ጳ   ው   ሎ   ስ  ባ ዲ ሳ ባ

talkshow

ሐዋርያው ጳውሎስ ከ46 እስከ 57 ዓ.ም. በሜዲተራንያ ባሕር አዋሳኝ አገሮች፣ በእስያና በአውሮጳ ተዘዋውሮ ወንጌልን ሰብኮአል፤ ካየውና ካነበበው ተነሥቶ የያኔውን ሕዝብ እንዲህ ገልጿቸው ነበር፦ “[የቤርያ ሰዎች] በተሰሎንቄ ከሚኖሩት ይልቅ ልበ ሰፊዎች ነበሩ ... የቀርጤስ ሰዎች እንደ ገዛ ራሳቸው ነቢይ [ኤፒሜኔዲስ] ዘወትር ውሸተኞች፥ ክፉዎች አራዊት፥ በላተኞች፥ ሥራ ፈቶች ናቸው” ብሎ ነበር። (የሐዋርያት ሥራ 17፡10፣11፤ ቲቶ1፡12)

ጳውሎስ እንደ አሸን የፈላውን ያዲሳባን መጤ ቶክሾው ባሕል ቢያይ፣ አዲስ አበቤዎች “እንደ አቴና ሰዎች ሁሉና በዚያ እንደ ኖሩ እንግዶች፣ አዲስ ነገርን ከመናገርና ከመስማት በቀር በሌላ ጉዳይ አይውሉም ነበር” የሚል ይመስለኛል። (የሐዋርያት ሥራ 17፡21)

ታማኝ ሾው፣ ሰይፉ ሾው፣ ሄለን፣ አርሂቡ፣ ጆሲ ሾው፣ ተፈራ ገዳሙ፣ ዮኒ ሾው፣ ዶ/ር አብርሃም፣ ዶ/ር ምሕረት ሾው፣ ሱለይስታር፣ ሰሎሜ፣ ወይኒ ሱሌይማን፣ ሊያ ሾው፣ ኤርታአሌ፣ ኤልቲቪ፣ ጌራ፣ ኤቫ፣ ኤቫንጀሊካል፣ ጆርዳና ኩሽና ሾው፣ ካሌብ፣ ናሁ፣ ጣይቱ ሾው፣ የኛ፣ ግራና ቀኝ ሾው፣ ጭፈራ ሾው፣ ንትርክ ሾው፣ ሰልፍ ሾው፣ የነቢያት ሾው፣ የዘፈን ሾው፣ የመዝሙር ሾው፣ የዘፈር ሾው፣ የመዝሙን ሾው፣ የፖለቲካ ሾው፣ ኦሮሞ ሾው፣ አማራ፣ ትግሬ ሾው፣ "ኢትዮጵያዊ" ሾው፣ ራዲዮ ሾው፣ ዶክዩ ሾው፣ የምሑራን ሾው፣ የስፖርት፣ ካቦድ ሞ፣ አፒል ፎር ፒዩሪቲ፣ ርዕዮት፣ ኢትዮ ልሳን ሾው፣ ሀረግ፣ ፈታ፣ ፈታ ሀኒ፣ ፍንፍኔ፣ ፋና ቶክሾው፣ 7ኛው ሆቴል ሾው፣ አንድ ዶላር ስታንድ አፕ፣ ስጦታ ሾው፣ ራፋቶኤል፣ አበባ፣ ሃብቴጋ ቶክሾው፣ ቴክቶክሾው፣ ኤሽታኦል፣ አሠር፣ አንፈት፣ አንዋር፣ አውድማ ቶክሾው፣ መስኮት ቶክሾው፣ ሸገር፣ ሳተናው፣ አይጋ፣ ቦርከና፣ ድሬ፣ ናዝሬት፣ ኦኤምኤን፣ አባይ፣ ዲጂታል ወያነ፣ ዛላዎቹ፣ ቀዛሕታ፣ የኛ ሬዲዮ ቶክሾው፣ ዳይስ ጨዋታ፣ ሲህርና መዘዙ፣ ታለንት፣ ሻይ ቡና ሾው፣ ዛሬ ምን አለ ቶክሾው። ይህ ዩቱብ እና ፌስቡክ ሳንጨምር ጥቂቱ ነው!

ቶክሾዎቹን ምን ያመሳስላቸዋል? ሞልቶ ውጭ አገር የፈሰሰው ወጣት፣ ውይይት፣ ፕሮፓጋንዳ፣ ዝና ሽምያ፣ ቂም በቀል፣ የዝግጅት ማነስ፣ ጉራ... ማይሌ፣ ጭፈራ፣ ሹክሹክታ፣ ድግግሞሽ፣ አድናቆት፣ አልሰማህም ስማኝ፣ አለባበስ፣ እውነቱ እኔ ጋ እንጂ ሌላ ጋ የለም፣ የጠያቂ ዲስኲር፣ አስደንጋጭ ዜና፣ ሴት፣ ወንድ ቶሎ ቶሎ ጋዜጠኛ፣ ሥራ አጥ፣ አዲስ ትምህርት፣ አዳዲስ ትምህርት፣ አዳዲስ ታሪክ፣ ቃል ገብቶ መርሣት፣ እውነቱን አለማወቅ፣ እውነቱን አውቆ መበረዝ፣ እውነቱ እንዳይወጣ ማፈን፣ ለጋራ ያልበጀ ለግል እንደማይበጅ አለማወቅ፣ ኦፕራ፣ ዶ/ር ፊል፣ ቲቢኤን፣ ሰቨን ሃንድረድ ክለብ፣ አልጃዚራ፣ ዐረብሳት፣ ናይልሳት፣ ሳት፣ ኢሳት፣ ሲኤን ኤን፣ ቲቢጃሽዋ፣ ዴቪድ ሌተርማን፣ ኮነን ኦብራያን፣ ጂሚ ፋለን፣ ቻርሊ ሮዝ፣ ሳተርዴይ ናይት ላይቭ፣ አሜሪካ፣ አሜሪካ፣ ናይጄርያ፣ እንግሊዝ፣ ፕሪሚር ሊግ፣ ትኲስ ወሬ፣ ሰበር ወሬ፣ ረብሻ ወሬ፣ ሤራ ወሬ፣ የጥንት ወሬ፣ ዛቻ ወሬ፣ በራሪ ወሬ፣ የሚያጓጓ ወሬ፣ ወዘተ።

አዲስ አበቤዎች “እንደ አቴና ሰዎች ሁሉና በዚያ እንደ ኖሩ እንግዶች፣ አዲስ ነገርን ከመናገርና ከመስማት በቀር በሌላ ጉዳይ አይውሉም።” የሚናገር በዝቶ የሚሰማ ጠፍቶአል። አጥርቶ የሚናገር፣ አጣርቶ የሚሰማ አጥሮአል። ሰምቶ የማያጣራ በዝቶአል።

እርስዎስ፣ አዲስ አበቤዎችን እንዴት ይገልጿቸዋል? ራስዎን እንዴት ይገልጻሉ?

ምትኩ አዲሱ

መስከረም 7/2012 ዓ.ም.

ጥቃቅን ናቸው፤ ጥቃቅን አይደሉም