×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 42
Sunday, 13 November 2011 21:00

እንዳይዛመት፣ እንዳይጋነን። Featured

Rate this item
(0 votes)

ርዕሰ አንቀጽ       

እንዳይዛመት፣ እንዳይጋነን።

 

ሰሞኑን በጂማ አካባቢ የታየው ግጭት ሊያሳስበን ይገባል። የዜና አውታሮች እንደ ዘገቡት ከሆነ ከክርስቲያኑና ከእስላሙ ወገን 15 ሰዎች ሞተዋል፤ የኦርቶዶክስ፣ የወንጌላውያንና የካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት ተቃጥለዋል። ችግሩ እንዳይዛመት ምን እርምጃ ይወሰድ የሚለው ነጥብ ሊያነጋግረን ይገባል።

በመሠረቱ አለመግባባት የሚፈጠረው መተማመን ሲጠፋ ነው። መተማመን ደግሞ የሚኖረው በጋራ ጉዳዮች ላይ ተቀራርቦ በመወያየት ነው። በዚህ ሁሉ ግን የግለሰቦችን ሚና ማስታወስ ይበጃል። ግለሰቦች ከእምነታቸው ጋር ፈጽሞ ባልተያያዘ ምክንያት ሊጣሉና ኋላም ተባባሪ ለማግኘት በሃይማኖት ሊያሳብቡ ይችላሉ። ወይም የሌላውን ልማድ የሚያንቋሽሽና ወደ ጠብ የሚወስድ ቃል ይለወዋጣሉ። ላለመተማመን ምክንያት የሚሆኑ ግለሰቦች የትኛውንም የእምነት ክፍል አይወክሉም፤ እንደሚወክሉም ተደርጐ መታሰብ የለበትም።

አንዳንዴም ለአካባቢው እንግዳ የሆነና የሚከፋፍል ዓላማ ያላቸው ኃይላት አለመግባባትን ይፈጥራሉ፤ ያባብሳሉ። የመንግሥት ድርሻ ባፋጣኝ ጠቡን ማስቆምና ማረጋጋት ሲሆን፣ ተቀራርቦ ጉዳዩን ማጣራትና ችግሩ እንዳይደገም መፍትሔ መሻት በቅድሚያ የሃይማኖት መሪዎች ኃላፊነት ነው።

አሁን የተከሰተው ጉዳይ ተጣርቶ ሕጋዊ እርምጃ ሲወሰድ የሃይማኖት ክፍሉን ሳይሆን የሚመለከተው በረብሻው ተባባሪ ሆነው የተገኙትን ሰዎች ብቻ ይሆናል።

በተጨማሪ ዜናውን ከማጋነን መቆጠብ ያስፈልጋል። ይህን የመሰለ ጥፋት በየወቅቱ መከሠቱ አልቀረም። ለአሁኑ ችግሩ የታየው በተወሰኑ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ከተሞች ነው። በመላ ኢትዮጵያ የሃይማኖት ግጭት እንደ ተቀጣጠለ ወይም በክርስቲያኑና በእስላሙ መካከል እልቂት እንደሆነ ተደርጐ ሊታሰብ ወይም ሊነገር አይገባም። የተሳሳተ አስተሳሰብ ለተሳሳተ ድርጊት ሁኔታን ያመቻቻልና። ይልቅ ለአገራችን ልማት በጐ ምኞት ያላቸው ሁሉ መጸለይና መግባባት እንዲገኝ መጣር ይጠበቅባቸዋል።

10/18/2005

Read 823143 times Last modified on Sunday, 13 November 2011 21:13

More in this category: ያለ ዕውቀት መቅናት »

308971 comments

  • Comment Link Web Sunday, 07 December 2025 23:46 posted by Web

    You break things down so clearly!

  • Comment Link Web Sunday, 07 December 2025 23:42 posted by Web

    Sharp points, great delivery.

  • Comment Link Web Sunday, 07 December 2025 23:40 posted by Web

    You express ideas beautifully.

  • Comment Link Web Sunday, 07 December 2025 23:38 posted by Web

    Impressive insight here!

  • Comment Link Web Sunday, 07 December 2025 23:35 posted by Web

    Superb structure and clarity.

  • Comment Link Web Sunday, 07 December 2025 23:34 posted by Web

    Strong writing with strong ideas.

  • Comment Link Web Sunday, 07 December 2025 23:33 posted by Web

    You explained everything so well.

  • Comment Link Web Sunday, 07 December 2025 23:31 posted by Web

    Truly enjoyed this content!

  • Comment Link Web Sunday, 07 December 2025 23:29 posted by Web

    Informative and engaging — nice!

  • Comment Link Web Sunday, 07 December 2025 23:27 posted by Web

    Impressive insight here!

Leave a comment

Make sure you enter all the required information, indicated by an asterisk (*). HTML code is not allowed.