×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 42
Sunday, 13 November 2011 21:20

የአቶ መርኪና መጃ ግለ ታሪክ - ክፍል አንድ Featured

Rate this item
(0 votes)

የመጽሐፍ ግምገማ

የአቶ መርኪና መጃ ግለ ታሪክ - ክፍል አንድ

 

አቶ መርኪና በሰማንያ ሦስት ዓመታቸው በኅዳር ወር 2000 ዓ.ም. ወደ ጌታ ተሻግረዋል። በቀብራቸው ሥርዓት ላይ ከስምንት ሺህ በላይ ሰው እንደ ተገኘ ታውቋል። ይህ ክፍል “የአቶ መርኪና መጃ ግለ ታሪክና የወላይታ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ታሪክ” በሚል ግለሰቡ ጽፈው በ 2000 ዓ.ም. ከታተመው መጽሐፍ የተቀነጨበ ነው። ከዚህ ቀደም እንዳደረግነው ሁሉ መጽሐፉን ከመገምገም ይልቅ ከተለያዩ የመጽሐፉ ክፍሎች ቆንጽሎ በማስነበብ አንባቢዎቻችንን በጌታ ሥራ ማደፋፈር የተሻለ እንደ ሆነ ተገንዝበናል። ከ 13 ዓመት በፊት አቶ አማኑኤል አብርሃም “የሕይወቴ ትዝታዎች” በሚል ርዕስ በእንግሊዝኛ ካሳተሙት መጽሐፍ ጋር ተመሳሳይነት አለው። የሚያስገርመው ሁለቱም መሪዎች በቅርብ መተዋወቃቸው ነው፤ ለምሳሌ፣ መርኪና በ ገጽ 44 ላይ ስለ አማኑኤል ያሉትን እንመልከት፦

 

“አንድ ቀን የሚስዮኑ ኃላፊዎች፣ “በታንዛንያ ለሚካሄደው የሉተራን ቤተ ክርስቲያን ታላቅ ስብሰባ የሲዳማን ቤተ ክርስቲያን ወክለህ እንድትገኝ ተጠርተሃል፣ ጉባኤው የሚካሄደው በክሊማንጃሮ ተራራ አጠገብ ነው” አሉኝ። እኔም ተደነቅሁና፣ “ከእነዚያ ታላላቅ ሰዎች ጋር ጉባኤውን ለመካፈል እኔ ምን ዕውቀትና ችሎታ አለኝ? የእግዚአብሔር ፈቃድ ከሆነ፣ ወደሚልከኝ ቦታ ሁሉ እሄዳለሁ” ብዬ “እሺ” አልኩኝ። ተነሥቼ የሚስዮኑ መሪዎች ጉባኤው ወደሚካሄድበት አገር ለመጓዝ ወደሚዘጋጅበት ወደ አዲስ አበባ ሄድኩኝ። ዶ/ር አማኑኤል አብርሃም እና ዶ/ር አማኑኤል ገ/ሥላሴ ከሚሄዱት መካከል ነበሩ። ለጉዞው ከመነሣታችን በፊት ዶ/ር አማኑኤል አብርሃም በመኖሪያ ቤታቸው የእራት ግብዣ አደረጉልን። በሕይወቴ እንደዚያ ዓይነት ግብዣ አይቼ አላውቅም። እሳቸው በጊዜው በኢትዮጵያ መንግሥት የተሾሙ ሚኒስትር ነበሩ። በድሆች መካከል ክርስቶስ ራሱን ዝቅ እንዳደረገ፣ እርሳቸው በእኛ መካከል ራሳቸውን ዝቅ ያደረጉ ነበሩ።”

 

