×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 42
Sunday, 13 November 2011 21:18

ሌላው መንገድ Featured

Rate this item
(1 Vote)

ግምገማ ድርሰት

ሌላው መንገድ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሃይማኖትና የፖለቲካ መሪዎቻችን ከተለምዶ ውጭ የሕይወት ታሪካቸውን በመጽሐፍ አሳትመው እያሠራጩ ነው። ይህ አዲስ ክስተት ነው፤ የሚደገፍ ነው። ማን እንደሆኑ፣ ምን እንደሠሩ አስረግጠን ሳናውቅና በሠሩት ሥራ ዙሪያ ሳንወያይ ያለፉ የሕዝብ መሪዎች ጥቂቶች አይደሉምና ተዘርፈናል፣ ቅርስ ባክኖብናል። የአገራችንን ታሪካዊ ወቅቶች በግለሰቦቹ እይታ አስታከን ማገናዘብ ብሔራዊ መብታችን ብቻ ሳይሆን፣ የተመሠረተውን በጎ ከመርሳት የተነሳ ስሕተቶች እንዳይደገሙ፣ ፍርሃትና አሉባልታ እንዳይገዙን ለመከላከል ጭምር ይጠቅማል። በዚህ አጋጣሚ የጄኔራል ታዬ ጥላሁን የሕይወት ታሪክ እስካሁን አለመጻፉ ያሳስበናል። በዚሁ ድረ ገጽ፣ ከእስር ተፈተው ወደ ክርስቶስ አማንያን ማሕበር ተቀላቅያለሁ ያሉት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ታምራት ላይኔ፣ አሁን የእውነትን መንገድ ለይተው አውቀዋልና ሁሉን ግልጽ አድርገው በመጽሐፍ እንዲያሠፍሩ ማሳሰባችን ይታወሳል። ሌሎች፣ በተለይ ሴቶች ካሉ እንደዚሁ።

የዛሬው ትኩረታችን፣ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ፣ ባለፈው ወር፣ “ዳንዲ - የነጋሶ መንገድ” በሚል ርእስ ባሳተሙት መጽሐፍ ላይ ስለ ሰማእቱ ቄስ ጉዲና ቱምሳ ባሠፈሩት ላይ ብቻ ይሆናል። በነገራችን ላይ፣ ዶክተር ነጋሶ በቤተክርስቲያን አካባቢ የሚታወሱት በምዕራቡና በደቡብ-ምዕራቡ የአገራችን ክፍል የወንጌል አገልጋይና መሪ የነበሩት የቄስ ጊዳዳ ሶለን [በ1969 ዓ.ም. በ 78 ዓመታቸው ሞቱ] ልጅ በመሆናቸው ነው። ዶክተሩ፣ በመጽሐፋቸው ውስጥ ስለ ፍትሕ፣ በእግዚአብሔርና በሕግ ፊት ስለ ሰው ልጆች እኩልነት፣ ስለ ነፃነት ይገደኛል፤ ለዚህም ስታገል ኖሬአለሁ የማለታቸው መሠረቱ ምን እንደ ሆነ መገመት አያዳግትም። አባታቸው ቄስ ጊዳዳ [“ጊዳዳ” ትርጓሜው፦ “ለሕዝብ የሚያነባ” ማለት ሲሆን] በወንጌል ምክንያት የተሰደዱና ቤተክርስቲያን በመትከል የታወቁ የእምነት ሰው ነበሩ። በተጨማሪ፣ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት አሳድገው ለአገር መሪነት ያበቋቸውን እንደ እነ ክቡር አቶ አማኑኤል አብርሃምን፣ አቶ መርኪና መጃን፣ ኦነሲሞስ ነሲብን መጥቀስ ይቻላል። በአፍሪቃ የነፃነት ትግል ውስጥ ደግሞ ስመ-ጥር የሆኑት እነ ኔሬሬ፣ ማንዴላ፣ ካውንዳ፣ ንኵሩማ፣ ወዘተ፣ ከወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት የፈለቁ ናቸው። የቤተክርስቲያን አስተዋጽዖ እንደ ቀላል ሊታይ አይገባም ማለት ነው።

