×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 42
Sunday, 13 November 2011 21:07

ፖለቲካና ሃይማኖት ይቀላቀላሉ Featured

Rate this item
(1 Vote)

ርዕሰአንቀጽ - ልዩ እትም

ፖለቲካና ሃይማኖት ይቀላቀላሉ

ሃይማኖትና ፖለቲካ አይቀላቀሉም ይባላል እንጂ ተነጣጥለው አያውቁም። ሰው ማህበራዊ ፍጡር ነው፤ ፖለቲካም በጋርዮሽ  የሚከናወን የሥልጣን ግንኙነትና አደረጃጀት ነው። ሰው ሃይማኖተኛም ነው፤ ራሱን ወይም ከእርሱ ውጭ ያለን ያመልካል፤ አምላክ የለም በማለቱ አምላኪነቱን ያውጃል። ለነፍሱ ያደረ ፈጣሪውን ያመልካል፤ ለአብዮት ያደረ አብዮት ያመልካል፤ ለሥጋው ያደረ ሥጋና ዓለምን ያመልካል።

ከዕለታት አንድ ቀን በአፄ ኃይለሥላሴ ዘመን ሃይማኖትና መንግሥት ተደጋግፈው በሰላም ይኖሩ ነበር። “ሃይማኖት የግል፣ አገር የጋራ ነው” መርሕ ነበር። በደርግ ዘመን ሃይማኖት ተወገዘ፤ እግዚአብሔር በአዋጅ ታገደ። የምሥራቃውያን ዐመል ብቅ አለ። ወደ ምሥራቅ ተዞረ። መንግሥት ካዘዘልህ ውጭ ወዮልህ መጣ። “እግዚአብሔር ይመስገን” ተከለከለ።

እንደምን አደርክ?

ደህና፣

ቤተሰብ እንዴት ነው?

ደህና፣

ሥራ እንዴት ነው?

ደህና።

አንድ ፈረንሣይ ለጋሲዮን የሚኖሩ ወይዘሮ፣ “እግዚአብሔር ይመስገን” ማለት ስላበዙ፣ ካድሬው በልግጫ፣ “ሴትዮ፣ እግዚአብሔር የሚባል የለም፤ ምን እግዚአብሔር እግዚአብሔር ትያለሽ?” ቢላቸው፣ የማይበገሩ ሴትዮ፣ “ከቤቴ ስወጣ አነጋግሬው የመጣሁትን እንዴት የለም ትለኛለህ?” ብለው አፍ አስይዘዋል።

በሶቭየት መጤ ሃይማኖት አገር ተወረረች። ደም ፈሰሰ፣ መንግሥትና ሃይማኖት ተፋቱ ተባለ። ለፖለቲካ ስላላመቸ ቆይቶ “ሃይማኖት አይለያየንም” መጣ። ወሬው “እኩልነት” “ነፃነት” ሆነ። የመስቀል አደባባይ ፕሮቶኮሉ ተቀየረ፤ ከሊቀመንበሩ በስተቀኝ የቤተክህነት መሪ፣ በስተግራ የመስጊዱ ተሰየሙ። የግል የሚባል ለጊዜው ከሠረ። “ሃይማኖት ለፖለቲካ፣ ፖለቲካ ለሃይማኖት” የሚል ስልት ተቀየሰ። “የየሱስ ቃል አያረጅም” የምትለዋ የስዩም ገብረየስ ዝማሬ በአብዮት ሐዋርያት ተጠልፋ የወቅቱን ረብሻ በጉያዋ ደብቃ ብቅ አለች።

