*  ተሹመህ ሩቅ አገር የምትዛወር ቢሆንና፣ ዝውውሩ ከወዳጆችህ እንደሚያቆራርጥህ ብታውቅ፣ ሹመቱን ትቀበላለህ?

*  አገራችን በብዙ ነውጥ ውስጥ ትገኛለች። ያንተ መሞት ብቻ ሰላም የሚያመጣ ቢሆን ለመሞት ፈቃደኛ ነህ?

* ወ/ሮ ደግነሽ ሁለት ህጻናትን ለማብላት፣ ለማልበስና ለማስተማር የሚያነሳሳቸው መሆኑን ብታውቅ፣ ለአንድ ዓመት ፕሪሚር ሊግ ጨዋታዎችን ላለመከታተል ትወስናለህ?

*  ከፍተኛ መስዋእት ከከፈልክ ያንተ እንደሚሆን ብታውቅ፣ የትኛውን ትመርጣለህ? የኢትዮጵያ ጠ/ሚንስትር፣ መስቀል አደባባይ ላይ ሐውልት፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባለቤት?