እግዚአብሔርን መውደድ ማለት…
እግዚአብሔርን መውደድ ማለት
ክፋትን መጥላት ከሆነ
ከዚህ ትንሽ ከዚያ ትንሽ
ነፍስህን እንዲህ ካባዘነ
የማይለይልህ፣ የማትቆርጠው
ኸረ እስከ መቸ ነው
ስም ቀየርክለት እንጂ እኰ
የባብ ልጅ እባብ ነው
ጨለማን መውደድ ማለት
ብርሃንን መጥላት ከሆነ
ወይ ፈጽሞ ካልሞተ
ወይንም ፈጽሞ ካልዳነ
ከሁለት መሃከል መሆን
ከጤናና ከጉድለት
የባሰ ሥቃይ እኰ ነው
ሰላም የማይገኝበት
ጨለማን ከብርሃን ቀላቅሎ
እስቲ በል ምን ይገኛል
ወይ አንደኛውን ይጠላል
ወይ ሌላኛውን ይወድዳል
እንጂ እንዳሰብከው ልትኖር
በብልጠትህ እንደ ሞከርኸው
ብታባብለው ብታሳምረው
እባብ እባብን ነው ‘ሚወልደው…
Óምአ2006