በ1983 ዲሞክራሲ የሚሉት ከምዕራቡ ዓለም ከገንዘብ እርዳታ ጋር ተላከልን። እኛም የምዕራባውያንን ዐመል ተቀበልን። ዲሞክራሲም ግለኛነትን እያገነነ “እኔ እኔ፣ ለኔ ለኔ” እያለ ቁና እየተነፈሰ ደረሰ። ወደ ምዕራብ ተዞረ! “ሃይማኖት የግል ነው” በየግልህ ተባለ። በየቀዬህ በየክልልህ ዛፍ ቢሆን ጥላህን ማምለክ መብትህ ነው ተባለ። የእኩልነትና የነፃነት መጽሐፍ ተደገመ።

በአፄ ኃይለሥላሴና በደርግ፣ እንደ ዘመነ ዲሞክራሲ መምረጥና መመረጥ አልነበረም። ሥልጣን፦ መስሎ ላደረ ሹመት፣ ለተዳፈረና ላቅማማ ሽረት ግዞትና ሞት ነበረ። በቀድሞው ልክ ባይሆንም ዛሬም ይኸ አልጠፋም። አሁን ግን ዲሞክራሲ ተብሏልና መምረጥና መመረጥ የሚለው አሠራር ገበያ ላይ ወጥቶ ፀሐይ እየሞቀ ነው። እዚህ ላይ ነው እንግዲህ ልዩነቱ። ሰው ያለ ተጽዕኖ መምረጥ ከቻለ ስብዕናው ተከበረ፣ ሕልውናው ተዘከረ ማለት ነው። መሪነት ብቃት ላላቸው ሁሉ እንጂ ለጥቂቶች የተሰጠ መብት አይሆንም። ወይም መሪዎች እንድ ግብጽ አማልክት ለዘላለም ተሰይመው ሕዝብ የሚያንቀጠቅጡበት አይሆንም፤ ስለ ታታሪነታቸው፣ የሕዝብ አገልጋይና አደራ ተሸካሚ ስለ መሆናቸው ተጠይቀው ግልጽ መልስ የሚሰጡበት፣ የሚመረጡበት ወይም የሚሻሩበት ሁኔታ የተፈጠረበት ዘመን ነው። ሃይማኖተኞችን በምጸት፦ እዚህ ምን ታደርጋላችሁ? ሄዳችሁ ብትጸልዩ አይሻልም? ሲሉ የነበረ እንዲመረጡ ደጅ ጥናት ከጀመሩ ሰነበተ። ተረስቶ የኖረ ሕዝብ በተፈላጊነቱ ሲኩራራና ሲሽኮረመም ማየት ተስፋ ሰጭ ነው። ቅንጅት በ1997 ምርጫ ዋዜማ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲጸልይ ማሳሰቡ ሃይማኖተኞችን ማግባባቱ ነበር። የቀድሞው የደርግ መሪ በቀውጢ ሰዓት ክርስቲያኑና እስላሙ በየቤተ አምልኮው አምላኩን እንዲማጸን መማጸናቸው አይረሳንም። የደረሰባቸው ጭንቅ ቀድሞ የተናገሩትን ሁሉ አስረስቶአቸው። ለሶሻሊስት ጓዶቻቸው ግን ይህን የነገሩ አይመስለንም፤ ምክንያቱም ቅድም እንዳመለከትነው እግዚአብሔር ስለሌለ ለማን ይጸልዩ? [እርግጥ ጓዶቹ በየጓዳቸው ጸልየው እንደ ሆነ ማወቅ አንችልም፤ ይህንን የሚያውቅ እግዚአብሔር ብቻ ነው]።

የትላንቱ ፖለቲከኛ ሞት ሳይጠራ [“እናት አገር ወይም ሞት!”] ወይም ሰማይና ምድርን ሳይራገም [ይውደም! ይውደም!] ንግግሩን አይቆርጥም። የዛሬ ዘመን ፖለቲከኛ ግን ዋዛ አይደለም። በየንግግሩ መሃል የእግዚአብሔርን ስም ጣልቃ እያስገባ [ሲመችም ለሙስና እየሰገደ] ያሳርጋል። ከአሜሪካ ፖለቲከኞች ቀድቶ ይሆን? እየቆየ እየቆየ የሚገርም ነገር አይጠፋም። እግዚአብሔርም ተቸገረ እኮ! የሶቭየት ሃይማኖት አገራችን ሲገባ “እግዚአብሔር የለም፣ አገር ለቆ ሄዷል” እንዳልተባልን፤ መንግሥታት ሲንኮታኮቱ ከወደ አሜሪካ ብቅ ብሎ ይሆን? የኛዎቹስ አሥሬ እግዚአብሔርን የሚጣሩ በአዲስ አበባና በዋነኛ ከተሞች የሞላውን የወንጌል አማንያንን ድምጽ ለማግኘት አለማቀዳቸውን ማስተባበል አይቻልም። በአንጻሩ ሃይማኖት ማጥላሊያና ተቀናቃኙን ለማጣጣያ ፍቱን መሣሪያ ሆኗል። ደግማ እሥር ቤት የወረደችው ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ አንድ ሰሞን “ጴንጤ” ነች መባሉ ለሙገሳ ወይም ስለርሷ ሐቁን ለመናገር ሳይሆን ለማዋረድ እንደ ነበር የሚያጠያይቅ አይደለም። ምክንያቱም “ሃይማኖት የግል ነው” ሲባል የሰማነው ድሮውንም ከልብ አልነበረማ።

ከዓመት በፊት የተፈቱት የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር የአቶ ታምራት ላይኔ ጉዳይ ሌላኛው ነው። በሙስና ተከሰው ከ 12 ዓመት እሥራት በኋላ በአመክሮ ሲፈቱ በአደባባይ “ፖለቲካ በቃኝ፣ ከእንግዲህ ኢየሱስን አገለግላለሁ” ማለታቸው ብዙ ጥያቄና ወረፋ አድርሶባቸዋል። [“ሙስና”፣ ጥንት “ጉቦ” የምንላት ነች፣ ዛሬ ቀጭን ነጠላ ደርባ ብቅ አለች። ደርግ “መንፈስ” ሲል ረቂቅ ቁሳዊነትን ለመግለጽ እንጂ ከቁስ ውጭ እውነት አለ ማለቱ እንዳልነበረ ሁሉ።] ታዲያ አቶ ታምራት ፖለቲካ በቃኝ ማለታቸው ምናኔም እንደማያስጥላቸው የዘነጉ አይመስለንም። “አለም አቀፍ ፈውስ በፍቅርና በአንድነት” ብለው የጀመሩት “ሚኒስትሪ” ሌላው ቢቀር የፖለቲካ ሂደቶችን ማጤንና ከፖለቲካ መሪዎች ጋር መግባባትን እንደሚጠይቅ አይታጣቸውም። በየሄዱበት “የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር” መባላቸው የፖለቲካ ጠባሳ እንደተወ የማይገነዘቡ አይመስለንም። እሰብካለሁ ያሉት ወንጌል፣ ሥር ነቀል ለውጥ የሚያስከትል በመሆኑ ምናልባት ዳግም “ሙስና” ውስጥ አልገኝም፣ ከሚያባልግ ሥልጣን እቆጠባለሁ ማለታቸው ይሆናል። ወይም ክርስቶስ ይቅር ብሎኛል እኔም እንደ ዘኬዎስ ማህበራዊ በደሌን አስተካክላለሁ፣ አካክሳለሁ ማለታቸው ይሆናል [ሉቃስ19፡1-10]። ክርስቶስን ሳያውቁ የኖሩትን  ሕይወት ባዶነት ከተረዱስ፣ ኢየሱስ ሕያውና እውነተኛ ጌታ እንደ ሆነ ካመኑ፣ ያለፉበትን የትግልና የሥልጣን ዘመን ከቀመሱት አዲስ ሕይወት አንጻር እውነቱን በመጽሐፍ የማስፈር ብሔራዊ፣ ሰብአዊና የታሪክ ግዴታ እንዳለባቸው እናሳስባለን። ለማንኛውም አንድ ጸሐፊ ወደ ክርስቶስ ማህበር መቀላቀላቸውን አስመልክቶ “ፖለቲከኛ ሲያረጅ፣ ሰባኪ ይሆናል” ብሎ  በከረመ ቁጣና በጥርጣሬ ተችቶአቸዋል። እግዚአብሔርን ማሰብ በስተርጅና ወደ ሞት መቃረቢያ ላይ ነው ማለቱ ይሆን? ምስክርነታቸውን ልብ ብሎ ለሰማ ግን ወንድም ታምራት እውነተኛ የሕይወት ለውጥ እንዳገኙ አያጠራጥርም። የቀረውን ጊዜ ይገልጠዋል። የጠቀስነው ጸሐፊ የክርስቶስን ወንጌል ኃይልና ምሥጢር ካለማወቅ የተነሳ እዚህ ድምዳሜ ላይ ደርሶ ይሆናል ብለን አልፈነዋል።

በሚያዝያ ወር ላይ ከላሊበላ ወሎ ተመራጭ የሆኑት ፖለቲከኛ አቶ ልደቱ አያሌው “ጴንጤ” ሆኑ ተብሎ አገር ታመሰ። “ብሮስታንት” ወይም “ጴንጤ” ሆኑ ብለው ያሟቸው ምን ማለታቸው እንደ ሆነ አላብራሩም። ይኸ “ብሮስታንትና ጴንጤ” በደፈናው መኾን የሌለበት፣ እንደ ለምጥ የሚሸሽ ነገር ይመስላል። “ጴንጤ” ሲፈለግ ማስፈራርያ ሲፈለግም ማግባብያ ነው። አቶ ልደቱን፦ “ጴንጤ ነዎት ይባላል፣ ጴንጤ ነዎት?” ሳይሆን “በኢየሱስ ክርስቶስ ያምናሉ?” ማለት ልኩ ነበር። ለማለት አልን እንጂ ስለ ልኩ የሚገደው ማን ነው? እርሳቸውም ሲመልሱ፣ ስሜን ለማጥፋት ባላንጣ የነዛብኝ እንጂ እኔስ “ጴንጤ” አይደለሁም፣ ሃይማኖቴን አልለወጥኩም እያሉ ነው። ቀድሞውኑ የያዙት ክርስቶስን ከሆነ ሃይማኖታቸውን አጸኑ እንጂ አልለወጡም። ታሪክ ራሱን ይደግማል። አፄ ኃይለሥላሴም እንደዚሁ የወሎውን ልጅ ኢያሱን ሰለሙ ብለው በቤተክህነት ትብብር ሕዝብ እንዳስነሱባቸው ታሪክ ነግሮናል። መቸ ይሆን የሃይማኖት መሪዎች ለኑሮአቸውና ለሥልጣን ሲሉ ከምድራዊ ሥልጣናት ጋር መመሳጠር የሚያቆሙ? የፖለቲካ መሪዎችስ መቸ ይሆን ሳይጦሙ ጦም ማወጅ የሚያቆሙ?

