጴጥሮስ
የቤተ ክርስቲያን
ጀማሪ አይደለም፤
መግደላዊት ማርያምን
የሚያመልኩአት
“የጽዮን ፕርዮሪ”
በሚል ስያሜ የተደራጀ
ማኅበር አላቸው፤
(ዳን ብራውን እንዲህ
ይበል እንጂ፣ እውነቱ
ግን ሌላ ነው።
ማኅበሩ የተቋቋመው
በአራት የፈረንሣይ
ዜጎች የዛሬ ሃምሳ
ዓመት ግድም ነው።
ማኅበሩን
የመሠረቱበት
ምክንያት በየሁኔታው
ተገናኝቶ ለመጫወት
እንዲያመቻቸው ነው።
“ጽዮን” ያሉት
እውነተኛይቱን
ጽዮንን ሳይሆን
የሠፈራቸውን ኰረብታ
መጠርያ አስበው ነው።
ማኅበሩ አሁን
ፈርሷል። ጉዳዩ ይኸው
ነው)
· ኢየሱስ ሰው ብቻ እንጂ አምላክ አይደለም ይለናል። ይህን መሰል ትምህርት የሚያስተምሩትን የእግዚአብሔር ቃል ‘ሐሰተኞች ነቢያት፣ ሐሰተኞች መምህራን’ ይላቸዋል (1ኛ ዮሐንስ 4፡ 1-2፤ 2ኛ ጴጥሮስ 2፡ 1)። ሐዋርያው ጳውሎስ እንኳን በደማስቆ መንገድ ላይ ሳይገለጥለት በፊት ኢየሱስን ሰው ብቻ እንደሆነ ይገምት ነበር፦ 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡ 16። በተጨማሪ በወቅቱ የነበሩትን የሃይማኖት መሪዎች ምልልስ ከማርቆስ 6፡ 3፤ ዮሐንስ 8፡ 53-57 ላይ ይመልከቱ።
እስቲ
ዝርዝር ውስጥ
ከመግባታችን
አስቀድሞ ጸሐፊው
ለምን ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን
ላይ አተኰረ? ብለን
እንጠይቅ። አንደኛው
ምክንያት
ከፕሮቴስታንቱ
የሃይማኖት ክፍል ይልቅ
ለምሥጢራት የሚሰጠው
ግምትና ትምህርት
በካቶሊክ እምነት
ውስጥ ከፍተኛ
ስለሆነና ይህም
ለደራሲው የፈጠራ ሥራ
አመቺ በመሆኑ ነው።
ለዚህም እ.ፈ.አ. በ 2005፣
ዓለም ሁሉ
በቴሌቪዥንና በአካል
የተከታተለውን የፓፓ ጆን
ፖልን የቀብር ሥነ
ሥርዓት ማስታወሱ
ይበቃል። ይቺው ቤተ
ክርስቲያን በታሪክ፣
በምሥጢራትና
በምስሎች የታነጸች
ነች። በፓፓው እግር
የሚተኩትን ለመምረጥ
የተደረገው ሥርዓት
ደግሞ እንዲሁ በምሥጢር
የተካሄደ ምርጫ
ነበር። ተዘግቶባቸው
ሲጠበቁ የቆዩት የቤተ
ክርስቲያኒቱ ዓለም
አቀፍ መሪዎች
በሚሰየመው ሰው ላይ
ሳይስማሙ ቀርቶ ነጭ
ጪስ፣ ስምምነት ላይ
በደረሱ ጊዜ ደግሞ
ጥቁር ጪስ ለምልክት
በጣራው ቀዳዳ ሲወጣ
ተስተውሏል።
ሁለተኛው ምክንያት፣
እንደ ቀድሞው ኰሚዩኒዝምን
በመኰነንና በማጋለጥ
የአንባቢን ስሜት
ማቀጣጠል እየቀረ ስለመጣ፣
ወደ ሃይማኖት ዘርፍ
መሸጋገሩ ነው።
ባጭሩ፣ ሃይማኖትን፣
ወሲብን፣ ግድያን፣
ታሪክን በአንድ ላይ
መቀመም የተዋጣለት
የደራሲያን መፈንጫና
የመጽሐፍት መሸጫ
የኖረ ብልሃት ነው።
ሐተታው
ሲተነተን
ደራሲው የተረጋገጠ ታሪክ ነው ብሎ ያቀረባቸው መሠረታዊ ነጥቦቹ ታሪካዊነታቸው ግምታዊ ቢሆንም፣ አብዛኛው ሰው ይህን ለማጣራት ጊዜውም ሆነ ዕውቀቱ የለውም። ዕውቀት ስንል የቤተ ክርስቲያንን ታሪክና የሐዲስን መሠረታዊ ትምህርት በተመለከተ የብዙዎች ዕውቀት ያልተያያዘ፣ ከአፈ ታሪክ ያላለፈና የተመጠነ ነው ለማለት ነው።
እርግጥ
በየወቅቱ እንዲህ
የመሰሉትን መጻሕፍት
ለአንባቢ ማቅረብ የተለመደ
ሆኗል። ወቅቱን
ጠብቀው ብቅ ሲሉ
ሰውን ያነጋግራሉ።
በጥቂቶች ዘንድ
ተቀባይነትና ሙገሣ
ይቀዳጃሉ።
ያልጸኑትን ወደ
ጥርጥር ይወስዳሉ።
የተለመደ
ከሆነ ታዲያ ምን
አስቸገረን? እንል
ይሆናል። እንደዚያ
እንዳንል፣
የእግዚአብሔር ቃል
“በእናንተ ስላለ
ተስፋ ምክንያትን
ለሚጠይቋችሁ ሁሉ
መልስ ለመስጠት
ዘወትር የተዘጋጃችሁ
ሁኑ” ይለናል (1ኛ
ጴጥሮስ 3፡15)።
በተጨማሪ፣
ለየትውልዱ የተመደበ
የሚያነጋግርና
የሚያሳስብ ጥያቄ ስላለ
እያንዳንዱ
የእምነቱን ምንነት
መመርመርና የራሱን
መልስ መሻት ይጠበቅበታል።
ይህን
መጽሐፍ ከሌሎቹ ሁሉ
ልዩ የሚያደርገው
መሠረተ እምነታችንን
መፈታተኑና ማጣመሙ
ብቻ ሳይሆን፣ ይህንኑ
የተዛመመ አስተሳሰብ
በዓለም ዙርያ
በየቋንቋው ማሠራጨቱ
ነው፤ በወገኖቻችን
መካከል ደግሞ ጥያቄ
ማስነሳቱና
ተቀባይነት ሊያገኝ
መቻሉ ነው (ይመልከቱ www.addisadmas.com እና www.cyberethiopia.net/warka3/viewtopic) ። ዳን
ብራውን ታሪክ ነው
ብሎ ያቀረባቸው
እንግዲህ ምን
ምንድናቸው? ለጊዜው
ዋነኛ የሆኑትን
ሁለቱን ብቻ
እንጥቀስ፣
·
ኢየሱስ
በጊዜው እንደ ነበሩት
መምህራን ቤተ ሰብ
ነበረው፤ ትውልዶቹ አሁንም
እንኳ ይገኛሉ፣
የሚልና
·
በጌታ
እራት ላይ ከተገኙት
ደቀ መዛሙርት መካከል
አንዷ ሴት ነበረች፣ የሚል
ነው።
በሌላ
አነጋገር የጌታን
ፍጹም ሰው፣ ፍጹም
አምላክ መሆን
ይክዳል። የእግዚአብሔርን
ቃል ምስክር
ያስተባብላል። ይህ
ደግሞ ሊደንቀን ወይም
ሊያደናግጠን
አይገባም። “ኢየሱስ
በአፉ መንፈስ
እስኪያጠፋውና
በመገለጡ እስኪሸረው”
ድረስ አሳቹ ምሥጢራዊ
ዓመጹን ማድረግ አያቆምም
(2ኛ ተሰሎንቄ 3፡ 8)።
ኢየሱስ ከሙታን
አልተነሣም መባል
የጀመረው ዛሬ
አይደለም። አጋንንት
አለበት፣ አጋንንትን
በአጋንንት ያወጣል፣
የተባለው ገና በምድር
ላይ እያለ ነበር
(ማቴዎስ 9፡ 34፤ ዮሐንስ
7፡ 20፤ 8፡ 48)። ተከታዮቹም
ሰው-በላ ናቸው፣
መባል የጀመረው ዛሬ
አይደለም። በድንቁርና
ይሁን በሥልጣኔ ተገን
ተጻራሪ ኃይላት
ዓላማቸው ያው አንድ
እንደሆነ
እንገነዘባለን።
በአገራችንም
እንኳ ወንጌል
አማኞችን ለማጥላላት
ሲባል፣ ከጣራ ላይ ገንዘብ
እየበተኑ
እግዚአብሔር ሰጠን፣
ይላሉ ተብሎ የለ?
