farmer

የኛ አገር “politics”

ያገር ልጅ ወንድም ነው
ያገር ልጅ እህት ናት
ባይወለድ ከናት
ባትዛመድ ባባት።
የወዳጅህ ወዳጅ
ለጠላኸው ጠላት
ላረቅኸው አለንጋ
‘ጎሽ’ ላልከው ምርቃት።
ባንድ ልብ አሳቢ
የማር/የ’ሬት ቀፎ
[ስጋህ ነው … ደምህ ነው]
እስኪተክል አጥር
ድንበርህን አልፎ።

ዝ—ም በይ ሐገሬ

ዝ—ም በይ ሐገሬ
ወርቅ ነዉ ዝምታ
ምን ደግ ይወለዳል
ከግደል ተጋደል
[እኔ’ብስ እኛ’ንግስ]
ሽለላ ፉከራ
ቀረርቶ ቀረርታ

~ መታሰቢያ “ሐበሺት” ሰይፉ

© 2020 by Metasebia “Abesheet” Seifu