በ “ነጋሶ መንገድ” ላይ፦ ደርግ፣ቄስ ጉዲና ቱምሳንየገደለው፣ “የኦሮሞ ነፃነት ግንባር [ኦነግ] ናቸው ብሎሲሆንደርግከወደቀበኋላደግሞየቄሱአስከሬንከጅምላመቃብርወጥቶበስርዓትበተቀበረበትጊዜደርግቄሱንየገደለውየሃይማኖትነፃነትንለማፈንነበር ተብሎየተነገረውን ትክክል አይደለም ብለዋል። ለዚህም ማስረጃቸውን እንደሚከተለው አቅርበዋል፦ 1969 .ቄስጉዲናለቤተክርስቲያንስራወደጀርመንሲመጡእግረመንገዳቸውንከኦነግመልእክትይዘውመጥተውነበር።መልዕክቱንለመንገርመጀመሪያዲማነገዎማስትሬትዲግሪውንእያጠናከነበረበትሴኔጋልወደጀርመንእንዲመጣአደረጉናከዚያፍራንክፈርትከእኔጋርተገናኙ።ለእሱየመጣውመልዕክትጀርመንሀገርቢሮበመክፈትየኦነግወኪልሆኖእንዲሰራየሚልነበር።እኔደግሞዲማንእንድረዳነበርየተፈለገውሌላውቄስጉዲናየሰጡኝመረጃኦነግበመካከለኛውምስራቅአንድልዑክእንደሚልክናልዑኩበባሮቱምሳእንደሚመራየሚጠቁምነበር ቄስጉዲናንለመጨረሻጊዜያገኘኋቸውያኔነው።ደርግ፣ሀገርቤትሲገቡእስርቤትአስገብቶገደላቸውናከሌሎችጋርበጅምላተቀበሩ…” [ገጽ 110]።

ዶክተር ነጋሶ ማስረጃ ብለው ያቀረቡት አከራካሪ አይሆንም። ደርግ ቄስ ጉዲናን የገደለው ኦነግ ናቸው በሚል ሰበብ ነው። ይህን ስንል፣ ደርግ የወሰደው የግድያ እርምጃ ሆነ ያቀረበው ሰበብ ትክክል ነው ማለት አይደለም። ቄስ ጉዲናን በኦሮሞነታቸው ወይም በፖለቲካ አመለካከታቸው ብቻ ፈርጆ ማለፍ ግን የኖሩለትንና የተሠውለትን የሕይወት ምስክርነት ማጕደፍ ይሆናል። ግለሰቡ ቁመተ-ረጂም፣ ከሠፈር ያለፈ ሰፊ አእምሮ የተለገሳቸው ነበሩና። ዶክተር ነጋሶ ይህን የሚክዱ አይመስለንም። በሌላ አነጋገር፣ የክርስቶስ ተከታይና የቤተክርስቲያኑ መሪ እንደሆኑ ከግምት ውስጥ ሳናስገባ ቄስ ጉዲናን ጠንቅቀን መረዳት አዳጋችና አሳሳች ይሆናል። ደርግ፣ ቄስ ጉዲናን የገደልኩት የቤተክርስቲያን መሪ በመሆናቸው ነው ሊል እንደማይችል ግልጽ ይመስለናል። በቤተክርስቲያን ላይ ስደት እና በአማንያን ላይ እስራት በታወጀበት ሰዓት የአምልኮ ነፃነት አለ አልልም ማለታቸው፤ ቀይና ነጭ ሽብር በየአውራ መንገዱ ያፈሰሰው ደም ሳይደርቅ እንዲህ የመሰለ አቋም መውሰድ ምን እንደሚያስከትል ለማንም ግልጽ ነው። በዚህ ላይ ወንድማቸው ባሮ ቱምሣ የአንጃ ፖለቲካ ፓርቲ መሪ ናቸው።

