redbug

* ከአንድ በላይ የልብ ወዳጅ ባይኖርህ፤ ወይም ብዙ ጓደኞች ኖሮህ አንድም የልብ ወዳጅ ባይኖርህ የቱን ትመርጣለህ? 

* ፖስታ ወድቆ አግኝተህ ስትከፍተው ውስጡ አንድ መቶ ዶላር አለበት፤ የባለቤቱ መታወቂያና ስልክ ቊጥርም አለበት፣ ግለሰቡ ቻይናዊ ነው፤ ምን ታደርጋለህ? ግለሰቡ ሐበሻ እናት ቢሆኑስ?

* ከእነዚህ ምቾቶች አንዱን ብቻ ምረጥ፦ ለአንድ ዓመት ያለ አሳብ ያለ ገደብ የተመረጠ ምግብ አብስሎ የሚያበላህ(ሽ) ወይም በመኪና የፈለግህበት ቦታ በፈለግህበት ሰዓት የሚያመላልስህ ወይም ሳያሰለች የሚያስቅህ የሚያዝናናህ ብታገኝ።

* ከሞት በኋላ ስለሚሆነው ነገር፣ እስካሁን እውነት ነው ብለህ የሰማኸውና የተቀበልከው ሁሉ ስህተት መሆኑን ብታውቅ ምን ታደርጋለህ?

* የሰማኸውን ወሬ ለሌሎች አጋንነህ ወይ ጨምረህ ታወራለህ? ለምን ይህን እንደምታደርግ አስበህበት ታውቃለህ?

* እንቅልፍህ የሚያስፈራ ቅዠት የሞላበት ቢሆን እና በዓመቱ አንድ መቶ ሺህ ዶላር ሽልማት የሚሰጥህ ቢሆን፣ ፈቃደኛ ነህ?

* ልክ የዛሬ ዓመት፣ ህመም ሳይኖርብህ ድንገት እንደምትሞት ብታውቅ፣ እስከዚያ ምን የአኗኗር ለውጥ ታደርጋለህ?