የእምነት አቋም መግለጫ ምንነትና አስፈላጊነት በምትኩ አዲሱ ክፍል አንድ መግቢያ ሁለተኛው ደግሞ፣ የእምነት አቋምዎን እንዴት ይገልጹታል? የሚል ይሆናል። ምናልባት፣ ከየት ልጀምር? የቱን ይዤ የቱን ልተው? ሳይሉ አይቀርም። ወይንም በርግጠኝነት፦ "እምነቴ መንፈስ ቅዱስ እንደ መራኝና እንዳረጋገጠልኝ ነው" ወይም "ምን ጥያቄ
ያሻዋል ደግሞ፣ www.jesuswalk.com እምነቴም አቋሜም ኢየሱስ ነው፤ መሠረቴም በቃሉ ውስጥ የሠፈረው ሁሉ ነው" ይሉ ይሆናል። ምላሽዎ ስህተት አይደለም። እንዲያውም ጥሩ ጅማሬ ነው። ሆኖም ሰፊና ድፍን ከመሆኑ የተነሣ ጥያቄውን እንደሚገባ ዘልቆ
አያብራራም። እንግዲህ ቀጥሎ ባሉት ገጾች ላይ የእምነታችን አቋም መግለጫ ምንነትና አስፈላጊነት ከእግዚአብሔር ቃልና ከክርስቶስ
ቤተ ክርስቲያን የሕይወት ምስክርነት ጋር በማያያዝ ለመረዳት እንሞክራለን። የምንገኝበት ዘመን ጥንቲቷ ቤተ ክርስቲያን ካሳለፈችው ጋር ሲስተያይ ብዙ ልዩነት አይታይበትም። ዛሬም እንደ ጥንቱ
የወንጌልን እውነት የሚቀናቀኑና የሚያዘናጉ ነገሮች በዝተዋል። የቤተ ክርስቲያን ሥልጣን ተንቋል። ግለኝነት እያየለ ነው።
የምዕመኑ ትኩረት በሚታየውና በሚጨበጠው ነገር ላይ ሆኗል። የወንጌልም ትምህርት ይህን የጊዜውን ሁኔታ እንዲያጸባርቅና
የሰሚውንም ስሜት እንዲያረካ ተመቻችቶ እየቀረበ ነው። የእምነት አቋማችንን አጥርተን ማወቅ ያለብን ለዚህ ነው። በተጨማሪ፣ የዚህ ጽሑፍ ዓላማ አቧራ እየጠጡ ያሉትን የጣልናቸውን ታሪካዊ ቅርሶቻችንን አራግፈን እንድናነሳ ለማሳሰብ
ነው። እግረ መንገዳችንን እነዚህ ቅርሶች የተዘነጉበትን ምክንያት እንመረምራለን። እስቲ ጌታ ይርዳን። የእምነታችን አቋም መግለጫ ምንነትና አስፈላጊነት የእምነት አቋም መግለጫ (እ.አ.መ) አራት የማይነጣጠሉ አሳቦችን ያካትታል፦ በመጀመሪያ፣ ግለኛ ሳይሆን የጋራ እምነት
ስለ መሆኑ፤ ሁለተኛ፣ ከቀደሙት የእምነት አባቶችና እናቶች የተቀበልነው ወይም የወረስነው ስለ መሆኑና፤ ሦስተኛ፣
የእምነታችንን ሚዛን ለመጠበቅና ለማስረዳት ዋነኛና መሠረታዊ የሆኑ ትምህርቶችን ስለ ማዘሉ፤ በመጨረሻም፣ ተፈትኖ የወጣ
ስለሆነ አማኒያን ሁሉ ሊቀበሉት የተገባ ስለመሆኑ፤ [በተጨማሪ ማቴዎስ 7.28፣ የሐዋ.ሥራ 2.42፣ ሮሜ 6.17፣ 1ኛ
ቆሮ 12.28-29 ይመልከቱ
ሁለት የማይነጣጠሉ ጥያቄዎችን በመጠየቅ እንጀምራለን፤ የመጀመሪያው፣ የእምነት አቋም መግለጫ ምንድነው? የሚል
ሲሆን፣
እግዚአብሔርን ለማወቅ፣ ሰውን ዓለማትንና ዘመናትን ለመረዳት፣ እግዚአብሔርም ከኛ የሚጠብቀውን ለመለየት ቃሉን ሥርዓትና ምልዓት ባለው መልኩ ማጥናት አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው። የእምነት አቋም ባጭሩ በዚሁ ተግባር ላይ የተመሠረተ ነው።
እኔ አምላክ ነኝ እንጂ ሰው አይደለሁምና፣ በመካከልህ ቅዱሱ ነኝና፤
ሰው ሆይ፣ መልካሙን ነግሮሃል
እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን ታደርግ ዘንድ፣ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፣ ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሄድ ዘንድ አይደለምን?