ቄስ ጉዲና የተሠውት በ 1971 ዓ.ም. በሃምሳ ዓመታቸው ነው። አመለካከታቸው ከጎሣና ከዘር ያለፈ ነው ስላልን መድገም አያሻንም። ጽሑፋቸውን ያነበበና ንግግራቸውን ያደመጠ ማንም እንደሚያውቀው ወንጌልን ከማሕበራዊ ፍትኅ ጋር አገናዝበው ማየት የተቻላቸው ግለሰብ ነበሩ። የክርስቶስን ወንጌል በቤተክርስቲያን ክልል መወሰን ወይም በማሕበረ ሰብ ጠርዝ ላይ መትከል፣ የወንጌልን “ብርሃን እና ጨው” ነት አለማጤን እንደሆነ የተረዱ መሪ ነበሩ። ለመንግሥት ሥጋት የሆኑት ከዚህ አመለካከታቸው የተነሳ ነው። ስለ ሰው ማንነት ያላቸው መረዳት ከወንጌል አስተምርሆ የመነጨ እንጂ ከሰብዓዊነት አመለካከት ብቻ የፈለቀ አልነበረም። ወንጌል፣ ሰው በእግዚአብሔር አምሳል መፈጠሩን፣ ከዚህ የተነሳ ክቡር መሆኑን፣ በአዳማዊ ኃጢአት ምክንያት ከፈጣሪው፣ ከራሱ፣ ከባልጀራውና ከፍጥረት ሁሉ ጋር መቆራረጡን ያስተምራል። ይህም ከማርክሳዊ አመለካከት፣ ብርሃን ከጨለማ እንደሚለይ ይለያል። ወንጌል፦ ሰው ቁስ ብቻ ሳይሆን፣ ነፍስም መንፈስም ነው፤ በሥጋ በተገለጠው በኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በኩል ከአምላኩ፣ ከራሱና ከሌላው ጋር የሚታረቅበት መንገድ ተዘጋጅቶለታል ይላል። እንግዲህ፣ እግዚአብሔርን ያላማከለ አመለካከት ሰውን ከኢኮኖሚያዊና ከማሕበራዊ ግንኙነቶቹ ነጥሎ ማየት እንደሚሳነው በደርግና አሁን በሚገዛው መንግሥታት የታየው አመራር በቂ ማስረጃ የሚሆን ይመስለናል።

ቄስ ጉዲና በኢትዮጵያ ጠቅላይ ግዛቶች ማንበብና መጻፍ እንዲስፋፋ ከወጠኑትና ጥረት ካደረጉት መካከክል የመጀመሪያው ናቸው። አብዮት ከመፈንዳቱ በፊት፣ ማሕበራዊ ነውጥ ተቃርቧል፣ ቤተክርስቲያን መዘጋጀት አለባት ሲሉ እንደ ነበረ የሰሙ ዛሬም በሕይወት አሉ። ደርግ ሥልጣን ሲይዝ፣ ጸረ-ሃይማኖት/ጸረ-ክርስቲያን መመሪያ እንደሚያውጅ፣ ለዚህም ሥርዓት መበገር እንደማይገባ ጠንቅቀው ተረድተው ነበር። ንጉሥ ቢሆን፣ የፓርቲ ማእከላዊ ኮሚቴ ሊቀመንበር፣ የክርስቶስን ጌትነት ለሚቀናቀን ለማናቸውም ምድራዊ ሥልጣን ማጎንበስ አይገባም ይሉ ነበር።

