beanstalk

ያ ደ ገ ች  ባ ቄ ላ

የባቄላ ፍሬ ወድቃ ሰውም ወፍም ሳያያት ሥር ሰድዳ ቶሎ አደገች። እንደ ምንም ተንጠራርታ አንድ የቆመ ባላ ተያያዘች። ባላው ላይ ተጠምጥማ ከርማ አናቱ ላይ ወጣችበት። ባላው፣ ወይ ቅብጠት! አለ እንጂ አልገፋትም። ባቄላዋ ቀጥላ ወደ ረጂም ዛፍ ተሸጋገረች። ተሸጋግራ ባላውን ከግርጌ ስታየው፣ ይህ ቅድም ያለፍኩት ባላ አደለም? ታዲያ ምነው አጠረብኝ? አለች። ከዛፉ ጫፍ ላይ ስትደርስ ባላው ጨርሶ አልታያት አለ።

ምሳር ይዘው መጡ። መልምለው ቤት ሊሠሩ ዛፉን ከሥሩ ቆረጡ።

© 2020፣ ምትኩ አዲሱ | “ፋቡላ ከንደገና”