እግዚአብሔር ከሰው ይህን እሻለሁ ሲል፣ በጎና ክፉ ምን እንደሆነ ሳያስታውቀው አይደለም፤ ምሕረትንና ትሕትናን ሳያሳየው አይደለም፤ በሌላ ስፍራ፣
"መሐሪ ነኝና፣ ለዘላለም አልቆጣም፣ … ከመሥዋዕት ይልቅ ምሕረትን፣ ከሚቃጠልም መሥዋዕት ይልቅ እግዚአብሔርን ማወቅ እወድዳለሁና… እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና…" እንደሚል ማለት ነው።
ከቀደሙት ቅዱሳን ሲወርድ ሲዋረድ የተላለፈልንን እምነት ማውሳት የሥጋዊነት ምልክትና ኋላ ቀርነት፣ ሲብስም የመንፈሳዊነት ጉድለት እንደሆነ ሲታሰብ ቆይቷል። ከዚህም የተነሣ አብዛኛው ምዕመን እምነተ አቋሙን በቅንጥብጣቢው እንጂ አሟልቶ እንዳይገነዘበው ተደርጓል። ይህ አሣዛኝና አሳሳቢ አዝማሚያ ነው።
ቤተ ክርስቲያን የሞተላት ጌታዋና የተከታዮቹ የጸሎት ፍሬ፣ የእንባና የእርዛት፣ የስደትና እስራት፣ የደስታና የደም ፍሬ እንደመሆኗ ታሪኳን ማወቅ ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል። ቤተ ክርስቲያን ያለችበትን ሁኔታ መገንዘብ የምትችለው የኋላውን በመናቅ አይደለም። ዘመናዊነት ብርቅ አይደለም። በገዛ ዘመኑ ብርቅና ዘመናዊ ያልሆነ የለምና። ሥልጣኔ የሰውን ዕድሜ ያክል የኖረ ነው። ኃጢአት አይሠለጥንም፣ ጽድቅ አይሻሻልም። ሰው መሠረቱንና ቀለሙን አይለቅም።
የረባ ግንዛቤ የሚገኘው ከሌላ በመኰረጅ ሳይሆን፣ ወንጌል የፈለቀበትንና ያደገበትን ባሕል ጠንቅቆ በመረዳትና ከተያዘው ባሕል ጋር በማጣጣም ነው። የትኛውም ባሕል ከሌላው አይሻልም። ለምሳሌ፣ የአሜሪካኖች ባሕል ከአበሾቹ አይሻልም። ሁለቱም እንከን አይታጣባቸውም። ሁለቱም የሰው ልጅ የኑሮ ትግልና ልምድ ውጤት ናቸውና። እንደ ተፈቀደለት መጠን የወንጌል ብርሃን የትኛውንም ባሕል ያጠራዋል፣ ይቀይረዋል። ክርስቲያናዊ ባሕልን፣ ክርስቲያናዊ ቋንቋና ሥነ-ምግባርን ያጐናጽፈዋል። ወንጌል በደረሰበት ሁሉ እንደየባሕሉ አምልኮውና ሥርዓቱ ሊለያይ ይችላል። ወንጌል መሠረታዊ መልእክቱ ሳይዛነፍ እንደየባሕሉ የሚ-ለ-ያይ ቅርጽ ይኖረዋል ማለት ነው።
የኢትዮጵያ ክርስትና አቅራቢያው ከሚገኘው ባሕል ጋር ሳይመሳሰል ለውጥ ማምጣት ሆነ ሥር ሰዶ ማደግ አይችልም። እንዲያውም ለገዛ ባሕሉ ባእድ ወደ መሆን፣ በተመልካች ዘንድ ወደ መጠርጠር ይደርሳል ማለት ነው።
በዚህ ዘመን ትኩረቱ በመንፈሳዊ ልምምዶች ላይ የሆነ ይመስላል። አንዳንዶቹ ልምምዶችና ትምህርቶች ሰሞናዊ መልክ ይታይባቸዋል። ይህን አባባል ለማረጋገጥ እነዚህን ሃያና ሰላሣ አመታት መቃኘት ይበቃል።
በስሜታችን የምንለማመዳቸው አያስፈልጉም አንልም። እግዚአብሔር የስሜታችንና የሁለንተናችንም ጌታ ነውና። ስሜት ግን በመሠረታዊ የእምነት ትምህርት ሚዛኑ ካልተጠበቀ ለስሕተትና ለግለኛ ሕይወትና አመራር ይዳርጋል። የእምነት አቋም መግለጫ ቦይ ቢሆን የሕይወት ልምምድ ደግሞ ውሃው ነው ማለት ነው። ሁለቱም ይጠባበቃሉ። ውሃው ፈሩን ለቅቆ እንዳይባክን፣ መረን ወጥቶ ጥፋት እንዳያስከትል ቦዩ ወደ አንድ ግብ ይመራዋል። ያም ግብ ኢየሱስ በሁሉ ላይ ጌታ እንደ ሆነ በሁሉ አቅጣጫ ማወጅ ነው።
