ስሟ አዲስ አበባ ነው

abeba addis

አበባ ኤክስፖርት እናደርጋለን። ልጆቻችን ግን አበባ ማየት አይችሉም። በአፍሪካ በጣም አበባ ኤክስፖርት በማድረግ የሚታወቅ አገር ኢትዮጵያ ነው። ከተማችን ውስጥ ግን አበባ የለም። አበባ በቀላሉ ይበቅላል እንደምታየው፣ ኢትዮጵያ የሚመች መልካም ምድር ነው ያለው፤ አበባን ማየት መልካም ነገር ማየት ለሰብ ኮንሸስ ማይንድ [ለልቦና] ትርጒም አለው። ጥሩ እያየ ያደገ ሰው በዚያ ልክ ጥሩ ያስባል። ጭንቅላት ይመገባል፤ ልክ እኛ ምግብ እንደምንመገበው፣ ጭንቅላትም ከሚያየው ከሚሰማው ይመገባል። መልካም ነገር ያላየ ጭንቅላት መልካም ነገር ሊያወጣ ይቸገራል። እና አበባ ብናደርግ አዲስ አበባን፣ አንደኛ፣ ስሟ አዲስ አበባ ነው። ሁለተኛ፣ በጣም ብዙ ሰዎች እየወጡ የሚገቡባት አገር ናት፤ ኢትዮጵያውያንም ቢሆኑ፣ አንተን ጨምሮ፣ ውጭ ቆይተው ሲመጡ፣ እኔን የሚያጋጥመኝ፤ ኮምፕሌን የሚያደርጉት [የሚያንጎራጒሩት] ይጨልማል፤ ልክ ከቦሌ ጀምሮ ጭልም ያለ ነው አገሩ። ያ ፊሊንግ ያ ኢምፕሬሽን [ያ ስሜት] እንግዳ ሲሆን፣ በማግሥቱ ምንም ብታናግረው ያ ጭለማ ስሜት ከውስጡ አይወጣም። እና አትሊስት [ቢያንስ] ከቦሌ ጀምሮ አበባም ብርሃንም እየታየ ወደ ሸራተን ወደ ሒልተን ቢሄድ ስለ አገራችን ያለው ምልክታ ከፍ ይላል። ሰዎችም ሲመለሱ፣ ወጥተው የሚገቡ ሰዎችም ሲያዩ፣ በአገራቸው ደስ ይላቸዋል። ይኸ ሥራ [ፎቶው ላይ የሚታየው] ከተሠራ በኋላ ወጥቼ ነበር፣ በቅርቡ ውጭ አገር፣ እና ያውም አውሮፓ ነው የሄድኩት፣ ስመለስ የኢትዮጵያ ቫሊዩ [ውድነት] ከፍ ብሎ ታየኝ። እዚያ ባዶ ነበር፣ ቅዝቃዜ ነበር።   ~ ጠ/ሚ ዐቢ አሕመድ

ሰይፉ ፋንታሁን ሾው | ጃንዋሪ 12/2020 | ክፍል 2   ቃለ መጠይቅ