የእግዚአብሔርን
ምሥጢር በቃል ብዛት
ካልተነተኑ
የማያሳርፋቸው ሁሌም
አይጠፉም። ካላየን
አናምንም የሚሉ አሉ።
እምነት ግን በማየት
አይመጣም። ጽኑ ተስፋም
በሚታይ ነገር
አይገኝም (ሮሜ 8፡24፤
10፡17፤ ዮሐንስ 20፡ 28)። እንደዚያማ
ቢሆን ኖሮ ያ
የሚታየው ሲጠፋ
እምነቱም ተስፋውም
ጠፋ ማለት ነው።
ይህን ስንል እምነት
በጭፍን ነው ማለት
እንዳይመስልብን።
እምነት መነሻ
ይኖረዋልና።
አንደኛ፣ የኢየሱስ
ሕይወትና ያስተማረው
ትምህርት፤ ሁለተኛ፣
አብረውት የኖሩት
የሰሙት የተከተሉት
ያመኑበትና የደቀ
መዛሙርቱ ምስክር፤
ሦስተኛ፣ በዘመናት
ሁሉ ተፈትና ጸንታ
ያለች ባሕልና ቋንቋ
ያልለያት ቤተ
ክርስቲያኑ፤
በመጨረሻም፣
በፈቀዱለት መጠን
በሰው ልጆች መካከልና
በሰው ልብ ውስጥ
ሊኖር የተቻለው ቅዱስ
መንፈሱ፣ እነዚህ
የእምነት መነሻ
ናቸው፤ መንቀሳቀሻ
ናቸው፣ ማረጋገጫና ማጽኛ
ናቸው (ኤፌሶን 2፡ 20-22፤
1ኛ ዮሐንስ 1፡ 1-2፤ 2ኛ
ጴጥሮስ 1፡ 16-21፤
የሐዋርያት ሥራ 1፡ 1-2፤
17፡ 22-31)።
ጌታን
በአካል ተገልጦ እያለ
ያላመኑበት እንደ
ነበሩ አንርሣ።
በዓይናቸው ፊት
ሙታንን እያስነሣና
ድውዮችን እየፈወሰም
እንኳ ያላመኑበት
ነበሩ። እምነት
በማየት አይመጣም
ያልነው ለዚሁ ነው።
አለማመን በመሠረቱ
የግለ ሰብ የሞራል
አቋምና ውሳኔ እንጂ
ለማመን የሚያስችል
በቂ ምክንያት
አለመኖሩ አይደለም።
ጌታን ማመንና ለርሱ
መገዛት የያዙትን
ዕቅድ የሚያስጥል
ስለሆነ ብዙዎች
ላለማመን ሰብበ
ይፈጥራሉ። አንዳንዶችም
ካለማወቅ። መጠየቅና
መጠራጠር በራሱ እንደ
ኃጢአት ሊቆጠር
አይችልም፣
አይገባም። እውነትን
ለማወቅ ከነፍስ የሆነ
ጥማት እስካለ ድረስ
እግዚአብሔር ራሱን
ለዚያ ሰው ለመግለጽ
ይገደዳል። ያም ሰው
እግዚአብሔርን
ካላገኘ በስተቀር ሌላ
ምንም አይጥመውም፤
በነፍሱም ዕረፍትን
አይቀምስም። ለሚሹኝ
እገኛለሁ፣ ይላል
እግዚአብሔር (ኤርምያስ
29፡ 12-13፤ ዮሐንስ 6፡ 37)።
ይኸ ጥሪና ተስፋ ዳን
ብራውንንም ይጨምራል።
አለዚያማ
እግዚአብሔር ጻድቅ
አይሆንም።
በአንጻሩ፣
“እግዚአብሔርን
ለማወቅ ባልወደዱት
መጠን እግዚአብሔር
የማይገባውን ያደርጉ
ዘንድ ለማይረባ
አእምሮ አሳልፎ
ሰጣቸው” ተብሎ
ተጽፏል (ሮሜ 1፡ 28)።
ዳን
ብራውን የሰበከንን
እስቲ አንዴ ተራ
በተራ እንይ። እውን
ኢየሱስ የራሱ ቤተ
ሰብ ነበረው? ስለ
ኢየሱስ የምናውቀውን
ያስተላለፉልን “በእግዚአብሔር
አስቀድሞ የተመረጡ
ምስክሮች… ከእርሱ
ጋር የበሉና የጠጡ ናቸው”
(የሐዋርያት ሥራ 10፡41)።
ከእነዚህ መካከል
አንዳቸውም ቤተ ሰብ
እንዳለው ሳይጠቅሱ
ማለፋቸው አያስገርምም?
ስለ ኢየሱስ እናት፣
ስለ ወንድሞቹ እና
ስለ አክስቱ ልጅ (ዮሐንስ
መጥምቁ) ነግረውናል
(ማቴዎስ 12፡47፤ ሉቃስ
1፡36)። ጌታም በመስቀል ላይ
ሆኖ ዮሐንስን አደራ
ያለው ስለ እናቱ
ነበረ (ዮሐንስ 19፡ 25-27)።
ከትውልዶቹ
መካከል የቀሩ ዛሬም
አሉ፣ የተባለውስ?
ካሉ ታዲያ ምነው ራሳቸውን
ሸሸጉ? ሳይዛመዱት
ሰበብ ፈጥረው
“ክርስቶስ” ነን የሚሉ
የሉም? ኰሪያዊው
ሬቭረንድ ሙን በመልክ
እንኳ አይሁድን
ሳይመስል ክርስቶስ
ነኝ ብሎ እንደ ተነሳ
አንርሳ!
ማርያም
መግደላዊትስ በጌታ
እራት ላይ ተገኝታ
ነበር? ዳን ብራውን
ተገኝታ ነበር፣ ሆኖም
ሴት ስለሆነች፣ ሴት
ደቀ መዝሙር አትሆንም
ለማሰኘት ወንዶች
በሴቶች ላይ ያደረጉት
ሤራ ነው ይለናል።
ይህን መሰል ተረት መስማት
የሚወዱ ሞልተዋልና።
ይህን ታሪክ የቀዳው
ኢጣልያዊው ሰዓሊ ሊዮናርዶ
ዳቪንቺ ከ500 ዓመት
በፊት ጌታንና
ሐዋርያቱን እራት
ሲበሉ ከሳለው ስዕል
ላይ ነው። ይኸው
ስዕል ተጠናቅቆ
ስላላለቀ ቀለሙ
የደበዘዘ ነው።
በተጨማሪ ጌታ ደረት
አጠገብ ተጠግቶ
የተቀመጠው ወጣቱ
ዮሐንስ ጢም
ስላልነበረውና
ይህንን በሚመለከት
ሌሎች በዘመኑ የነበሩ
ሰዓልያን ዮሐንስ
እንደ ሴት የሚያምር
ወንድ ነው እያሉ
ስላስወሩ ነው። የቱን
ከየቱ እንዳገናኘ
እንታዘብ!
