ማስታወቂያ
1. ቢታንያ የጸሎት አገልግሎት
ቢታንያ፣ ማርያም እህቷ ማርታና ወንድማቸው አልዓዛር የሚኖሩባት መንደር ናት።
ኢየሱስ ሲያልፍ ወደ ቤታቸው ጐራ ማለት ይወድ ነበር። ቤታቸው ሁሌ ለጌታ የተከፈተ ነበር። ያስተናግዱት ነበር፤ ያሳርፉት ነበር። እርሱም ያስተምራቸው ነበር። ይጸልይላቸው ነበር። ከሦስቱ ጋር በቅርብ ይተዋወቅ ነበር። ይወዱት ነበር፤ ይወዳቸው ነበር። ሲባክኑ አረጋግቶአቸዋል። ሲያዝኑ አጽናንቷቸዋል። ኢየሱስ ባለበት ይህና ሌላም ብዙ መልካም ነገር ይሆናል።
ብዙ ወገኖቻችን ከዚህ አገር ሩጫ የተነሳ እየባከኑ ነው። ለጽሞና ጊዜና ሥፍራ እየጠበባቸው ተቸግረዋል። ይህን በማሰብ ይጠቀሙ ዘንድ ይህ ደጅ ከብዙ ጸሎት በኋላ ተከፍቶላቸዋል።
በአንድ ጊዜ ሁለት ሰው ማስተናገድ የሚችል ቦታ ተዘጋጅቷል። ሊገለገሉ የሚፈልጉ ሁሉ እነዚህን መመሪያዎች ይከተላሉ፦
· ከሦስት እስከ አምስት ቀኖች መቆየት ይፈቀዳል፤
· ሕጻናት አይስተናገዱም፤
· መስተንግዶው ምግብ፣ መጓጓዣ፣ ኢንሹራንስ፣ ወዘተ አይጨምርም፤
· በቀን አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትና የጸሎት ጊዜ ይኖራል፤
· በዚህ አድራሻ መሠረት በቅድሚያ መመዝገብ ያስፈልጋል
ቴሌፎን፦ (615) 460.2433
ኢ-ሜይል፦ tsehaialemu@yahoo.com
2. ለጥናታዊ ጽሑፎች የቀረበ ጥሪ
ጥናታዊ ጽሑፎችን፣ የሕይወት ምስክርነት፣ ወዘተ፣ በማቅረብ ለመሳተፍ የምትፈልጉ በ info@ethiopianchurch.org ላኩልን። ጥናቱ በነዚህ ብቻ ሳይወሰን የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ይጥራል፦
· በውጭ አገር የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት እንቅስቃሴ ባለፉት 30 ዓመታት ምን ይመስላል? የሚገኙበት ባሕል በአምልኰ ሥርዓታቸው ላይ ምን ለውጥ አስከትሏል? ከአስርና ሃያ ዓመታት በኋላስ ምን መልክ ሊኖራቸው ይችላል?
· በውጭና አገር ውስጥ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት ምን ዓይነት ግንኙነት ሊኖራቸው ይገባል?
· የሴቶች የአገልግሎት ድርሻ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ምን ይመስላል? እንዴትስ ሊሆን ይገባል?
· ቤተ ክርስቲያንን ሊያሳስቧት የሚገቡ ዋነኛ ጉዳዮች ምንድናቸው? ለዚህስ ምን ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ነው?
· በዚህ ዘመን ቤተ ክርስቲያን ምን ዓይነት አስተዳደር ያስፈልጋታል?
· መንፈሳዊነት ምንድነው? መንፈሳዊስ ማነው?
· የእግዚአብሔርን ቃል እንዴት እንተርጉም? ሁሉም “እንደ ተገለጠለት” ይተርጉም?
የጥናቱ ይዘትና መጠን፦
· ከ 6-8 ገጽ በ ግእዝ ፊደላት ተቀርፆ በኢ-ሜል የተያያዘ
· ከግድፈት ነጻ የሆነ፤ በቀላል አማርኛ የተጻፈ፤ አሳቡ የተያያዘና ተግባራዊ ለማድረግ የተመቸ
· ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር የሚታይበት
· የጥናቱን አዘጋጅ ሕጋዊ ስምና አድራሻ የያዘ (አድራሻው ይፋ አይሆንም)
· እንደ አስፈላጊነቱ ጥራቱንና መጠኑን በተመለከተ መጠነኛ እርምት ሊደረግ ይችላል
· በጽሑፉ ውስጥ ለሠፈረው አሳብ ተጠያቂው የጥናቱ አዘጋጅ ይሆናል
3. አዲስ መጽሔት ተዘጋጅቶ እየተሸጠ ነው።
የአንዱ ዋጋ፦ መላኪያውን ሳይጨምር $5.00 ነው። ከሃያ በላይ ኮፒ የሚገዙ 10% ቅናሽ ያገኛሉ። አድራሻችን፦
BHBC/Ethiopianchurch.org
2100 Belmont Blvd
Nashville, TN 37212
ነው።

