ያልደመቁበት ጌጥ?

አጃቢ የሚያጋብስ - ታምር ባይሰራ

እጅን  ባፍ የሚያስጭን - ለመነጋገሪያ

ከወትሮ ወጣ ያለ - ቀልብን የሚከትር

አዲስ የተሰኘ - ምንም ነገር ባይኖር

´ዕዋፍ ምስጋና - የሰማይ ዳመና

የቀኑ መንጋቱ - የማለም ውበቱ

የወዳጅ ፈገግታ - የእስትንፋስ ስጦታ

ጀንበር ዝቅዝቅታዋ - ጨረቃም መውጣቷ

ጤና መለምለሙ - ከሰርክ መታደሙ

የህይወት ዑደቱ 

    የተዘራው ታጭዶ - ዳግም መዘራቱ

ተለምዶ አድርገሽው  ባ´ይንሽ ፊት አይቅለል

ያልተገኘ ለታ

ውሃም ዕንቁ ይሆናል

ውሃም ዕንቁ ያስንቃል!!!

- ሔርሜላ ሰለሞን / 2006