ማግባት
ሆነ አለማግባት ድንቅ
ነገር አይደለም።
ጋብቻ ክቡር ነው፣
እግዚአብሔር ራሱ “ከፍጥረት
መጀመሪያ” የደነገገው
ሥርዓት ነው
(ዕብራውያን 13፡ 4፤
ማርቆስ 10፡ 6)። ኢየሱስ
ከድንግል ማርያም
የተወለደውና ወደ
ምድር የመጣበት ዓላማው
ምድራዊ ኑሮን ለመኖር
አልነበረም።
በመስቀል ሞቶ ሰዎችን
ከኃጢአት ሊያድንና
ከአብ ጋር ሊያስታርቅ
እንጂ (ሉቃስ 4፡ 19፤ 1፡
30-35፤ ማርቆስ 10፡ 45)።
እንዲያስ ባይሆን
ኖሮ፣ ጌታን፦ “የሰው
ልጅ ራሱን
የሚያስጠጋበት የለውም”
ምን አሰኘው?
ከመወለዱ በፊት
በነቢያት አፍ
“ናዝራዊ” እንደሆነ
የተነገረለት ለምንድነው
(ማቴዎስ 2፡ 23፤ 19፡10-12)?
ሐዋርያው ጳውሎስ
እራሱም ያላገባ ሆኖ
ሳለ ስለ እነ ጴጥሮስ
ማግባት ገልጾ ስለ
ጌታ ሳይገልጽ እንዴት
ቀረ (1ኛ ቆሮንቶስ 7፡7፤
9፡5)? ካቶሊክ ቤተ
ክርስቲያን ከመፈጠሯ
በፊት፣ በወቅቱ
የነበሩ ስመ-ጥር
የሮማ ታሪክ ጸሐፊዎች
እነ ሱቶኒየስና
ታሲተስ ስለ ናዝሬቱ
ኢየሱስ ሲጠቅሱ
ትልቁን ቁም ነገር
ምነው ዘነጉ?
እንግዲህ የዳን
ብራውንን መጤ ታሪክ
ከመቀበል ይልቅ
የጌታን፣
የሐዋርያቱንና
የቅድስት ቤተ
ክርስቲያንን
ትምህርት ማመን
ይቀለናል፣
እንላለን።
ዳን
ብራውን ደጋግሞ
የተጠቀመበት ስልት፣
መጽሐፍ ቅዱስ ትክክል
ለመሆኑ ምን ማስረጃ
አለ? የሚለውን
ጥርጥር ላይ የሚጥል
ጥያቄ በመጠየቅ ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ ትክክል
ላለመሆኑማ ራሱም
እንኳ አጥጋቢ መልስ
መስጠት አይችልም።
የቀደመው እባብ፣ ሔዋንን
በማወቅ ጉጉትና
“እንደ አምላክ መሆን
ይቻላል” በሚል አሳብ
ልቧን አጭሮ
እንዳታለላት ሁሉ
ዛሬም ለተገለጠላቸው
እውነት ላለመታዘዝ
ምክንያት
የሚፈልጉትንና
ጆሮአቸውን ለከንቱ
ነገር ለሚከፍቱ
ወጥመድ አዘጋጅቷል
(ዘፍጥረት 3)። ጌታ ግን
የሚሹትን
ያውቃቸዋል፤ እርሱን
ብለው አቅም
ያነሳቸውን
ይለያቸዋል። ሌሎችን
ደግሞ “እባብ
በተንኰሉ ሔዋንን እንዳሳታት፣
አሳባችሁ ተበላሽቶ
ለክርስቶስ ከሚሆን
ቅንነትና ንጽሕና
ምናልባት
እንዳይለወጥ” ሲል
በከንቱ ነገር
እንዳይበከሉ ያስጠነቅቃቸዋል
(2ኛ ቆሮንቶስ 11፡ 3)።
የርሱ የሆኑትን
ያውቃቸዋል፤ አሳልፎ
አይሰጣቸውም። ፈጥኖ
ይደርስላቸዋል።
“እግዚአብሔር
በመካከልዋ ነው አትናወጥም፣
እግዚአብሔርም ፈጥኖ
ይረዳታል” (መዝሙር 46፡
5)።
ለመሆኑ
ዳን ብራውን ማነው?
መልእክቱንና
መልእክተኛውን
መነጣጠል አጥርተን
እንዳናይ ይከልለናል።
መልእክቱ ምንድነው?
መልእክተኛው ማነው?
ምን ዓላማ ይዞ ነው
የተነሳው? ስለ
ትምህርቱ
የእግዚአብሔር ቃል
ምን ይላል? እኔስ ምን
አቋም ሊኖረኝ
ይገባል? ዳን
ብራውንን መለየት
የሚያሻን በነዚህ
ነጥቦች መሠረት ነው።
ዳንኪራ
ቤት የሚያዘወትር
ክርስቲያን ስለ
መቀደስ ቢያወራ
አንተስ ማን ሆንክና?
ብለን ልናፋጥጠው
እንደፍራለን።
የመቀደስ ትምህርት
ስህተት ነው ማለት
ግን አይደለም።
ያልኖረበትን ያወራል
ማለት እንጂ። ይኸው
ወንድም፣ ዳንኪራ ቤት
የምሄደው እኰ ቤተ
ክርስቲያን ለሚኖረው
አምልኰ እንዲረዳ ነው
ቢል የባሰ ጥያቄ
ይፈጠርብናል።
ስለ
ዳን ብራውን ገድል
ለመዘርዘር አንሻም፤
ዓላማችን
አይደለምና። ሆኖም
አምስት ቁም ነገሮችን
እናስቀድም።
አንደኛ፣ ይህ ግለ
ሰብ የሐዲስ ወይም
የብሉይ ሊቅ አለመሆኑ
ሊታወቅ ይገባል። የ
(ቤተ ክርስቲያን) ታሪክም
ምሑር አይደለም።
ኰሌጅ ገብቶ ያጠናው
ለአስተማሪነት
የሚያበቃ የእንግሊዝኛና
ስፓንሽ ቋንቋዎችን
ነው።
ስለ
ራሱ ሲጠየቅ፦
“ክርስቲያን ነኝ፤
ሆኖም ሰፊው ማኅበረ
ምዕመን በሚያውቀው
መንገድ አይደለም።
ክርስቲያን መባል
ለተለያዩ ሰዎች
የተለያየ ትርጉም
አለው። ለአንዳንዶች
ኢየሱስን በአዳኝነቱ
መቀበል ነው፤ ለሌሎች
መጠመቅ ነው፤ ወይም
የእግዚአብሔርን ቃል
ፍጹም እውነተኛነት መታመን
ነው። እንደሚመስለኝ
ከሆነ እንዲህ ዓይነቱ
አስተሳሰብ ግትርነት
ነው። ሁላችንም
የሕይወትን ምሥጢር
ለማወቅ በጥረት ላይ
የምንገኝ ነንና።
በዚህ መልኩ እኔም
የብዙ ሃይማኖቶች
ተማሪ ነኝ ማለት
እችላለሁ።
የሚገጥሙኝ ሁኔታች
ሁሉ አዲስ ትምህርት ይሰጡኛል።
ደግሞ አዲስ ጥያቄ
ይፈጥሩብኛል። በዚህ
ጐዳና ላይ እርግጠኛ
መሆን አይቻልም”
ይለናል። ባጭሩ፣
የዳን ብራውን አቋም
ወንጌላትና የክርስቶስ
ቤተ ክርስቲያን ስለ
ክርስቶስ
ከሚያስተምሩት
ትምህርት የወጣ ነው።
እየተማታ “ኸረ
ቀልዴን ነው” ወይም
የልቡን ካደረሰ በኋላ
‘ጨዋታም አታውቁም
እንዴ?” የሚል ሰው
ዓይነት ነው።
ክርስቶስ ባስተማረበትና
በኖረበት የሕይወት
መንገድ ውስጥ ሳይሆን
እራሱ በፈቀደውና
በቀየሰው አሳብ
የሚጓዝ ሰው ነው።
ክርስትና
ስለ ኃጢአት ስርየት
በመስቀል ላይ ሞቶ
ስለ ጽድቅ ከሙታን የተነሳውን
ፍጹም ሰው፣ ፍጹም
አምላክ የሆነውን
ኢየሱስን አምኖ
መከተል እስከሆነ
ድረስ ዳን ብራውን
ክርስቲያን
አይደለም። ነኝ ሊል
ይችላል። “እምነት
የግል ነው።