ለመሆኑ የቤተ ክርስቲያን እምነተ አቋም በአብዛኛው ማሕበረ ምዕመን ዘንድ ሰርጾ የማይታወቀው ለምንድነው? ስድስት ምክንያቶችን መጥቀስ ይቻላል። እነዚህም የሚከተሉት ናቸው፦
የእምነት አቋም መግለጫን ምንነትና አስፈላጊነት አለማጤን
ክርስትና መገለጥ ብቻ ሳይሆን ታሪካዊም መሆኑን መዘንጋት
በፍጹም አሳብ ጌታን አለመውደድ
"መንፈሳዊ" ለሚለው ቃል የሚሰጠው ትርጉም አለመሟላት
የቤተ ክርስቲያን ሥልጣንና የግለ ሰብ ነፃነት ድንበር መደብዘዝ
የሚሲዮናውያን አስተዋጽኦ የራሱን ዐመል ጥሎ ማለፍ። እነዚህን አንድ ባንድ እንያቸው፣
1. ምንነቱንና አስፈላጊነቱን አለማጤን፣
የእምነታችን አቋም መግለጫ ከእግዚአብሔር ቃል እንደተውጣጣ ሳይሆን ሰዎች ከፈቃዳቸው የቀመሙት፣ ከቤተ ክርስቲያን አብራክ እንደ ተገኘ ሳይሆን ደረቅ ቃልና መንፈሳዊነት የጐደለው እንደሆነ ይታሰባል። የእምነት አቋማቸውን በአምልኮ ሰዓት የሚያውጁ ማኅበረ ምእመናን መንፈሳዊነት እንደጎድላቸው ይታሰባል። ይህ ስሕተት ነው። ይልቅ የእ.አ.መ. በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ለመጠበቅ፣ ለመንጋው የማይራሩ ግለ ሰቦች አምኒአንን ወደ ኋላ ለመሳብና ለማጣመም እንዳይችሉ ዓይነተኛ መሣሪያ ሆኖ ኖሯል።
ዝግ ብሎ ላጤነው ተራው ምዕመን ሳይቀር እንደ ደረሰበት የጸጋ እርምጃ መጠን ስለ ክርስቶስ አዳኝነት፣ ስለሚመጣው ዓለም፣ ስለ ቤተ ክርስቲያን፣ ወ.ዘ.ተ. የራሱ አቋምና መረዳት አለው። የእምነት አቋም መግለጫ ይህንና ይህን የመሰለውን ያደራጀዋል፤ ቅርጽ ይሰጠዋል፤ የጋራ አቋም ያጎናጽፈዋል።
እንግዲህ አንድ የአማኒያን ትውልድ ስለ ክርስቶስ የተቀበለውን ወግ ለሚቀጥለው ትውልድ የሚያስተላልፍበት ዓይነተኛ መንገድ ነው፤
"እኔ ደግሞ የተቀበልሁትን ከሁሉ በፊት አሳልፌ ሰጠኋችሁ" ይላልና።
በመሠረቱ የእ.አ.መ. በታሪካዊ ይዘቱ አራት ገጽታዎች ይታይበታል፤
ሀ. አጭርና ቀጥተኛ ነው። ለምሳሌ፣ የዓሣ ምስል
![]()
ለቀደሙት የሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች መለያቸውና ምሥጢራዊ ቋንቋቸው ነበረ። ይህ ምስል የተመረጠበት ምክንያት አለው። ሐዲስ ኪዳን የተጻፈው በግሪክኛ ሲሆን፣ በዚሁ ቋንቋ ዓሣ "ኢክቱስ" ይሰኛል። የ"ኢክቱስ" እያንዳንዱ ፊደል ደግሞ ሲተነተን "ኢየሱስ ክርስቶስ ቴኡ ኢኦስ ሶቲር" ማለትም "ኢየሱስ ክርስቶስ፣ የእግዚአብሔር ልጅ፣ አዳኝ" የሚል ትርጉም እንዳዘለ እንረዳለን።
አጭርና ቀጥተኛ መሆኑ የእግዚአብሔርን ቃል ማወቅ ለሚሹ፣ ምኑን ምን ብዬ ከየት ልጀምር ለሚሉ ሁሉ ምሪት ይሆናቸዋል፤ ለጥረታቸው ቅርጽ ይሰጠዋል ማለት ነው።