ኢየሱስ ነው ከሁሉም በላይ

ጌታችን ነው ከሁሉም በላይ

አቻ የሌለው በምድር በሰማይ

እንደ እውነቱ ከሆነ፣ ዶክተር ነጋሶ ስለ ቄስ ጉዲና የነገሩን አዲስ ነገር የለም። ቄስ ጉዲና ኦሮሞ መሆናቸው፣ የመጣው ለውጥ ከአብራኩ ለወጡት ሕዝብ ያስገኘው ጥቅም አንሶ እያዩ ዝም አለማለታቸው እንደ ድንቅ ሊታይ አይገባም።  ዶክተር ነጋሶም እኮ ኦሮሞ ናቸው። ኦሮሞ ስለሆኑ፣ የሚታገሉት ለኦሮሞ ሕዝብ ብቻ ነው ማለት ታዲያ የትግላቸውን ፈር ባጭር አያስቀርም? ያስቀራል እንጂ። አያስቀርም ብንል፣ በመጽሐፋቸው ላይ እንደ ተመለከተው ለዲሞክራሲ፣ ለሕግ የበላይነትና ለሰብአዊ መብት መከበር ያደረጉት አስተዋጽዖ ያግደናል። ስለ ቄስ ጉዲና ግን ሊዘነጋ የማይገባ ጉዳይ፣ ደርግ በፍትኅ ስም የሚያካሄደውን ግድያና በደል አይተው ዝም አለማለታቸውና አለመተባበራቸው ነው። እኚህን ሰው በአንድ አንጃ መከለል አግባብ አይሆንም የምንለው ለዚህ ነው። የሰውን ሞላ ነፃ የሚያወጣውን የክርስቶስን ፍትሓዊ ወንጌል አቋማቸው ቢያደርጉ ድንቅ አይደለም ማለት ነው። በሌላ አነጋገር፣ ዶክተር ነጋሶ፣ ኦነግ ናቸው ብለው ያቀረቡት ማስረጃ፣ ቄስ ጉዲና የክርስቶስ ቤተክርስቲያን መሪ ከመሆናቸውና ዘርና ጎሣ ከማይወስነው ፍትኀዊ ወንጌል አራማጅነታቸው አንዳች እንደማይቀንስ ነው። ባጭሩ፣ የጉዲናን ስነመለኮታዊና ማሕበራዊ አቋም መነጣጠል ሐቅን ማዛባትና የሌለ ስም መስጠት ይሆናል። 

መንግሥታት ሁሉ የሚቀናቀናቸውን ለማስወገድ የሚጠቀሙበት ዘዴ ተመሳሳይ ነው። የአሜሪካ መንግሥት፣ እ.አ.አ በ1968 ዓ.ም. የሰብአዊ መብት ተሟጋች የነበረውን ቄስ ማርቲን ሉተር ኪንግን [በ 39 ዓመቱ ተሠዋ] የገደለው ኮሚዩኒስት ብሎ ነው። ማርቲን ኪንግ የአገሩን ዘረኛ ፖሊሲ መቃወሙ ብዙ ችግር አስከትሎበታል፤ የራሱና የቤተሰቡ ሕይወት እለት እለት ለአደጋ የተጋለጠ ነበር። የፍጻሜ እርምጃ የተወሰደበት ግን ከቤተክርስቲያን ክልል ወጣ ብሎ፣ አሜሪካ በቪዬትናም ስለምታካሄደው ሕገ ወጥ ጦርነት እና፣ በተለይም በኢኮኖሚ ረገድ በጥቁሮች ላይ የሚካሄደውን አድልዎና ግፍ መቃወምና ወደ ሰሜኑ የአሜሪካ ግዛት ዘልቆ ማደራጀት በጀመረበት ወቅት ነበር። ወንጌል ሙሉ የሚሆነው፣ ቤተክርስቲያን ነፍሳትን ወደ ክርስቶስ መንግሥት ከማምጣት ጋር ለማሕበራዊ ፍትኅ ስትታገል ጭምር ነው። ይህም ከፍተኛ መስዋእት ይጠይቃል፤ ፍሬው ደግሞ በደም ይደረጃል።

የጀርመን መንግሥት ቄስ ዲትሪኽ ቦንኦፈር [እ.አ.አ. በ1945 ዓ.ም. በ 39 ዓመቱ ተሠዋ] እውነተኛዪቱ ቤተክርስቲያን፣ ይሁዲና ጂፕሲዎች እየታደኑ ባለበት ሰዓት፣ ማሕበረ ምእመኑን እንዳያስተምር አሳቡን በጽሑፍ እንዳያሠፍር በማገዱ ሂትለርን ለማስወገድ ከተደራጁት ጋር ለማበር ተገደደ። ያኔ ለቦንኦፈር ጥያቄ የሆነበትና ዛሬም ለኛ ጥያቄ ሊሆን የሚገባው፣ እንዴት ከተመረዘ ማሕበራዊ ሥርዓት ውስጥ ራስን ማዳን ይቻላል የሚለው ሳይሆን፣ የሚቀጥለው ትውልድ እንዴት ይሆናል? እንዴትስ ይኖራል? የሚለው ነው። ቦንኦፈር አሜሪካ ሄዶ በዚያው መቅረትና ተደላድሎ መኖር ሲችል፣ የሚያውቁት ሁሉ ‘አትሂድ፣ ችግሩ ይለፍ’ ሲሉት እምቢ ብሎ ወደ ትውልድ ምድሩ ወደ ጀርመን አገር የተመለሰው ሊገደል እንደሚችል ሳይጠረጥር ቀርቶ አይደለም።