ለመሆኑ፣ ሃይማኖትና ፖለቲካ አይቀላቀሉም የሚለው አስተሳሰብ ከወዴት መጣ? በመጀመሪያ ፖለቲካ ምን እንደ ሆነ ካለማወቅ ነው። ወይም በተሳሳተ መንገድ ከመረዳት ነው። ፖለቲካ መጥፎ፣ ቅጥፈት የሞላበት ጉዳይ ነው ከማለት፤ [ይህም በአንድ መልኩ ትክክል ነው።] ለነፍሱ ያደረና ወንጌል ያነበበ ሰው ከእንደዚህ ዓይነት ምግባር መራቅ  ይኖርበታል ከማለት። ፓለቲካ ግን ከላይ እንደ ጠቀስነው በቅድመ አሳቡ የመንግሥት ሥርዓትና አስተዳደር ነው፤ በክፉዎች እጅ ለክፉ፣ በቅኖች እጅ ለበጎ ሊውል ይችላል። ቀጥሎ፣ የሃይማኖትን ምንነት ካለመረዳት ነው። ሃይማኖት ሲባል ለሰማይ መንግሥት መዘጋጃ ሥጋን ለማጎሳቆያ እንጂ የምድሩን ለመመርመሪያና ታግሎ ኑሮን ለማሸነፊያ እንዳልሆነ ይታሰባል። ይኸ ነው አብዮተኛውን ትውልድ ዙሪያ ገባውን የነገሠውን ድህነት፣ ድንቁርናና የፍትሕ መጓደል አይቶ ሃይማኖትን ለመጥላትና ቤተክርስቲያንን ለማሳደድ ያነሳሳው። እንግዲህ ፖለቲካዬን የሚል ፖለቲካው ውስጥ ይገባል፤ ሃይማኖቴን የሚል ደግሞ እንደየሃይማኖቱ ይሆናል ማለት ይመስላል። ሃይማኖተኛ ትርፍ ሲያይ ፖለቲካውን ይያያዘዋል። ፖለቲከኛም ሲከስር ወይም መከራ ሲበዛበት ሃይማኖተኛ ይሆናል። በዚህ ስሌት ሁለቱ እንደ ዘይትና ውሃ ናቸው፣ አይቀላቀሉም፤ ፖለቲካም እንደ ኮሬንቲ ነው፣ አይቀረብም።

ወንጌል ግን ምን ይላል? ላመኑ “የምድር ጨው ናችሁ” ይላቸዋል። ማህበረሰብ የሞራል ቅንቅን ቦርቡሮ እንዳያፈርሰው ተሳትፎአችሁ አስፈላጊ ነው ይላል። “የዓለም ብርሃን ናችሁ” ይላል። ዓለም ጨለማ ነች፤ እውነትን ከሐሰት መለየት እንዳይጠፋ ብርሃን የሆነውን፣ ጻድቅ ፈራጅ የሆነውን፣ የሰላም አለቃ የሆነውን ኢየሱስን ለማወጅ ታስፈልጋላችሁ። ፈርሃ እግዚአብሔር ሠርጾ እንዲወጣ ምልክት ናችሁ ይላል። ለመሪዎች ጸልዩ፣ ፍትሕ እንዳያጓድሉ፤ በአምላክ አምሳል የተፈጠረውን እንዳይንቁ እንዳያጠቁ፣ ምድርን እንዳያራቁቱ፣ ራሳቸውን እንዳያተልቁ። “ክንዳችን ይህን ሠራችልን” እንዳይሉ።

         

ግንቦት 15/2002 የሕዝብ ምርጫ ይደረጋል። ክርስቲያኖችም እንደ ተቀረው ሕዝብ ብሔራዊ ግዳጃቸውን ሊወጡ፣ መብታቸውን ሊያስከብሩ ድምጽ በመስጠትና በመቀበል በምርጫው ይሳተፋሉ። ከዚህ አንጻር ሃይማኖትና ፖለቲካ አይቀላቀሉም የሚለው አባባል የተሳሳተ ብቻ ሳይሆን ጎጂ ነው። ግብር መክፈል ፖለቲካ ነው። በጎ አድራጎት ፖለቲካ ነው። መገኘት ራሱ ፖለቲካ ነው። “ኢየሱስ በሁሉም ላይ ጌታ ነው” ማለት ከፖለቲካም ዋና ፖለቲካ ነው። ከዳር የቆምን በመሰሉን ዘመናት ሁሉ የፖለቲካው ተካፋይ እንደ ነበርን መካድ አንችልም። መፈክሩ፣ “ከሁሉም በላይ አብዮቱ” ሲለን፣ የለም ምን ተደርጎ፣

“ኢየሱስ ነው ከሁሉም በላይ

ጌታችን ነው ከሁሉም በላይ

አቻ የሌለው

በምድር በሰማይ”

ያልናቸው ጊዜአት ዛሬም አልተለወጡም። ይኸ በነፍሳችን ተወራርደን የምንኖረው ኑሮ ነው። ሃይማኖትና ፖለቲካ አይነጣጠሉም ስንል ግን ከመንግሥት አስተዳደር አንጻር አባባሉን ልናርም ይገባል። የአንድ አገር ሕዝቦች እምነታቸው አንድ ወጥ ስላይደለ፣ ቅድም እንደጠቀስነው ሰው ክቡርነቱ በጅምላ ሳይሆን በግል በፈጣሪው አምሳል መፈጠሩ ስለሆነ፣ የሃይማኖትና የመንግሥት አደረጃጀትና ተልዕኮ ሊነጣጠሉ ያስፈልጋል። ቤተክርስቲያን ኃይሏና ሥልጣኗ ለግራና ለቀኝ የማይለውን ለነፍስና ለሥጋ ለውጥና ተስፋ የሚያመጣውን ወንጌል ስትሰብክ ነው። የዜጎች እምነት የተለያየ ስለሚሆን የዜግነት መብታቸው ሊጣስ አይገባም። ይህን እንጂ ያንን አምኖ ላለመከተል ነፃነት ሊኖር ይገባል። ሃይማኖቱን በግፊት ሳይሆን በአክብሮት የመለፈፍ መብቱ ሊከበርለት ይገባል። ሃይማኖትና መንግሥት አይደራረሱ ማለት አይቻልም። ሳውዲ በሕግ የእስላም አገር ናት፣ ክርስቲያን መሆን በልምድ እንዳየነው እንደ መብት አይቆጠርም፤ ብዙ አሣር ያስከትላል። ዛምቢያ በሕገ መንግሥት የክርስቲያን አገር ናት፤ እስላም መሆን ግን ለእስር አይዳርግም፤ ዜግነትን አያስነጥቅም። የተቀሩት አገሮች ይህንኑ በተለያየ መልኩ ተግባራዊ እያደረጉ ይገኛሉ። ባጭሩ፣ ሙስሊሞች በክርስቲያን አገር ያላቸውን ነጻነት፣ ክርስቲያኖች በሙስሊም አገር አይኖራቸውም።