እግዚአብሔር ልቤን
ያውቃል፤ አንተ ማን
ሆንክና ነው
የምትፈርድብኝ?” ሊል
ይችላል።
የእግዚአብሔር ቃል
ግን እንዲህ ይላል፣
“ቃሌን
ሰምቶ የማይጠብቀው
ቢኖር የምፈርድበት
እኔ አይደለሁም።
የሚጥለኝ ቃሌንም
የማይቀበለው እርሱ
የሚፈርድበት አለው።
እኔ የተናገርሁት ቃል
እርሱ በመጨረሻው ቀን
ይፈርድበታል።… እኔ
መንገድና እውነት ሕይወትም
ነኝ፤ በእኔ በቀር
ወደ አብ የሚመጣ
የለም… መጻሕፍትን
ካላመናችሁ ግን ቃሌን
እንዴት ታምናላችሁ?…
እርስ በርሳችሁ ክብር
የምትቀባበሉ
ከአንዱም
እግዚአብሔር ያለውን
ክብር የማትፈልጉ፣
እንዴት ልታምኑ
ትችላላችሁ?… በአፍህ
በልብህም ሆኖ ቃሉ
ቀርቦልሃል፣ ይህም
የምንሰብከው
የእምነት ቃል ነው።
ኢየሱስ ጌታ እንደ
ሆነ በአፍህ
ብትመሰክር እግዚአብሔርም
ከሙታን እንዳነሣው
በልብህ ብታምን
ትድናለህና፤ ሰው በልቡ
አምኖ ይጸድቃልና
በአፉም መስክሮ
ይድናልና…ልጁ ያለው
ሕይወት አለው፣
የእግዚአብሔር ልጅ
የሌለው ሕይወት
የለውም” (ዮሐንስ 12፡ 47-48፤
14፡6፤ 5፡47፣ 44፤ ሮሜ 10፡
8-10፤ 1ኛ ዮሐንስ 5፡ 12)።
ዳን
ብራውን የኢየሱስን
አምላክነት ይክዳል፣
ቢቻለውም ያስክዳል።
የእግዚአብሔርን ቃል
ምስክርነት
ያጣጥላል። ንጉሥ
ቁስጠንጢኖስ በአራተኛው
መቶ ክፍለ ዘመን
“ኢየሱስ አምላክ ነው”
እንዳሰኘና መጽሐፍ
ቅዱስን እንዳስገኘ
ከዋሸ
ክርስቲያንነቱ፣
ምሑርነቱ፣
እውነተኛነቱ ምኑ ላይ
ነው? ክርስቲያን
ለመሆን ክርስቲያን
ነኝ ማለት ይበቃል?
ክርስቶስን ሳያምንና
እንደ ትዕዛዙ ሳይኖር
ክርስቲያን መሆን
ይቻላል?
የዳን
ብራውን እናት በ
“ኤፒስኰፔሊያን” ቤተ
ክርስቲያን ኦርጋን
በተሰኘ የሙዚቃ
መሣርያ የሚያገለግሉ
ሴት ናቸው። በሰሜን
አሜሪካና በአውሮጳ
የሚገኙ የ
“ኤፒስኰፔሊያን”
አብያተ ክርስቲያናት
ደግሞ ወንድና ወንድን
(ሴትና ሴትን)
በማጋባት፣ እንዲህ
የመሳሰሉትን ጳጳስ
አድርጐ በመሾም
ምክንያት
እየተወዛገቡ
ከሚገኙት መካከል
ናቸው። ዳንም
የሰንበት ትምህርት
ከመከታተሉ ሌላ
ለጥቂት ጊዜ የወጣት
መዘምራን አባል
ነበር። “እንዴት
ክርስቲያን ሆነህ
የቤተ ክርስቲያንን
ትምህርት የሚጻረር
ድርጊት ትፈጽማለህ
ታዲያ?” ተብሎ
ሲጠየቅ፣ “አሳቤ
በዚህ ጉዳይ ላይ
ውይይት ለመፍጠርና
ዞሮ ዞሮ የአማንያንን
እምነት ለማጠናከር
ነው” ብሏል።
እንግዲህ ቅድም
ዳንኪራ ቤት ያዘወትራል
እንዳልነው ወንድም
የዚህኛውም መልስ ግር
ይላል። ሁለተኛ፣ ዳን
ምስጢራትን
በአዕምሮው ብርታት
ለመረዳት ብዙ ዝንባሌ
ያሳየ ሰው ነው።
ከዚህም ፍላጎቱ
የተነሣ ሁኔታዎችን
አጠማዝዞ ፈቃዱን
እንዲፈጽሙ ሲያደርግ
ይስተዋላል።
የደረሳቸውን
መጻሕፍት ርዕስ ብቻ
እንኳ ብናይ፦ “ምሽግ”፣
“መላእክትና ክፉ
መናፍስት”፣
“የስሕተት አሠራር”፣
“የሰሎሞን ቁልፍ”
የሚሉ ሃይማኖታዊ
ሐረጐች
ይገኙባቸዋል።
ለዳን ብራውን “ዳቪንቺ ኰድ” አራተኛ መጽሐፉ ነው። ከቀደሙት ከሶስቱ ጋር የሚመሳሰለው ሁላቸውም ስለ ስሕተት አሠራር፣ ስለ ግድያ፣ ስለ ወሲብ፣ ወዘተ ስለሚያወሱ ነው። ከላይ እንደ ገለጽነው የአንባቢን ስሜት ለመማረክና የመጽሐፍትን ሺያጭ ከፍ ለማድረግ እነዚህ ፍቱን መሣሪያነት አላቸው። ሶስተኛ፣ ከኰሌጅ ከተመረቀበት እ.ፈ.አ. ከ 1986 ጀምሮ “ዳቪንቺ ኰድ” እስከ ታተመበት እስከ 2003 ድረስ የሚረባ ሥራ ኖሮት አያውቅም። ሙዚቀኛነቱንም ሞክሮ አልቀናውም። ዞሮ ዞሮ ሲደክመው ተመልሶ እተማረበት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስተማሪ ሆነ። ቀድሞ ያሳተማቸው ሶስት መጻሕፍት እያንዳንዳቸው በቁጥር ከአስር ሺህ አልፈው አያውቅም። አራተኛ፣ አሥራ ሁለት ዓመት የምትበልጠውን ሴት ማግባቱ ነው። እንዲሁ ሲታይ ታዲያ ምን ይደንቃል? ያሰኝ ይሆናል። ደግሞ እስከ ተዋደዱ ድረስ ምን ያገባናል? ይባል ይሆናል። ሁለቱም ተገቢ አስተያየቶች ናቸው። ስለ ግለ ሰቡ ግን የሚያስረዱን ቁም ነገር ይኖራል። ዳን ከራሱ ጥቅም አልፎ ስለ እውነተኛ እምነት ሆነ ስለ ታሪክ እምብዛም የሚገደው ሰው አይደለም። በ 1991 ወደ ሆሊውድ ሲሄድ ጀማሪ ተማሪዎችን በማስተማርና ሙዚቃ በመድረስ የኑሮ እሽቅድድሙን ተያያዘው። በዚህ ውድድር በበዛበት ሁኔታ ውስጥ ሲታገል፣ ከላይ የጠቀስናትን ሴት ይተዋወቃል። ሴትዮዋ በሆሊውድ አርቲስቶችን የሚመለምልና የሚያስተዋውቅ ድርጅት ዲሬክተር ነበረች። ውሎ ሲያድር ልዩ ወዳጅነት ፈጠሩ። ከጥቂት ዓመታት በኃላ ጋብቻቸውን በሕግ ፈጸሙ፤ ተባለ። ይህቺው ሴት (ሚስቱ) እስካሁን ለሕትመት ያበቃቸውን ሥራዎቹን በማጠናቀር ይሁን በማስተዋወቅ ከፍተኛ ድርሻ እንዳላት ታውቋል። አምስተኛ፣ ዳን ብራውን በትውልዱና በባሕሉ አሜሪካዊ/አውሮጳዊ እንደሆነ መረሣት የለበትም። ይህም ማለት ስለሚጽፈው ስለ አይሁድ ባሕል (እንዲሁም የመጽሐፍ ቅዱስ ቋንቋና ዘይቤ) የራሱ ልምድና ባሕል ይወስነዋል ማለታችን ነው።
ወቅታዊነቱ
ምን ያመለክታል?
