“ለእውነት እንጂ በእውነት ላይ ምንም ለማድረግ አንችልም” [2ኛ ቆሮ 13፡8]

የወንጌል እውነት እንዲሮጥ ምክንያት ቢሆኑ ይወዳሉ? የወቅቱን ሁኔታ በወንጌል ብርሃን መመርመርስ? ለጌታ ሥራ 30 ደቂቃ ለመስጠት ፈቃደኛ ነዎት? እንግዲያውስ፦

  • ይጸልዩልን = 2 ደቂቃ
  • በዚህ ድረ-ገጽ ላይ የሚለጠፉትን ጽሑፎች በጥሞና ያንብቡ = 7 ደቂቃ
  • እንድንማማር ባነበቡት ላይ አስተያየትዎን ይላኩልን = 3 ደቂቃ
  • ያነበቡትን ባዘጋጀነው ኢ-ሜይል መላኪያ ለወዳጆችዎ ያስተላልፉ = 3 ደቂቃ
  • ይገምገም የሚሉትን መጽሐፍ፣ ወይም ግምገማውን በአድራሻችን ይላኩልን = 7 ደቂቃ
  • ያዘጋጁትን ጽሑፍ ለሌሎች እናዳርስልዎ = 3 ደቂቃ
  • በቤተክርስቲያን ውስጥ ዋነኛ ነው የሚሉትን ጉዳይ ይጠቁሙን = 3 ደቂቃ
  • ደግመው ይጸልዩልን = 2 ደቂቃ
  • በቀን ውስጥ እግዚአብሔር በምሕረቱ እንዲያው የለገስዎ ደቂቃ ብዛት = 1440
  • የሚተርፍዎ ደቂቃ [ለዚያውም ከኖርን] = 1410
  • በዚህ ድረ-ገጽ የሚለጠፉትን ጽሑፎች ለማንበብ የሚያስወጣዎ ወጪ = 0

ቀኒቱንና ሰዓቲቱን አታውቁምና እንግዲህ ንቁ። ወደ ሌላ አገር የሚሄድ ሰው ባሮቹን ጠርቶ ያለውን ገንዘብ እንደ ሰጣቸው እንዲሁ ይሆናልና፤ ለእያንዳንዱ እንደ ዓቅሙ፥ ለአንዱ አምስት መክሊት ለአንዱ ሁለት ለአንዱም አንድ ሰጠና ወደ ሌላ አገር ወዲያው ሄደ። አምስት መክሊትም የተቀበለው ሄዶ ነገደበት ሌላም አምስት አተረፈ፤ እንዲሁም ሁለት የተቀበለው ሌላ ሁለት አተረፈ። አንድ የተቀበለው ግን ሄዶ ምድርን ቈፈረና የጌታውን ገንዘብ ቀበረ። ከብዙ ዘመንም በኋላ የእነዚያ ባሮች ጌታ መጣና ተቆጣጠራቸው። አምስት መክሊት የተቀበለውም ቀረበና ሌላ አምስት መክሊት አስረክቦ። ጌታ ሆይ፥ አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ፥ ሌላ አምስት መክሊት አተረፍሁበት አለ። ጌታውም። መልካም፥ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፥ በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው። ሁለት መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ። ጌታ ሆይ፥ ሁለት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ፥ ሌላ ሁለት መክሊት አተረፍሁበት አለ። ጌታውም። መልካም፥ አንተ በጎ፥ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፥ በብዙ እሾምሃለሁ፥ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው። አንድ መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ። ጌታ ሆይ፥ ካልዘራህባት የምታጭድ ካልበተንህባትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ፤ ፈራሁም ሄጄም መክሊትህን በምድር ቀበርሁት፤ እነሆ፥ መክሊትህ አለህ አለ። ጌታውም መልሶ እንዲህ አለው፦ አንተ ክፉና ሃኬተኛ ባሪያ፥ ካልዘራሁባት እንዳጭድ ካልበተንሁባትም እንድሰበስብ ታውቃለህን? ስለዚህ ገንዘቤን ለለዋጮች አደራ ልትሰጠው በተገባህ ነበር፥ እኔም መጥቼ ያለኝን ከትርፉ ጋር እወስደው ነበር። ስለዚህ መክሊቱን ውሰዱበት አሥር መክሊትም ላለው ስጡት፤ ላለው ሁሉ ይሰጠዋልና ይበዛለትማል፤ ከሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል። የማይጠቅመውንም ባሪያ በውጭ ወዳለው ጨለማ አውጡት፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል … ያ ባሪያ ግን። ጌታዬ እስኪመጣ ይዘገያል ብሎ በልቡ ቢያስብ ሎሌዎችንና ገረዶችንም ይመታ ይበላም ይጠጣም ይሰክርም ዘንድ ቢጀምርስ? [ማቴዎስ 25፡14-30። ሉቃስ 12፡45]