ሁለቱም መጽሐፎች በድምሩ ቢያንስ የመቶ ዓመት የቤተክርስቲያንን ታሪክ ከነበረው ማሕበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ጋር በማያያዝ ይተረጉማሉ። ሁለቱም ጸሐፊዎች በሂደቶቹ ውስጥ ታዛቢ ብቻ ሳይሆኑ መሪዎችም ስለ ነበሩ ያቀረቡልንን ሠነድ ጠቃሚነት አጉልቶታል። በኛ አስተያየት ይህን መሰል መጽሐፎችን በቤተክርስቲያን አመራር ላይ የሚገኙ ሁሉ በጥንቃቄ ሊያነብቡ ይገባል። በመጽሐፍ ቅዱስ ትምሀርት ቤቶችና ሴሚናሪዎች እንደዚሁም የመሪነት ሥልጠና በሚሰጡባቸው ቦታዎች ሁሉ ዋነኛ የመማርያና የመወያያ መጽሐፎች ሆነው ሊቀርቡ ይገባል። የሁለቱን መሪዎች አመራር በጥንቃቄ መመርመር ተገቢም ጠቃሚም ነው። እነዚህን ዓይነት አገልጋዮች ስለ ሰጠን አምላካችንን በብዙ ልናመሰግነው ያስፈልጋል። በተጨማሪም አልተተረጎሙ እንደ ሆነ የአቶ አማኑኤል ወደ አማርኛ፣ የአቶ መርኪና ደግሞ ወደ እንግሊዝኛ ሊተረጎሙ ይገባል እንላለን። ጽሑፉን እንድናዳርስ ላስቻሉን ሁሉ ምስጋናችን ይድረሳቸው። የመርኪ ታሪክ እነሆ፦

 

አቶ መርኪና መጃ ተወልደው ያደጉት በደቡባዊ ኢትዮጵያ በወላይታ ዞን ነው። የአቶ መርኪና አባት አቶ መጃ ማዴሮ በ 1888 ዓ.ም. ከአቶ ማዴሮ ሃናቆ እና ከወ/ሮ አሽሬ ዳኖሌ ተወለዱ። አቶ መጃ ነገሮችን ፈጥነው የመረዳት ችሎታ የነበራቸው አስተዋይ ሰው ስለ ነበሩ፣ ሰዎች ከቅርብና ከሩቅ እየመጡ የምክር አገልግሎትን ከእርሳቸው ያገኙ ነበር። መልካም ባሕርያቸውም በኅብረተሰቡ መካከል አክብሮትን እንዲያገኙ አድርጎአቸዋል።

 

አንድ ቀን አባቴ ክርስቲያን ከመሆኑ በፊት ብዙ ክፉ ሥራዎችን ይሠራ እንደ ነበር ነገረኝ፤ እኔም ክፉ ሥራ ሠርቼ እንደ ነበር ተገነዘብኩ። ወንጌል ወደ ማኅበረሰባችን ከመድረሱ በፊት በጨለማ ሕይወት ውስጥ እንኖር ስለ ነበረ፣ የተሻለው ነገር ምን እንደ ሆነ አናውቅም ነበረ። ከዚህም የተነሣ ሕይወታችን ጎስቋላና በፍርሃት የተሞላ ነበር። ከበሽታና ከሞት ለማምለጥ፣ አዝመራችን የበለጠ ምርት እንዲሰጠንና ሌላም ብዙ የሕይወት ውጣ ውረዶችን ለማለፍ መልካም መናፍስትንና ክፉ መናፍስትን መለማመን ነበረብን። ታላቅ እንደ መሆኔ መጠን፣ መሥዋዕት ለማቅረብ ከአባቴ ጋር የምሄደው እኔ ነበርኩ። በእኛ አካባቢ የታወቁ ሰዎች ወደ ፈለጉት አቅጣጫ አንድን ሰው አስከትለውና በቅሎ ላይ ተቀምጠው ይሄዱ ነበር። የአባቴን ካባ ተሸክሜ ከበቅሎአቸው ኋላ የምከተለው እኔ ነበርኩ። በእናቴ ቤተሰቦች በኩል አንድ ስሕተት ቢፈጸም ለመሥዋዕት የሚሆን በግ ይቀርባል። በአባቴ ቤተሰቦች በኩል ደግሞ ክፉ ሥራ ቢሠራ ወይፈን ይታረዳል። ከታረደው እንስሳ የተለያዩ ብልቶች ተወስደው ይጠበሱና ጠንቋዩ ይቀመጥ ባለበት ስፍራ ይቀመጣል። መስዋዕቱ ለሰይጣን የሚቀርብ ከሆነ ፍየል ይታረድና ሥጋው ጠንቋዩ ባዘዘበት ቦታ ይደረጋል። የበቆሎ እሸት እንደ ደረሰ ለዓመቱ ምስጋና የማቅረብ ሥርዓት ይካሄዳል። በቆሎውን ከነገለባው ጠብሶ ወይም ቀቅሎ በመንገድ ዳር ወይም ቤተሰብ ተሰብስቦ በሚያመልክበት ዛፍ ሥር ያኖሩታል። በተጨማሪም አባቴ ጣቶቹን በማር ውስጥ በማጥለቅና ወደ ሰማይ በመርጨት የጣዖት አምላክን ይለምን ነበር። የተረጨው ማር ተመልሶ ሲወድቅ ሮጬ ሄጄ ለመብላት እከጅላለሁ። ሆኖም አባቴ ያየኝ ይሆናል ብዬ እፈራ ስለ ነበር እተወዋለሁ።

