በዛ ፡ ለኔ፡ በዛ

አዝ፦ በዛ ፡ ለኔስ ፡ በዛ ፡ ምህረትህ ፡ በዛ
በዛ ፡ ለኔስ ፡ በዛ ፡ ምህረትህ ፡ በዛ
በዛ ፡ ለኔስ ፡ በዛ ፡ በጐነትህ ፡ በዛ
በዛ ፡ ለኔስ ፡ በዛ ፡ ምህረትህ ፡ በዛ

አፌን ፡ ሞልቼ፡ ተናግሬአለሁ ፡ በማንነትህ ፡ ስለ ተመካሁ
ሁሉ ፡ በሁሉ ፡ የሆነ ፡ አባት ፡ አለኝ ፡ እዩልኝ ፡ ብዬ በድፍረት
ሆነህ ፡ አግኝቼሃለሁ ፡ ከስትንፋሴ ፡ ቀርበህ
ከምልህም ፡ በላይ ፡ ጌታዬ ፡ ልዩ ፡ ነህ

አዝ፦ በዛ ፡ ለኔስ ፡ በዛ ፡ ምህረትህ ፡ በዛ (ምህረትህ፣ ቸርነትህ፣ ቸርነትህ)

ስሜ ፡ ተጽፎ ፡ በሕይወት ፡ መዝገብ
ይህም ሳያንሰኝ ፡ ሰው ፡ በምድር ፡ ስታስብ
መፃተኝ ፡ ሰው ፡ መሆኔን ፡ ሳውቀው
የጌታዬ ፡ ጣት ፡ ጓዳዬን ፡ ሞላው
በስብከት ፡ ሞኝነት ፡ የወደድኩት ፡ ጌታ
በፍቅሩ ፡ ማረከኝ ፡ መጥቶ ፡ በዝግታ
በስብከት ፡ ሞኝነት ፡ የመረጥኩት ፡ ጌታ
የራሱ ፡ አረገኝ ፡ መጥቶ ፡ በዝግታ

አዝ፦ በዛ ፡ ለኔስ ፡ በዛ ፡ ፍቅርህ ፡ እጅግ በዛ (ፍቅርህ፣ ምህረትህ፣ በጎነትህ)

ያለ ፡ ኢየሱስ ፡ ራቊቱን ፡ ቆሞ
ፈውስ ፡ ይላል ፡ ቃላት ፡ ገጣጥሞ
ወግ ፡ ማዕረግ ፡ ረፍት ፡ ፍፁም ፡ እርካታ
በኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ሰላም ፡ እፎይታ
የተገረማችሁ ፡ በሚያስገርም ፡ ጌታ
ደስታችሁን ፡ ግለጹ ፡ በሆታ ፡ በደስታ
የተደነቃችሁ ፡ በሚያስደንቅ ፡ ጌታ
ደስታችሁን ፡ ግለጹ ፡ በሆታ ፡ በዕልልታ

አዝ፦ በዛ ፡ ለኔስ ፡ በዛ ፡ ቸርነትህ ፡ በዛ (ቸርነትህ፣ በጎነትህ፣ ቸርነትህ)

~ ሳሙኤል ፡ ቦርሳሞ [አብሮ ለመዘመር]