የኢጣልያ ፋሺስት አቡነ ጴጥሮስን [በ 1928 ዓ.ም. በ 54 ዓመታቸው ተሠው] ገና አገራችንን እንደ ወረረ ወዲያው ያስገደለው አላስቀምጥ አላስተኛ ስላሉ ነው፤ ሕዝቡን ለአረመኔ ወራሪ አልገዝትም፣ የተቀበልኩትን የወንጌል አደራና ሕዝቡን አሳልፌ ከምሰጥ ብሠዋ ይሻለኛል ስላሉ ነው። ለሕይወታቸው አልሳሱም።

ቄስ ጉዲና፣ ቄስ ማርቲን፣ ቄስ ቦንኦፈር እና አቡነ ጴጥሮስ በተገኙበት ሰማእታት ናቸው። ሁሉም የወጡት ከክርስቶስ ቤተክርስቲያን ነው። የሞቱት በወንጌል ዓላማ ለፍትኅ ነው። በመጨረሻዋ ሰዓት የተናገሩትን ቃል ማገናዘብ ደግሞ የሕይወታቸውን ጥሪና ቁምነገር ቁልጭ አድርጎ ያሳየናል። ሰው ወደ ሞት ሲቃረብ የሚናገረው ከሌላው ጊዜ ይልቅ ተኣማኒነት ይኖረዋልና። ለዚህም ነው ወደ ሞት ለተቃረበ ሰው፦ ምን የምትለው ነገር አለህ? ተብሎ የመጨረሻ እድል የሚሰጠው።

ብፁእ አቡነ ጴጥሮስ፣ በፋሺስት ገዳዮች ፊት ቆመው፦ “ሥጋንም የሚገድሉትን፣ ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ …” እያሉና ሕዝቡ እጁን እንዳይሰጥ እየመከሩ በጥይት ተደብድበው ሞቱ። ይህም፣ “ለጊዜው፣ በኃጢአት ከሚገኝ ደስታ ይልቅ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራ መቀበልን መረጠ” የሚለውን ሐዋሪያዊ ቃል ያስታውሰናል [ማቴዎስ 10:28 እና ወደ ዕብራውያን 11:25]።

ማርቲንኪንግ የተጋበዘበት የምሽት ፕሮግራም ከመድረሱ በፊት፣ ሙዚቃ እንዲጫወት ለተመደበው ሰው፣ “ውድ ጌታ [ኢየሱስ] …እጄን ያዘኝ” የምትለዋን ዝማሬ ጥሩ አድርጎ እንዲጫወታት ደጋግሞ ጠይቆት ነበር። ቦንኦፈር ደግሞ፣ “እነሆ ፍጻሜው ደረሰ፣ ለኔ ግን የሕይወት ጅማሬ ነው” ብሎ ተንበርክኮ ከጸለየ በኋላ ተሰቀለ።

ለቄስ ጉዲና፣ “… እንግዲያስ ሁሉ ሞቱ፤ በሕይወትም ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ” የሚለው ቃል መመሪያቸው እንደነበር ተዘግቧል [2ኛ ቆሮንቶስ 5:15]። ተይዘው በተገደሉበት ምሽት፣ በኡራዔል መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ኢየሱስን ከሰበኩ በኋላ ኢየሱስን እያሰቡ ደጅ ወጡ። በጨለማ ተገን አፍነው ገደሏቸው። ነፍሳቸው ግን ወደ ዘላለሙ ብርሃን፣ የዓለም ብርሃን ወደ ሆነው ወደ ኢየሱስ አገር አመለጠች። ሃሌ ሉያ!