ለ. ለማስታወስ እንዲረዳ በዜማ ቅኔ የተያዘ ነው፣
እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ
ከእግዚአብሔር
ጋር መተካከልንመቀማት
እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥ነገር
ግን የባሪያን መልክ ይዞበሰውም
ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥በምስሉም
እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ለሞትም
ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ።በዚህ
ምክንያት ደግሞእግዚአብሔር
ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፥ከስምም
ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው፤ይህም
በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉበኢየሱስ
ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥መላስም
ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብርኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው።
እርሱም የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው።
የሚታዩትና
የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑወይም
ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥በሰማይና
በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልናከፍጥረት
ሁሉ በፊት በኵር ነው።ሁሉ
በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል።እርሱም
ከሁሉ በፊት ነውሁሉም
በእርሱ ተጋጥሞአል።እርሱም
የአካሉ ማለት የቤተ ክርስቲያን ራስ ነው።እርሱም
በሁሉ ፊተኛ ይሆን ዘንድ፥መጀመሪያ
ከሙታንም በኵር ነው።እግዚአብሔር
ሙላቱ ሁሉ በእርሱ እንዲኖር፥በእርሱም
በኩል በመስቀሉ ደም ሰላም አድርጎበምድር
ወይም በሰማያት ያሉትን ሁሉለራሱ
እንዲያስታርቅ ፈቅዶአልና።መ. ከውጭና ከውስጥ ስደትና ችግር ሲነሣ ስሕተትን ለማረም፣ እውነቱን ደግሞ ለማስረገጥ እንደ ሁኔታው የሚለወጥ ነው።
ይህም
በኢየሱስ
ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ። እርሱንም እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተስሪያ አድርጎ አቆመው፤ ይህም በፊት የተደረገውን ኃጢአት በእግዚአብሔር ችሎታ ስለ መተው ጽድቁን ያሳይ ዘንድ ነው፥ ራሱም ጻድቅ እንዲሆን በኢየሱስም የሚያምነውን እንዲያጸድቅ አሁን በዚህ ዘመን ጽድቁን ያሳይ ዘንድ ነው …ነገር