እፊታችን ባለው ምርጫ ላይ ለመሳተፍ ምን ጠቃሚ ክርስቲያናዊ መመዘኛዎች ሊኖሩ ይችላሉ? እንግዲህ ዝርዝሩ ላይ አቋማችን ሊለያይ ቢችልም፣ መሠረታዊው ላይ አንድ ነው። መሠረታዊው ምንድነው? የመጀመሪያው፣ የሥልጣን ሁሉ ምንጭና ባለቤት እግዚአብሔር ነው። ቢገነዘቡ ባይገነዘቡ ሥልጣን ላይ ያሉ ሁሉ ሥልጣናቸው በአደራ የተሰጣቸው ነው። መሪዎች የሚሾሙት ጽድቅና ፍትሕን ለማስፈን ነው። በምድሪቱ ሰላም ቢሆን ከእግዚአብሔር ነው፣ የአማንያን ጸሎትና ተሳትፎ ፍሬ ነው። ስደትና መከራ ቢመጣ እግዚአብሔር ለዓላማ ፈቅዶ ነው። ሁሉን የሠራ እግዚአብሔር ነው፤ እግዚአብሔር በሠራው ሰው ሊመሰገን አይገባም። ወንጌልን ያመኑ በሞት ሆነ በሕይወት ከእግዚአብሔር ሌላ ተጨማሪ ምክንያት አያሻቸውም።[ፊል1፡20] አለዚያ በሰላሙ ሰዓት ሰውን ማመስገን፣ በስደት ደግሞ እግዚአብሔርን ማማረር ሊመጣ ነው። ሁለተኛው፣ ሰው ሁሉ በእግዚአብሔር አምሳል ተፈጥሯል የሚል ነው። [1ኛቆሮ11፡7፤ዘፍ1፡27] ሰው ከዝንጀሮ መጣ ወይም ክብሩና ህልውናው የተቃረኑ ማህበራዊ ኃይላት ውጤት ነው የሚል ሁሉ የሳተ ነው። ወይም አንዱን ሰው ወይም ጎሣ ከሌላው ሰው ወይም ጎሣ የሚያበላልጥና የሚያቃቅር አስተሳሰብ ሁሉ የወንጌልን ሥልጣን የሚጻረር ነው። ሦስተኛው ከሁለተኛው የሚቀጥል ነው፤ ይኸውም፣ ሰው በአምላክ አምሳል ተፈጥሯል ካልን፣ የደሆች [የሥራ አጦች፣ የአዛውንት፣ የመንገድ ተዳዳሪ ሕጻናትና ሴቶች] ሁኔታ ምን ይመስላል? መሪዎች የገቡትን ቃል ያጥፋሉ ወይስ ይፈጽማሉ? ሕግ ለሁሉም እኩል ይሠራል? ሰብአዊ መብት [የመደራጀት፣ የመናገርና የመጻፍ] ይከበራል? ክፉ የሚያደርጉ ተመስግነው መልካም የሚያደርጉ ይገፋሉ? በዚህ ሁሉ ቤተ/ክ ምዕመኑን በጽድቅ ወንጌል ማስታጠቅ ትታ ከምድራዊና ጊዜአዊ ድርጅቶችና አስተሳሰቦች ጋር መወዳጀትና መወገን ብትጀምር ሥልጣኗን ትጥላለች፤ ያም ለክርስቶስ ክብር አይሆንም። ጸጋ፣ ችሎታና ጥሪ ያላቸው አማንያን ደግሞ ተመርጠው በፖለቲካም መሳተፍ ይችላሉ።

ከሁሉ በላይ ግን መጸለይ ነው፤ ሰላም እንዲኖር፣ አመጸኞች እንዲገቱ፣ እንዳያይሉ፣ የሰላም ሰዎች፣ ቅን ዜጎች፣ ፍትሕ የሚወዱ እንዲነሱ። ባለጠጎች ደሃውን መኖሪያ እንዳያሳጡት። የተሰጠን የክርስቶስ መንፈስ ስለሆነ እርሱ ወደ እውነት ሁሉ ይመራናል። ሰው የማያየውን ያያል፤ ፖለቲካ የማይመረምረውን ይመረምራል። የእግዚአብሔር መንፈስ ሰው እንደሚያይ አያይም። ሥልጣናትና ኃይላት በስውር የሚመክሩትን ይሰማል፣ ለባሪያዎቹ ያስታውቃል። ቅንነት የተገኘበትን ይገነዘባል፤ መነሻን ብቻ ሳይሆን ፍጻሜን ያያል። ከስምንቱ የእሴይ ልጆች በነቢዩ ሳሙኤል የተመረጠው በሥፍራው ላይ ያልነበረው ትንሹ ዳዊት ነው። እግዚአብሔር እንደ ቂሮስ ያሉትን አሕዛብ ፈቃዱን እንዲፈጽሙ ያስነሳል። ይህን ያነሳል፤ ያንን ይጥላል። ዕጣ በጉያ ይጣላል፣ መደብዋ ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው። ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር የእግዚአብሔርና የመሲሑ ነው። እግዚአብሔር ምድራችንን ርህራሄ፣ ቅንነትና ማስተዋል ባላቸው ሰዎች ይባርክልን። [ጥቅሶች፦ ሮሜ 13፡1-5፤ የሐዋ ሥራ 5፡29፤ ራእይ 13፤ 1ኛጴጥሮስ 2፡13-17፤ ማርቆስ 12፡13-17፤ ቲቶ3፡1፤ ምሳሌ16፡33፤ 1ኛሳሙኤል16፤ 2ኛነገሥት 6፡8-13፤ 2ኛ ዜና 36፡22፤ ዕዝራ1፡2፤ ኢሳይያስ 6፡1-]               5/13/2010

 

Read 147074 times

37832 comments

  • Comment Link https://www.cakeresume.com/me/seedfriday17/ Friday, 04 February 2022 15:25 posted by https://www.cakeresume.com/me/seedfriday17/

    This paragraph will help the internet people for creating new website or even a weblog from start to end.