መጽሐፉ
በታተመበት ወቅት
የአሜሪካና የአውሮጳ
ፖለቲካዊና ባሕላዊ ሁኔታ
ምን ይመስል ነበር?
የ“ዳቪንቺ ኰድ”
እንዲህ እንደ ሰደድ
እሳት መዛመቱ ባጋጣሚ
ነውን? ይህን ሁኔታ
እንደሚገባ
ለመረዳት፣ ቢያንስ
ያለፉትን አሥር
ዓመታት መቃኘት
ይኖርብናል።
ባጭሩ፣
ክርስቲያናዊና
ዓለማዊ አመለካከት
ባላቸው ደራሲያን
መካከል ግብ ግብ
የተጧጧፈ ይመስላል።
እርግጥ ለደራሲያኑ፣ ለአታሚዎቹና
ጋሻ ጃግሬዎቻቸው
ትኩረቱ ዝናና ሃብት
ማካበቱ ላይ ብቻ ሊሆን
ይችላል።
ለተገነዘበው ግን
ወዳቀረብነው
መደምደሚያ መምጣት
አይቸግርም።
ለምሳሌ፣ ለሕጻናት
ተብለው የተደረሱ
ነገር ግን አዋቂውም
ሁሉ ሳይቀር
የተለቀቀበት ሁለት
ረድፍ መጻሕፍት ውስጥ
ክርስቲያኑ እንግሊዛዊ
ሲ.ኤስ.ሉዊስ (እ.ፈ.አ 1963
ሞተ) የደረሳቸው
“ናርንያ ክሮኒክልስ”
እና እንግሊዛዊቷ ጄ
ኬ ሮውሊንግ ከ 1997 ጀምሮ
የደረሰቻቸው “ሄሪ
ፖተር” የተሰኙ
ጥንቆላ-ገብ መጻሕፍት
ይገኛሉ።
ሌሎች
ክርስቲያን ደራሲያን
ደግሞ፣ ቲም ላሄይ
“ሌፍት ብሃይንድ”
የተሰኘውን፤ ሪክ
ዋረን “ፐርፐስ
ድሪቭን ላይፍ”፤
ብሩስ ዊልክንስ “ዘ
ፕሬየር ኦፍ ጄቤዝ”
ለገበያ ማቅረባቸው
ነው። በደረሱበት
መረዳት መጠንና የሚገኙበት
ማሕበረ ሰብ
በሚጠይቀው አኳኋን
አቅርበውለት የባለ ብዙ
መቶ ሚሊዮን ዶላር
ባለጸጋ ሆነዋል።
በዚህ ላይ ካቶሊኩ
ፊልም ተዋናይ ሜል
ጊብሰን “ዘ ፓሽን ኦፍ
ክራይስት” የተሰኘ
በወቅቱ የገነነ ፊልም
ሠርቶ አስተዋውቋል።
የአሜሪካ
ክርስቲያኖችም
በፖለቲካው ሂደት
ውስጥ ዋነኛ ሥፍራ
አግኝተዋል።
አንዳንዶች ይህን
ክስተት ለወንጌል
ስርጭት ጥሩ አጋጣሚ
ነው ሲሉ፣ ሌሎች
ደግሞ ወንጌልን ሰዎች
በሚፈልጉት ሁናቴ እንደ
መዝናኛ ማቅረብ
ከመሸቃቀጥ
አያልፍም፤ ጥራት
ይነሳዋል ይላሉ።
እኛስ “ሰዎች
እንዳይሸሹ፣
በፍቅርና በጥበብ
እንያዝ” ስንል አማኞች
እግዚአብሔርንና
የቤቱን ሥርዓት
እንዳያውቁ መበደልና
ማታለል አይሆንብንም
ወይ?
በዚህ ሁሉ ውስጥ አንድ የማይካድ እውነት አለ። ይኸውም፣ ክርስቲያን ደራሲዎችም ክርስትና ዋጋ ማስከፈሉን ሳይሆን እንደ ዓለማውያኑ ሁሉ ሰዎች ሊሰሙ የሚፈልጉትን አቀናብረው ሕዝቡን እየጋቱት መሆኑ ነው። የእነዚህም ትምህርት በአብዛኛው “ራስን ማሻሻል” በሚል ፍልስፍና ላይ የተመሠረተ እንጂ ጸጋን ስለ መለማመድ የሚያስረዳ አይደለም። ሕዝቡም ስልቹ ስለሆነ የተከታተለ መዝናኛ ይሻል። ሥጉ ስለሆነ ምሥጢራትን ለመፍታት በሚደረጉ ሙከራዎች እየተጠንላጠለ ራሱን ያዝናናል፣ ያረሣሣል። ቲም ላሄይና አጋሩ የጻፉት መጽሐፍ፣ መጽሐፈ ራእይን የተንተራሰ ቢሆንም አንዳንድ ዝርዝሩ ከነርሱ ግምት የመነጨ እንጂ ቃሉ የሚገነዘበው አለመሆኑን ማወቅ መልካም ነው።
እውነትና
ውሽትን መቀላቀል
ዳን
ብራውን እውነተኛ
ታሪክ ነው ብሎ
ያቀረበልን ድግስ
የሠመረ ይመስላል።
በዚህ ዘመን የሠፈነው
አንዱ አስተሳሰብ
“አታክርር” የሚል
ነው። ይህ አባባል
“እንደየሁኔታው
እንጂ፣ ፍጹም እውነት
ሊኖር አይችልም” ከሚል
አስተሳሰብ
ይመነጫል። ስለዚህ
ሌላውን ቅር ልታሰኝና
ልታገልለው ስለምትችል
“መዳን በኢየሱስ ብቻ
ነው” አትበል። ይልቅ
በሁሉም የሃይማኖት
ዘርፍ ውስጥ መልካም
ነገር አይጠፋም በል።
ደግሞም መልካሙን
ከያንዳንዱ ለቅሞ
መጠቀም የግለ ሰቡ መብት
እንጂ ድርጅታዊ ግዴታ
ሊሆን አይገባም፤
እንኳን ተጨምረህ
እንደዚሁም የዓለም
ጣጣዋ በዝቷል፤
ሚዛናዊነትን
እንጠብቅ።
እንቻቻል፤ እንተሳሰብ፤
ፍቅርና ሰላም
አንድነትን
እናጠናክር፤
ይሉናል። መቻቻሉና
መተሳሰቡ ባልከፋ።
እግዚአብሔር
እውነት ነው፤
ከእግዚአብሔር ውጪ
እውነት የለም፤ እውነት
ሁሉ በተገኘበት ደግሞ
የእግዚአብሔር እውነት
ነው (ዮሐንስ 1፡ 14-18፤
ቆላስይስ 1፡ 15-16፣ 20፤ 1ኛ
ጢሞቴዎስ 2፡ 5)። ይህም
እውነት ፍጹም ሰው
ፍጹም አምላክ በሆነው
በኢየሱስ ክርስቶስ
በኩል ብቻ በምልዐት
ተገልጿል።
የክርስቶስ ተከታይ
የሆኑት እምነታቸው
ይኸ ነው። ሌሎች ሌላ
እምነት ሊኖራቸው
ይችላል። እንግዲህ
ሚዛናዊ የሚሉት ውሎ
አድሮ እነርሱ
የሚሉትን ብቻ ነው።
እውነቱ እነርሱ ያሉት
የቆሙበትና የደረሱበት
ነው። ያልተስማማቸው ሁሉ
አክራሪ ነው።
ያልተስማማቸውንም
አቋም አክርረው
ከመቃወም አይቦዝኑም።
ዳን
ብራውን ስለ ራሱና
ስለ ሚስቱ የሰጠው
መግለጫ የተጨማመረ
እንደሆነ
ተደርሶበታል። ሊለው
ለሚፈልገው ጉዳይ
ተጠማዝዞ ድጋፍ
ለማግኘት ይጥራል።
ሚስቴ የኪነ ጥበብ
ታሪክ ተመራማሪ ነች
ይለናል።
አይደለችም። ሴቪል
ዩኒቨርሲቲ (ስፔይን)
የኪነ ጥበብ ታሪክ
ምርምር አካሂጄአለሁ
ይለናል።
ዩኒቨርሲቲው
ሲጠየቅ፣ መቼ ይሆን?
ነበር መልሱ። የታሪክ
ምሑር አለመሆኑ
እንዳይነቃበት ይሆን?
የቀድሞው የእንግሊዝ
ጠቅላይ ሚኒስትር
ዊንስተን ቸርቺል
የሮማ ካቶሊካዊት
ማሕበረ ምዕመን ናቸው
ይለናል።
አልነበሩም። ሉቭር
(ፓሪስ) መግቢያ ላይ
የሚገኘው ፒራሚድ ከ 666
መስታወት የተገጣጠመ
ነው ይለናል (መጽሐፈ
ራእይ 13፡ 18 ይመልከቱ)።
መሐንዲሶቹ ሲጠየቁ
ደግሞ የመስታወቱ
ቁጥሩ 687 ነው ይሉናል።
ማንን እንመን?
የሚጠቅሳቸው ሰዎች
(ለምሳሌ፣ ንጉሥ
ቁስጠንጢኖስ)፣
ሥፍራዎች (ሮም) እና
ሰነዶች (የንቅዔ
ጉባዔ) ታሪካዊና
የታወቁ ቢሆኑም
ከነዚህ ጋር ግን
አያይዞ አዘናግቶ
ተጨማሪና ያልተረጋገጠ
መረጃ አሾልኰ
ያቀርብልናል።
እንዲያውም በድፍረት
የተረጋገጠ ታሪክ ነው
ይለናል።
የጠቀስካቸው
ምሳሌዎች አሁን ምን
ይጐዳሉ ብለህ ነው?
ተራ ግድፈትስ ሊሆኑ
አይችልም ወይ? እንል
ይሆናል። አዎን፣
መጽሐፉ ልብ ወለድ
እንጂ እውነተኛ ታሪክ
ነው ባይለን ኖሮ
እንደ ቀላል ግድፈት
ሊታለፍ ይችል
ይሆናል። አሁን ግን፣
ስለ ሌላው ቁም ነገር
የጻፈውን
እንዳንታመን በቂ
ምክንያት ሰጥቶናል፤
እንድንጠረጥረው
ያስገድደናል
ማለታችን ነው።
በቅርብ ያለውን
እውነትና ራሱን በሚመልከት
ችላ ባይነት
ከታየበት፣ ሩቅና
እርግጠኛ
ያልሆነበትንማ ሲያስረዳ
ተላላ ካልሆነ ማን
ይቀበለዋል? ማለታችን
ነው። አንድ ተማራማሪ
ነኝ ባይ
በሚያቀርባቸው
ሐተታዎች ውስጥ ግድ
የለሽነትና ያልተጣሩ
መረጃዎች ከተገኙበት
ማዕረጉን ያጣል።
ይሻራል። ይዋረዳል።
ጥፋቱ ከበረታ ወደ
ወህኒ ሳይቀር
ይወርዳል። ዳን
ብራውን አድር ባይና
ለምቾቱ የተሸጠ
ተመራማሪ ነው፤
ለእውነት የቆመ ቅን
ልብና አዕምሮ
ይጐድለዋል።
በቤተ
ክርስቲያን ታሪክ ሆነ
በወንጌል ዕውቀት
ያልጸኑ ግን መልስ
እንዳገኙ ቆጥረው
ይቀበሉታል።
አጥብቀው ለያዙት
ስሕተት ድጋፍ
ይሆናቸዋል። ስለ
ራሳችን እንዲነገረን
የማንፈልገው እውነት
የለም? በውሸት
ራሳችንን የምናባብል
ስንቶች ነን?
እግዚአብሔር
ሳይናገር ተናገረ
የምንል?
የእግዚአብሔር ቃል
ያላለውን እንዲል
የምናጠማዝዝ? በእግዚአብሔር
አምሳል ተፈጥረን ሳለ
እግዚአብሔርን
በአምሳላችንና በምኞታችን
ልንመስለው
የምንደክም? ይህስ
አዝማሚያ ውሎ ሲያድር
ውሸቱን እውነት፣
እውነቱን ደግሞ ውሸት
ወደ ማለት አያመራም?
የዚህ መጽሐፍ አደገኛነት
እንግዲህ እዚህ ላይ
ነው።
የቤተ
ክርስቲያን ድርሻና ኃላፊነት
እንዴት ሊሆን
ይገባል?
የቤተ
ክርስቲያንን
ኃላፊነት ለመዘርዘር
ከመሞከር ይልቅ
እነዚህን ጥያቄዎች
መጠየቅ ይጠቅማል፣
እንላለን።
·
በዚህ
ዘመን በቤተ
ክርስቲያን አመራር
ላይ የሚገኙ
አገልጋዮች ምን ይመስላሉ?
የመጋቢነት፣ የቤተ
ክርስቲያን
አስተዳዳሪነት ወይም
የወንጌል አስተማሪነት
ብቃት ሳይኖራቸው
የተሰየሙ የሉም?
በቃሉ ዕውቀት የታነጹ፣
ቃሉንና የዘመኑን
ሁኔታ፣
የሚገኙበትንም
ባሕልና ዘመናዊነትን
ማገናዘብ ብቃት
የሚታይባቸው ስንቶች
ናቼው?
የሚያስተምሩትስ ትምህርት
ምን ዓይነት ነው?
ስንቶቹስ ይሆኑ
ወንጌልን ማትረፊያ
ያደረጉ?
ጥሪ
አለኝ ማለት ብቻውን
አይበቃም። የስነ
መለኰት ትምህርት
ቀስሜአለሁ ማለትም
እንደዚሁ። የንግግር
ቅልጥፍና አይበቃም።
“በሚያባብል በጥበብ
ቃል… በቃልና በጥበብ
ብልጫ… በሰው ጥበብ…
ወደ እናንተ
አልመጣሁም” (1ኛ
ቆሮንቶስ 2፡ 1-4፤
ቆላስይስ 2፡ 4) ይላልና።
እንግዲያስ፣
ለእውነተኛ ጥሪ
የቆረጠ ልብና የቃሉ
ዕውቀት መጣመራቸው
አስፈላጊ ነው።
ለማንኛውም፣ ልክ
የሆነ ነገር ሁሉ
ያስታውቃል፣ ይታያል።
ለጊዜው ማስመሰል
ይቻል ይሆናል፣ ኋላ
ግን መገለጡ
አይቀርም።
የዳን
ብራውንና የመሰሎቹ
መጽሐፍት እንዲህ
መዛመታቸው ቋንቋቸው
ግልጽና የሚያባብል
የሰው ጥበብ
የተካናቸው ስለሆኑ
ነው። ዳን የሰንበት
ትምህርት ሲከታተል
እንደነበረ
ተመልክተናል። እዚህ
ደረጃ ላይ የደረሰው
ለምን ይሆን?
ያስተማሪዎቹ ሕይወት
ምን ይመስል ነበር
ይሆን? መቸም
በአሜሪካ “ክርስቲያን
ነኝ” ማለት የተለመደ
ነገር ነው፣ ተቀባይነት
የማግኛ አንዱ መንገድ
ነው። ከዓለማውያን
እምብዛም የተለየ
አኗኗር አይጠይቅም፣
አይታይበትም፣
አይጠበቅበትም።
እርግጥ ይህ አባባል ሁሉንም
አይመለከትም።
ባጠቃላይ ግን
ክርስትና
በዲሞክራሲና በንግድ መንፈስ
ተቀያይጧል። በኛም
እንኳን ሳይጋባብን
አልቀረም።
·
የሞራል
ልቅነት በተዛመተበት
ዘመን ላይ
እንገኛለን።
የእግዚአብሔርን ቃል
ለምኞቱ ለማስገዛት
በሚሻ ትውልድና ባሕል
መካከል እንገኛለን። ባሕሉንና
የቃሉን እውነት
እንለያለን?
የአሜሪካኖች ባሕላዊ
ክርስትና የሐዲስ
ክርስትና መስሎን
አስተናግደነው
እንዳይሆን
እንፈራለን። የቤተ
ክርስቲያን አምልኰ
ሥርዓትና የአሰባበክ
ዘይቤ እውነት አሁን
ከምናየው ቴሌቪዥን
ጋር አይመሳሰልም?
“እግዚአብሔር ልቤን
ያውቀዋል፤ እግዚአብሔር
የውስጥ አምላክ
ነው…እያንዳንዱ እንደ
ተሰማውና እንደ ተተረጐመለት
ቃሉን ይወቅ…እኔ
የምረዳው እንደዚህ
ነው፤ እምነት የግል
ነው፤ አንተስ ብትሆን
ማን ነህና ነው
የምትመረምረኝ?”
የሚለው አባባል ፍጹም
እውነት የለም ከሚል
አስተሳሰብ የመነጨ
አይደለምን?
የእግዚአብሔር ቃል፦
“ሁሉን ፈትኑ፣
መልካሙንም
ያዙ…መንፈስንም ሁሉ
አትመኑ፣ ፈትኑ እንጂ
አትመኑ” ይለናል።
ለዚህ የምንሰጠው
አጸፋ፣ “አትፍረዱ…ዝም
በሉ፣ ምን አገባን?
ምንስ አታገለን” ነው?
ልኩን
የሚያውቁ ዝም ሲሉ
አመጽ ያይላል፣ ሐሰት
እንደ እውነት
ይቆጠራል። ይህ
በእግዚአብሐር ፊት
በደል ነው።
·
የቤተ
ክርስቲያን ትኩረት
በሚታየውና በግል
ልምምድ ላይ ብቻ
አተኩሮ ይሆን?
“በአእምሮ ሕጻናት
አትሁኑ፣ የበሰሉ
ሁኑ…አስተማሪ ልትሆኑ
ሲገባችሁ… እንደ ገና
የሚያስፈልጋችሁ
ወተት ነው” የሚለን
አስተሳሰባችንና ሥነ
ምግባራችን
ከስሜታዊነት ማለፍ
ስላልቻለ ይሆን
(ዕብራውያን 5፡11-14)? ቤተ
ክርስቲያንስ
የክርስቶስ መሆኗ
ቀርቶ የግለ ሰብ
ወይም የቡድን ድርጅት
እንደሆነች መታሰቡ
ምን ሊባል ነው?
·
ዳን
ብራውን ቤተ
ክርስቲያናችን ቢመጣ
እንዴት አድርገን
እናስተናግደው ይሆን?
“እዚህ ፊት ለፊት ቁጭ
በል…ጌታ
ይባርክህ…እግዚአብሔር
እንዴት የባረከው ሰው
ነው?…ይኸማ
ለአገልግሎት
ይጠቅማል…ጌታ
ይመስገን” ሳንል እንቀራለን
(ያዕቆብ 2፡ 1-4)? የትም
ፍጭው ዱቄቱን አምጪው
ነው? ትንግርት
የሚያደርግ ሰው ቢመጣ
ሰው ነቅሎ
እንደማይሄድ ምን
ማስተማመኛ አለ?
ከእግዚአብሔር ቃል
ጋር እንደሚገባ
ሕይወታቸው
ያልተያያዘ
ለውዥንብር የተጋለጡ
ናቸው። አንድ አገልጋይ
ለሚያገለግላቸው
ሊያደርገው የሚገባው
ዋነኛ ነገር ቢኖር
ራሱንና መሰሎቹን
ከማስተዋወቅ ይልቅ
በጌታ ቃልና በቤተ
ክርስቲያን ታሪክና ሥርዓት
አስተሳሰባቸውን
መገንባት ነው።
ኢየሱስ ሊልቅ፣ እውነተኛ
አገልጋዮቹ ሊያንሱ
ይገባል (ዮሐንስ 1፡
20-30፤ 3፡ 30)። አንድ አገልጋይ
ምዕመኑን ጉዳት ላይ
የሚጥለውና
የተሰጠውንም አደራ
የሚያበላሸው ራሱን
በቃሉ ብቁ ሳያደርግ
ሲቀር፣ ሊሰሙ
የሚፈልጉትን
ሲያስተጋባ ነው።
በዚህ ወቅት
ሊያሳስበን የሚገባው
ከደቀ መዝሙርነት
ይልቅ በዕለት ፕሮግራምና
እንቅስቃሴ ላይ
ትኩረት መደረጉ ነው።
ከተሰጠ ሕይወት ይልቅ
ስጦታ የሚያቀብለው
ቅድሚያ ማግኘቱ ነው።
ባሕል በክርስትና ላይ
እና ክርስትና በባሕል
ላይ የሚያደርገውን
ተጽዕኖ ለይቶ
አለማወቁ ላይ ነው።
የፈረንጆች ባሕላዊ
ክርስትና ክርስትና
እንደሆነ መቆጠሩና
የኛም ባሕል ያነሰ
መምሰሉ ነው።
·
የቤተ
ክርስቲያን ድርሻዋና
ኃላፊነቷ የጌታዋን
ምሕረት ማወጅ ነው።
ምሕረቱን በነጻ
ተቀብለናል፣ በነጻ
እንድንሰጥ ታዝዘናል
(ማቴዎስ 10፡ 8)። ዳን
ብራውን እንደ
ማንኛችንም ኃጢአተኛ
ነው። “አባት ሆይ፣
የሚያደርጉትን
አያውቁምና ይቅር
በላቸው” የሚለው
የጌታ ጸሎት ዳንንም
ይጨምራል (ሉቃስ 23፡ 34)።
ለመዳኑ ከጌታ ዘንድ
የተቀጠረለት ቀን
ከንግዲህ ይሆን?
ምናልባት አሁን ዓለም
ያቀዳጀችው መድረክና
ንብረት ክርስቶስ
በሕይወቱ ለሚሰራው
ድንቅ ሥራ ምስክርነት
የሚውል ቢሆንስ?
ጌታን ምንም አይደንቀውም፤
ምንም አያቅተውም።
የሰውን ልጆች ጠንቅቆ
ያውቃልና። አሳቡና
መንገዱ ከሰው አሳብና
መንገድ ጋር
አይገጥምም (ኢሳይያስ
55፡ 8)።
መደምደሚያ
“የማያውቁትን
ሁሉ መሳደብ”
ማሕበራዊ ሥርዓቶችን
በጭፍኑ ማውገዝ፣ ማትረፊያ
ማድረግ ወግ ሆኗል
(ይሁዳ 10)። ክቡር
ያልናቸውንና
የምንወዳቸውን ሁሉ
በአደባባይ
ማንቋሸሽ፣ የግልና
የወሉን ድንበር
ማደብዘዝ፣ ማፍረስ
የዘመናዊነትና
የምሑርነት ምልክት
ሆኖአል።
የተቀደሰውን ሲያራክስ፣
የነፍስህን ወዳጅ፣
አዳኝና ጌታ ሲደፍር
እንዴት አያስቆጣህም?
አብረህ መጓዝስ
እንዴት ይሆንልሃል?