ግን የሆነው ሁሉ፥ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን፥ ከእግዚአብሔር ነው …እግዚአብሔር
በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ። እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን። እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው።ነገር
ግን በዚያ በሚመኩበት እንደ እኛ ሆነው ሊገኙ፥ ምክንያትን ከሚፈልጉቱ ምክንያትን እቆርጥ ዘንድ አሁን የማደርገውን ከዚህ ወዲህ ደግሞ አደርጋለሁ። እንደ እነዚህ ያሉ ሰዎች የክርስቶስን ሐዋርያት እንዲመስሉ ራሳቸውን እየለወጡ፥ ውሸተኞች ሐዋርያትና ተንኮለኞች ሠራተኞች ናቸውና። ይህም ድንቅ አይደለም፤ ሰይጣን ራሱ የብርሃንን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለውጣልና። እንግዲህ አገልጋዮቹ ደግሞ የጽድቅን አገልጋዮች እንዲመስሉ ራሳቸውን ቢለውጡ ታላቅ ነገር አይደለም፤ ፍጻሜአቸውም እንደ ሥራቸው ይሆናል …እንደ ክርስቶስ ትምህርት ሳይሆን፥ እንደ ሰው ወግና እንደ ዓለማዊ እንደ መጀመሪያ ትምህርት ባለ በፍልስፍና በከንቱም መታለል ማንም እንዳይማርካችሁ ተጠበቁ።
በዚህ መሠረት፣ በመጀመሪያዎቹ አራት መቶ አመታት የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ አራት ዓይነተኛና በወቅቱ ለተነሱ ኑፋቄዎች ማፍረሻ የሚሆኑ የእምነት ሕይወት ማጽኛና መመሪያዎች ተላልፈውልናል (በዚህ ርዕስ ሥር ከሚቀርቡት ተከታታይ ክፍሎች በመጨረሻው ክፍል ላይ ይመልከቱ)።
የእምነታችን መካከለኛና መሠረቱ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ይህም እውነት በብሉይና በሐዲስ ኪዳን ትምህርት ላይ የታነጸ ነው። ሆኖም የሰው ወግና ሥርዓት የኢየሱስን መካከለኛነት በዘመን ሁሉ ሲቀናቀነው ይታያል። በቃሉ ላይ የተመሠረተ ትምህርት ኢየሱስን እያወጀ ይተረጉመዋል። በትንሣኤው እውነት ኃይል ወንጌሉን ለዓለም ሁሉ እያዳረሰ የሰጠውን ትእዛዝና ለርሱ ክብር የሚገባውን አምልኰ ያስረዳል፣
እኔ
ለኬፋም
ታየ በኋላም ለአሥራ ሁለቱ … እንግዲህስ እኔ ብሆን እነርሱም ቢሆኑ እንዲሁ እንሰብካለን እንዲሁም አመናችሁ … ትንሣኤ ሙታንስ ከሌለ ክርስቶስ አልተነሣማ፤ክርስቶስም
ካልተነሣ እንግዲያስ ስብከታችን ከንቱ ነው እምነታችሁም ደግሞ ከንቱ ናት፤[1
ኛ ቆሮንቶስ 15. 3-5፣ 11፣ 13-14]ሠ
. የማሕበረ ምዕመኑን የእምነት አቋም እያስረዳ ከሌሎች የእምነት ክፍሎችና ከሰፊው ሕብረተ ሰብ ባሕልና አስተሳሰብ የሚለይበትን አኳኋን ይገልጻል፤ የሕይወት ልምምዶችን ደግሞ ይተረጉማል።
ይቀጥላል…

Copyright © 2006 ethiopianchurch.org