  • Comment Link https://postheaven.net/seedtank00/minecraft-server-software-ideas Friday, 04 February 2022 15:20 posted by https://postheaven.net/seedtank00/minecraft-server-software-ideas

    hi!,I love your writing so much! percentage we keep
    in touch more approximately your post on AOL?
    I require an expert on this house to solve my problem.
    Maybe that's you! Taking a look ahead to see you.

  • Comment Link https://spinalhub.win/wiki/Six_Simple_Steps_To_An_efficient_Minecraft_Launcher_Technique Friday, 04 February 2022 15:20 posted by https://spinalhub.win/wiki/Six_Simple_Steps_To_An_efficient_Minecraft_Launcher_Technique

    Aw, this was a really nice post. Spending some time and actual effort to generate a really good article… but what can I say… I hesitate a lot and don't seem to
    get anything done.

  • Comment Link cope4u.org Friday, 04 February 2022 15:18 posted by cope4u.org

    Great beat ! I would like to apprentice while you amend your site, how could i subscribe for a weblog site?
    The account aided me a acceptable deal. I have been a little
    bit familiar of this your broadcast provided brilliant clear idea

  • Comment Link https://championsleage.review/wiki/Minecraft_Servers_Concepts Friday, 04 February 2022 15:16 posted by https://championsleage.review/wiki/Minecraft_Servers_Concepts

    Thanks on your marvelous posting! I truly enjoyed reading it, you happen to be a great author.I
    will remember to bookmark your blog and definitely will come back someday.

    I want to encourage you to definitely continue your great job, have a nice holiday weekend!

  • Comment Link migadikos.gr Friday, 04 February 2022 15:15 posted by migadikos.gr

    I constantly spent my half an hour to read this blog's articles everyday along with a cup of coffee.

  • Comment Link http://brewwiki.win/wiki/Post:Vital_Pieces_Of_Minecraft_Jar Friday, 04 February 2022 15:15 posted by http://brewwiki.win/wiki/Post:Vital_Pieces_Of_Minecraft_Jar

    Unquestionably believe that which you said. Your favourite reason seemed to be on the web the simplest factor to be aware of.
    I say to you, I definitely get annoyed while other people consider
    worries that they just don't recognize about.
    You managed to hit the nail upon the highest as smartly as defined out the entire thing with no need side-effects ,
    other people can take a signal. Will probably be again to get more.
    Thanks

  • Comment Link www.fcc.gov Friday, 04 February 2022 15:15 posted by www.fcc.gov

    This excellent website truly has all of the info I needed about this subject and didn't know who to ask.

  • Comment Link rojakmarket.com Friday, 04 February 2022 15:12 posted by rojakmarket.com

    Good day! I could have sworn I've visited your blog
    before but after browsing through a few of the articles
    I realized it's new to me. Nonetheless, I'm definitely delighted
    I stumbled upon it and I'll be bookmarking it and checking back often!

  • Comment Link rojakmarket.com Friday, 04 February 2022 15:12 posted by rojakmarket.com

    Good day! I could have sworn I've visited your blog
    before but after browsing through a few of the articles
    I realized it's new to me. Nonetheless, I'm definitely delighted
    I stumbled upon it and I'll be bookmarking it and checking back often!

Leave a comment

Make sure you enter all the required information, indicated by an asterisk (*). HTML code is not allowed.