ታዲያ፣ አንድን ግለሰብ ሰማእት ነው የሚያሰኘው ምንድነው? ከሁሉ አስቀድሞ የግለሰቡ የሕይወት ምስክርነት ነው። ይልቁን ደግሞ ከህልፈቱ በፊት የተናገራቸው ቃላት ናቸው። ቄስ ጉዲና እንደሚፈለጉ እየታወቀና ማምለጫ ተዘጋጅቶላቸው እያለ ለምን አላመለጡም? ታስረው መፈታታቸው ማስጠንቀቂያ ሳይሆናቸው ቀርቶ ነው? ምሥጢሩ፣ ራሳቸውን የቤተክርስቲያኑ እረኛ ከሆነው ከኢየሱስ በታች የመንጋው እረኛ መሆናቸውን ጠንቅቀው የተረዱ ሰው ስለነበረ ነው። በታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ጁሊየስ ኔሬሬ አማላጅነት ከእስር ተፈትተው፣ ከአገር እንዲወጡ አሳብ ሲቀርብላቸው፦ “እኔ የቤተክርስቲያን መሪ ሆኜ ሳለ፣ እንዴት በፈተና ሰዓት መንጋውን ትቼ እሸሻለሁ? ደግሞስ፣ ካህናቱን የትም አትሂዱ ብዬ እየተማፀንኳቸው ልሸሽ? አልሸሽም፣ አላደርገውም” ብለው ነበር የመለሱት። “መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል። እረኛ ያልሆነው በጎቹም የእርሱ ያልሆኑ ሞያተኛ ግን ተኵላ ሲመጣ ባየ ጊዜ በጎቹን ትቶ ይሸሻል፤ ተኵላም ይነጥቃቸዋል፣ በጎቹም ይበተናሉ” [ዮሐንስ 10:12]።

የ”ነጋሶ መንገድ” ይህን ዋነኛ ስነ መለኮታዊ መረዳት የዘነጋው ይመስላል። ምናልባት መጽሐፉ የተጻፈው ከዚህ አኳያ ስላልሆነ ሊሆን ይችላል። ወቅቱ በወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ላይ መንግሥት የስደት እና የእሥራት ዘመቻ የሚያካሄድበት ሰዓት ነበር። ቄስ ጉዲና የሚመሩት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ደግሞ ብዙ እንቅስቃሴዋ በውጭው ዓለም እና በምዕራብና ደቡብ-ምዕራብ ኢትዮጵያ መሆኑ፣ የኦነግ መሪዎችም [ዶክተር ነጋሶን ጨምሮ] አብዛኛዎቹ ከቤተክርስቲያንና ከዚሁ ክፍለ ሃገር የወጡ መሆናቸው ለመንግሥት ሥጋት ፈጥሮ ነበር። ከዚህ የተነሳ ቤተክርስቲያንና መሪዎቿን በዐይነ ቁራኛ መከታተል ግድ ሆነ፤ አድራጎቱም፣ የመንግሥትን ኢፍትኀዊ አመራር አደባባይ አወጣው።

