የእምነት አቋም መግለጫ

[ንቅዔ 325፤ 381 ዓ.ም.]

 niceaCouncilሁሉን በሚችል፣ ሰማይንና ምድርን፣ የሚታየውንና የማይታየውን በፈጠረ፣ አንድ አምላክ በሚሆን፣ በእግዚአብሔር አብ እናምናለን።

እርሱ ብቻ የአብ ልጅ በሚሆን፣ ዓለም ሳይፈጠር ከአብ በተወለደ፣ ከአምላክ በተገኘ አምላክ፣ ከብርሃን በተገኘ ብርሃን፣ ከእውነተኛ አምላክ በተገኘ እውነተኛ አምላክ፣ በህልውናው ከአብ ጋር አንድ የሆነ፣ በተፈጠረ ሳይሆን በተወለደ፣ ሁሉ በእርሱ በሆነ፣ ስለ እኛ ስለ ሰዎች ስለ ደኅንነታችንም፣ ከሰማይ በወረደ፣ በመንፈስ ቅዱስ፣ ከድንግል ማርያም ሥጋ ነስቶ ሰው በሆነ፣ በጴንጤናዊው በጲላጦስ ዘመንም ስለ እኛ በተሰቀለ፣ በሞተ፣ በተቀበረም፣ በቅዱሳት መጻሐፍትም እንደ ተጻፈ፣ በሦስተኛው ቀን ከሙታንም ተለይቶ በተነሣ፣ ወደ ሰማይም በወጣ፣ በአብ ቀኝ በተቀመጠ፣ በሕያዋንና በሙታንም ሊፈርድ ዳግመኛ በክብር በሚመጣ፣ ለመንግሥቱም ፍጻሜ በሌለው፣ በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ፣ እናምናለን።

ከአብና ከወልድ ጋር በሚሰገድለትና በሚከበር፣ ከአብና ከወልድ በሚሠርጽ፣ በነቢያት በተነገረ፣ የሕይወት ጌታና ሰጭ በሆነ፣ በመንፈስ ቅዱስም እናምናለን።

የሁሉም በሆነች፣ በአንዲት ቅድስት የሐዋርያት ቤተ ክርስቲያንም እናምናለን፣ ለኃጢአት ማስተሰርያ በተደረገች፣ በአንዲት ጥምቀትም እናምናለን፤ የሙታንን ትንሣኤና፣ ገና የሚመጣውን ዓለም ሕይወትም፣ እንጠባበቃለን፤ አሜን።