train to harar               

ስ     ደ     ት

በተወለድንበት ባደግንባት አገር
ጭቃ እያቦካን እንጀራ ስንጋግር፤
ባልና ሚስት ሆነን ቤት ከአሸዋ ሠርተን
ሥኒ ከእሽክርክሪት ከጭቃ ጀበና
እንደእናቶቻችን እያፈላን ቡና
የውሸቱን ቡና እውነት አስመስለን።
እትዬ እታፈራሁ እትዬ በለጡ
ቡናው ፈልቷልና ኑና አቦሉን ጠጡ።
እየተባባልን ቡና ቊርስ አቅርበን
በድንጋይ በርጩማ ደርድረን ተቀምጠን
ወሬ እያወራን ዘፈን እየዘፈን
መንደር ተሰብስበን ከጧት እስከ ማታ
እንጫወት ነበርን እቃ እቃ ጨዋታ።
የዛሬው ይመጣል ብለን መቼ አሰብን
ያቺም ርቀት ሆና ካዲሳባ ሐረር
ለቫኬሽን ስንሄድ እንላቀስ ነበር።

ሙሉመቤት ገ/ዮሐንስ
ሕልምና ስኬት፣ ሚያዝያ 2003፣ ገጽ 8

ጭራቆቻችን