ወ ፍ እ ና ማ ለ ዳ
እንኳንስ ችግኙ፥ ሰዎች የተከሉት
ሥር ይይዝ ነበረ፥ አዕዋፍ የዘሩት።
ዘንድሮ ግን ወፎች፥ እንኳንስ ሊዘሩ
ናፍቆኛል ማለዳ፥ መስማት ሲዘምሩ።
ወፎች ከማለዳ -
በምን ተቃቃሩ?!
ፅልመቱ ሲገፈፍ -
እንዳላበሰሩ፤
ማዜም ተስኗቸዉ -
ተዘግቶ ጀንበሩ
ወደሚነጋበት -
ወዴትስ በረሩ?!
~ አብደላ ዕዝራ
pic credit: pinterest.com