‡ የሰው ዘመኑ
ዕድሜህ ስንት ነው?
የትኛውን ዕድሜዬን ነው?
ስንት ዕድሜ አለህ?
ሶስት
ምንና ምን ናቸው?
የልደቴ ሰላሣ ነው። የመከራዬ መቶ ሰላሣ ነው። የደስታዬ ቢደማመር አምስት ቀንም አይሞላም። ለዚያውም ሁለቱን አላስታውስም። የሰው ዕድሜ ምን አላት ብለህ ነው? በለቅሶ ወደ ዓለም ይገባል። አልቅሰውለት ይሰናበታል። … ይልቅ ቡናው ሳይበርድ አቀብለኝ።
ገጽ 1
? አሜሪካ መሄድ ወይስ መንግሥተ ሰማያት የቱ ይሻልሃል?
‡ አሜሪካ ከመሄድና … መንግሥተ ሰማያት ከመሄድ …