ከዚህ መጽሐፍ ጋር በተያያዘ አንድ የሚከነክነንን ጉዳይ እናንሳና እንጨርስ። ለመሆኑ፣ የአገራችን ምሑራን ባለፉት ሃምሳ ዓመታት ዘላቂ የሆነ ምን ማሕበራዊ አስተዋጽኦ ወይም መፍትሔ አስገኝተዋል? በመደብና በጎሣ ሕዝቡን ከፋፍለው አለመተማመንን ዘርተውበታል፤ ይህን አይተናል። ያውቃሉ የተባሉት እርስ በርስ መስማማት ሆነ መከባበር ተስኖአቸዋል። አገሪቷን ወዴት መምራት እንደሚገባቸው ገና እርግጠኞች አይደሉም፤ የሌሎችን አሳብ ለመስማት አይፈቀዱም። የጋራ በሆነች አገር፣ ያልተስማማቸውን የማግለልና የማውገዝ ባሕል ተጠናውቶአቸዋል። ይህንና ያን ሲሉ ስንት ትውልድ ፈጁ፤ በሙከራ ብቻ ምድሪቷን አስረጁ። ቤተክርስቲያንን ከሚያፈርስ፣ ፈርሃ እግዚአብሔርን ከሚሸረሽር አድራጎት ሊቆጠቡ አልቻሉም። ቤተክርስቲያንን ለዓላማቸው ከመጠቀም አልቦዘኑም። የክርስቶስን ወንጌል ከባህል፣ ከአፈ-ታሪክና ከጎሠኛ አስተሳሰብ ለይተው ስለማያዩ፣ ሕዝበ ክርስቲያኑን ያምሳሉ። “እግዚአብሔር የለም” ያሉንና ሊያሰኙን ያንገላቱን ዛሬ ወዴት አሉ? የክርስቶስ ቤተክርስቲያን ግን ዛሬም አለች፣ ጌታዋ ሕያው ስለሆነ፣ ሕያው ነች። እግዚአብሔርን የማይፈሩ፣ እግዚአብሔር የማያይ የመሰላቸው ሕዝብን ሲበድሉና ሲያንገላቱ፣ ለወገኔ ይጠቅማል ማለት ሲያበዙ፣ የምሕረት እጁን ስለ ዘረጋ እንጂ፣ ዝምታው ስለማይፈርድ አለመሆኑን አላስተዋሉም። እግዚአብሔር ሳ-ይ-ፈ-ራ ሕዝብ አይዋደድም፤ እግዚአብሔር ሳይከበር ሕዝብ አይከበርም፤ አይከባበርም።

“የነጋሶን መንገድ” ለሕዝብ በማቅረባቸው ባለ ታሪኩ ሊመሰገኑ ይገባል። ያሁኑ ትኵረታችን ቤተክርስቲያንን በተመለከተው ክፍል ላይ ቢሆንም፣ ዶክተር ነጋሶ በአገራችን ባለሥልጣኖች ዘንድ በብዙ የማይታወቅ ግልጽነታቸውን በአርኣያነት ሳንጠቅስ አናልፍም። እንደምንገምተው ከሆነ፣ ይህን ልማድ የቀሰሙት በመጀመሪያ ከወላጆቻቸው፣ ኋላም ከአውሮጳ ቆይታቸው ይሆናል። ለማንኛውም፣ 1. የአገር መሪ በሕይወት እያለ ከሥልጣን ወርዶ በሕዝብ መካከል እንደ ተራ ዜጋ መኖር፤ 2. የአገራችን ፕሬዚዳንት እንዲሆኑ በተጠየቁ እለት እንደ ፈሩና ሌላ ሰው ፈልጉ እንዳሉ መግለጻቸው፤ 3. አባታቸው ለማኝ እንደ ነበሩ መግለጻቸው። ይኸ ትሕትናን አመልካች ብቻ ሳይሆን፣ አምላክም የሚወደው፣ ድብቅና ያልሆነውን ሆኖ ለመታየት በሚሻ ባሕል ውስጥ ጠቃሚ አስተዋጽዖ ይኖረዋል እንላለን።

እንግዲህ፣ “የነጋሶ መንገድ” እነሆ። ሌላው መንገድ የክርስቶስ እና የተከታዮቹ መንገድ ነው። የአገራችን ምሑሩ ክፍል ሃምሳ ዓመት የተጓዘበት መንገድ የእግዚአብሔር ፍርሃት የሌለበት ምድረ በዳ ነበረ፤ አላዋጣም። የእረፍት እህል፣ የእረፍት ውሃና ሰላም አላመጣም። አለማዋጣቱ በሥጋና በነፍሱ ላይ ጠባሳ ትቶ አልፏል። ደርግና ምሑራኑ እግዚአብሔርን ሻሩ፤ በመጤ ፍልስፍና የመደብ ልዩነት ብለው ምድሪቷን አመሳቀሉ። ደርግን ተቃውመው የተነሱ ተራ ሲደርሳቸው በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረውን ሰው በጎሣ ልዩነት አቃቃሩ። ሁለቱም የእግዚአብሔርን ፍርሃት አጥብቀው ተጻረሩ። ኧረ ለመሆኑ፣ የኢትዮጵያ መሪዎችና ምሑራን የሚማሩት መቼ ይሆን? ለ “ክርስቶስ መንገድ” የሚለቁለትስ መቼ ይሆን?! 