እንዲህ
የመሰለው ሁኔታ
እየተባዛ፣ እየከፋ
እንደሚሄድ ጌታ
አስታውቆናል (ማቴዎስ
24፤ 2ኛ ጢሞቴዎስ 4፡ 3)።
በተለይ ደግሞ
የሠለጠኑ አገር ዜጎች
የመናገር
መብታቸውንና
መሰላቸታቸውን እንደ
ቀድሞዎቹ ግሪኰች
“አዲስ ነገርን
በመናገርና በመስማት”
ይወጡታል (የሐዋርያት
ሥራ 17፡ 21)። ባጭሩ፣ የዳንንና
የመሰሎቹን “በብልሃት
የተፈጠረ …መጨረሻ
የሌለው ተረት…ለዓለም
የሚመች ጨዋታ”
መስማትና ማስተባበል
ሥራ ፈት ከማድረግ
ወዲያ የሚፈጥረው
ትርፍ የለም (1ኛ ጢሞቴዎስ
1፡3-4፤ 4፡7፤ 2ኛ ጴጥሮስ
1፡16)።
ባገራችን
የስድሳ ስድስቱ
አብዮት ፈነዳ በተባለ
ማግስት፣ የቤተ ክርስቲያን
መሪዎችና ምዕመናን
ዋነኛ ጥያቄ
የማርክስንና
የዳርዊንን ድንገተኛ
የክህደት ትምህርት
ምን እናድርገው?
ነበር። ቤተ
ክርስቲያን አሁንስ
በዘመናዊነትና
በዲሞክራሲ ግርግር
ተገን የሚካሄደውን
ትርምስ ለመቋቋም ተዘጋጅታለች?
ወይስ ጌታዋ ስደት
ይዘዝላት?
እንግዲህ
የነዚህ አሁን
የጠቀስናቸው ሁለት
ምሑራን ትምህርት
ሊያስረዳ የሞከረው፣
ሰው በራሱ ብቁ
እንደሆነና
እግዚአብሔር
እንደማያስፈልገው፣
እንዲያውም
እግዚአብሔር ጨቋኞች
የጠነሰሱት ዕፅ ነው
ብሎ ነበር።
የትምህርቱም ውጤት
እነሆ፣ ለብዙ ትውልድ
የሚሆን መቅሠፍት
አመጣ። እግዚአብሔር
ከሌለ፣ ሰው ከዝንጀሮ
ካልተለየ፣ መረን ወጣ
ማለት ነው። ነፍስ
ማጥፋት በእግዚአብሔር
ዘንድ ላያስጠይቅ
ነው። መዳራት፣
መስረቅ ወዘተ የሞራል
ግድፈት ላይሆን ነው።
ታዲያ
ብዙዎች አገልጋዮች
የነዚሁኑ ምሑራንን
ትምህርት አጥንተው
ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር
እያስተያዩ
ማስጠናቱን
ተያያዙት። በዚህም
የአንዳንዶችን
እምነት አጽንተዋል።
የማይረሳኝ ግን፣
አንድ ወንድም፣
የማርክስን ስሕተት
ከማስተምር
የኢየሱስን እውነት
ባስተምር ይሻለኛል
ማለቱ ነበር።
እውነትም ሲታሰብ
ልኩን ሳናውቅና
ሳናሳውቅ ስሕተቱን
እንዲለይ ማሰብ
ምዕመንን ለባሰ
ስሕተት መዳረግ
ይሆናል።
ዛሬ
ደግሞ የ”ዳቪንቺ ኰድ”
የሚሞክረው ይህንኑ
የክሕደት ሥራውን
በምሑርነትና
በሥልጡንነት ተገን
ለማስፋፋት ነው።
መልኩና ድምጹ ተለወጠ
እንጂ መልእክቱ ያው
እንደ ጥንቱ ነው።
ኢየሱስ ሰው ብቻ
ከሆነ፣ የወንጌል
ምስክር በጥርጣሬ
ከታየ እምነታችን
ውድቅ ሊሆን ነው
ማለት ነው (1ኛ ቆሮንቶስ
15፡ 12-19)። ስለ ኃጢአት
መሞት አላስፈለገም
ማለት ነው፤ የኃጢአት
ነገር በሰው አእምሮ
የሚወሰን ነው ማለት
ነው። ኢየሱስ ሰው
ብቻ ከሆነ፣ ከኛ
በምንም አይለይም
ማለት ነው። ኢየሱስ
አምላክ ከሆነ እኛም
አማልክት መሆናችን
ነው። አመጽ
ይኸውላችሁ። ደግነቱ፣
የአንድን ትምህርት
እውነተኛነት
የምናረጋግጠው
በድምጽ ብልጫ፤
በገንዘብ ወይም በሰው
ብልሃት ብልጫ ወይም
ተቀባይነትን ለማግኘት
ከመነጨ ጥማት ሳይሆን
ውስጣችን በሚኖረው
ሕያው በሆነው በክርስቶስ
መንፈስ ነው። ይኸው
መንፈስ ደግሞ ቅዱስ
ቃሉን ያበራልናል። የቤተ
ክርስቲያን
ትምህርትና የቅዱሳን
ሕብረትና ጸሎት ደግሞ
ይጠብቀናል
(የሐዋርያት ሥራ 6፡ 4፤
2፡ 42፤ ኤፌሶን 4፡ 12-16)።
“ዓለም የማያየውና
የማያውቀው ስለ ሆነ
ሊቀበለው የማይቻለው
የእውነት መንፈስ …
ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር
በውስጣችሁም
ስለሚሆን እናንተ
ታውቃላችሁ” ይለናልና
(ዮሐንስ 14፡17)።
ከዚህ
አኳያ፣ ለሁላችንም
ጥያቄው ይኸ ነው፦
የእግዚአብሔርን ቃል
ለማጥናት ወይም የ
“ዳቪንቺ ኰድ” ሲኒማ
ለማየት ጥሪ ቢደርሰን
የቱን እንመርጣለን?
“እንደ ሽንገላ ባለ
ተንኰል በሰዎችም
ማታለል ምክንያት፣
በትምህርት ነፋስ ሁሉ
እየተፍገመገምን
ወዲያና ወዲህ
እንዳንሳፈፍ” ምን
ጥንቃቄ እያደረግን
ነው (ኤፌሶን 4፡14)? ይህም
በዳን ብራውን
ትምህርት ብቻ
የሚወሰን ሳይሆን፣
በቤተ ክርስቲያን ስም
የሚደረገውን ሁሉ
ይጨምራል።
የምናምነውን
ጠንቅቀን እንወቅ።
“ዘወትር የተዘጋጃችሁ
ሁኑ… የብርሃን ልጆች
ናችሁ… እንግዲያስ
እንንቃ፣ በመጠንም
እንኑር… አናንቀላፋ”
ተብለናል (1ኛ ጴጥሮስ
3፡ 15፤ 1ኛ ተሰሎንቄ 5፡
4-7)። ዝግጁ መሆን
እንዲሁ አይገኝም፤
ራስን ማለማመድ
ይጠይቃል። በጸሎትና
በቃሉ ዕውቀት ማደግን
ይጠይቃል። ቤተ
ክርስቲያን
በማስተዋል የማደጊያ
ክልል ናት።
ተገናኝተን በስሜት
ተሟሙቀን መለያየት
ብቻ ከሆነ እንጫጫለን።
በቀላሉ
እንወሰዳለን።
የምንሰማቸውን
መልእክቶች ጥራት መመርመር
ያሻናል።
የተናጋሪዎቹን
ማንነት ታሪካቸውን
ሕይወታቸውን ለይቶ
ማወቅ ከመታለልና
ከማታለል
ይጠብቀናል።
የስሕተት ትምህርት
አደገኛነቱ
የትምህርቱ አራማጆች
ስሕተት መሆኑን
አለማወቃቸው ላይ
ነው፤ ትክክል ነው
ብለው ደፍረው
ማስተማራቸው ላይ
ነው። እውነትን
የምንሻ ከሆንን ግን
“ነገሩ እንደዚህ
ይሆንን?” እያልን
መመካከርና ቃሉን
“በሙሉ ፈቃድ መቀበል”
ይኖርብናል
(የሐዋርያት ሥራ 17፡ 11፤
ዕብራውያን 10፡ 24-25)።
Óምአ2006