Read 9633197 times Last modified on Sunday, 13 November 2011 22:03

1439457 comments

  • Comment Link หนังโป๊ Saturday, 04 October 2025 07:48 posted by หนังโป๊

    I'm really impressed with your writing skills as well as with the layout on your blog. Is this a paid theme or did you customize it yourself? Anyway keep up the excellent quality writing, it?s rare to see a nice blog like this one nowadays..

  • Comment Link หนังโป๊ Saturday, 04 October 2025 07:48 posted by หนังโป๊

    Today, I went to the beachfront with my children. I found a sea shell and gave it to my 4 year old daughter and said "You can hear the ocean if you put this to your ear." She put the shell to her ear and screamed. There was a hermit crab inside and it pinched her ear. She never wants to go back! LoL I know this is entirely off topic but I had to tell someone!

  • Comment Link หนังโป๊ Saturday, 04 October 2025 07:47 posted by หนังโป๊

    Hey there, You have done a fantastic job. I?ll definitely digg it and personally recommend to my friends. I'm confident they'll be benefited from this web site.

  • Comment Link дрова дешево_qbEr Saturday, 04 October 2025 07:46 posted by дрова дешево_qbEr

    купить кубометр дров .

  • Comment Link 有道下载 Saturday, 04 October 2025 07:46 posted by 有道下载

    在现代学习和工作中,有道 已成为提升效率的必备工具。无论是下载安装
    有道下载,还是使用 有道翻译 进行多语言交流,都能快速解决问题。对于需要更多功能的用户,可以选择 有道翻译下载 版本。

    国际用户也可以依赖 youdao 与 youdaofanyi,它们提供简洁高效的语言学习与翻译体验。在日常学习中,有道词典 能够帮助随时查词,而 有道云 则支持笔记和文件的同步管理。

    依托 网易有道翻译 与 网易有道 的技术优势,翻译有道 更加精准。出国旅行或日常交流时,有道翻译官 也是一个可靠选择。

    你可以在线使用 有道在线翻译,也可以通过 youdao
    downlooad 获取桌面版本。对于更高需求,有道翻译电脑版
    与 有道翻译官网 将提供最全面的服务和最新功能支持。

  • Comment Link ведение бухгалтерии аутсорсинг_rwki Saturday, 04 October 2025 07:45 posted by ведение бухгалтерии аутсорсинг_rwki

    vedenie-buhgalterii-autsorsing-811.ru .

  • Comment Link look at this Saturday, 04 October 2025 07:44 posted by look at this

    What's Happening i'm new to this, I stumbled upon this I've found It
    absolutely helpful and it has helped me out loads.

    I'm hoping to contribute & help other users like
    its helped me. Great job.

  • Comment Link купить дрова колотые_tnKi Saturday, 04 October 2025 07:41 posted by купить дрова колотые_tnKi

    kupit-drova-kolotye-49651.ru .

  • Comment Link Google Authenticator Saturday, 04 October 2025 07:41 posted by Google Authenticator

    推荐去 谷歌验证器官网 获取更多信息。
    我经常在电脑端用 谷歌验证器电脑版。
    大家都在分享 谷歌身份验证器下载 的便捷方法。
    更新建议直接看 Google Authenticator官网。
    在PC端尝试 Google Authenticator电脑版 很不错。
    整体来看安全性非常高,值得信赖。

  • Comment Link Loribot Saturday, 04 October 2025 07:41 posted by Loribot

    в казахстане с 1 апреля 2007 г. вступил в реальность закон «об игровом бизнесе», согласно которому во всех регионах (исключение составляют Конаев и Щучинск) закрыты все онлайн крипто казино и однорукие бандиты.

Leave a comment

Make sure you enter all the required information, indicated by an asterisk (*). HTML code is not allowed.