 

በ1927 ዓ.ም. አንድ ቀን አባቴና እኔ ወደ ቤታችን ስንሄድ አረፋማውን ጅረት እየተከተልን ወደ ምንጩ አመራንና የአቶ አጌዶን ቤት ስናልፍ አቶ ዋንዳሮ ዳባሮ በአቶ አጌዶን ቤት ውስጥ ወንጌልን እየሰበኩ ኖሮ እኔና አባቴን አይተው ገብተን እንድንሰማ ጋበዙን። እኛም ተስማማን፣ ነገር ግን አባቴ እኔን በቅሎውን እንዳስር ሲያዝዘኝ ልጓሙን ፈትቼ እግሩን በገመድ በዛፍ ግንድ ላይ አሰርኩና ገብተን ለመስማት ተቀመጥን። አቶ ዋንዳሮ ስብከታቸውን ቀጠሉና በመካከሉም መዝሙር ጣልቃ እያስገቡ ያዘምሩ ነበር። ከመዝሙሮቹ አንዱ እንዲህ የሚል ነበር፦

     

በጎቹ የኢየሱስ ክርስቶስን ድምጽ ሲሰሙ

      ሊከተሉት ተፋጠኑ

      አስቀድመው ድምጹን ያልሰሙ ሊደርሱባቸው ተቻኮሉ

      እግዚአብሔርም ጠራቸውና ራሱን ገልጦላቸው ምሥጋናቸውን በደስታ ተቀበለ።

 

ሰባኪው ለረዥም ጊዜ ቢናገሩም እኔ የማስታውሰው ዋና ነጥብ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚች ዓለም አንድ ቀን ይመጣል የሚለውን ነበር። የሚያምኑትንም ከእርሱ ጋር ወደ ሰማይ ይወስዳቸዋል። በእርሱ የማያምኑትን ደግሞ በእሳት ባሕር ውስጥ ይጥላቸዋል። “እናንተ ሰይጣንን ማምለክ አቁማችሁ በጌታ ኢየሱስ እመኑ። አለበለዚያ ግን ከሰይጣን ጋር ወደ እሳት ትጣላላችሁ። ዛሬውኑ ማመን አለባችሁና ፍጠኑ፤” እያሉ ያስጠነቅቁ ነበር።

 

በማጠቃለያውም፣ ስንቶቻችን በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ለማመን እንፈልግ እንደ ሆነ ጠየቁን። ብዙ ሰዎች እጆቻቸውን አወጡ፤ አባቴና እኔም እጆቻችንን አነሣን። አቶ ዋንዳሮም ስብከታቸውን ቀጠሉ። አሁን ሁላችሁም በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በእርግጥ እናምናለን የምትሉ ከሆነ፣ ሰይጣንንና መላእክቱን ማምለክ አቁሙ። እባካችሁ እኔ የምለውን ቃል ከእኔ በኋላ ድገሙ።

 

“አሁን ሰይጣንን ክጃለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስም አምናለሁ። እርሱ ለኃጢአቴ እንደ ሞተልኝ አውቃለሁ። ከኃጢአቴም እንዲያነጻኝ እፈልጋለሁ፤ ዳግመኛ ሰይጣንን አላመልክም፤ ነገር ግን ኢየሱስን እከተለዋለሁ፤ እታዘዘዋለሁም” እያልን ደገምን። ከዚያም ከኢየሱስ ጋር ለመኖር እንዲረዳን አንዳንድ ቀላል መመሪያዎችን ሰጡን። ወደ ቤታችሁ ሂዱና በቤታችሁ ውስጥ የሚገኙትን ለጣዖት አምልኮ የምትጠቀሙባቸውን ቁሳቁሶች አውጥታችሁ ጣሉ። ሁሉንም አቃጥሉት፤ ከዚያም ምግባችሁን በምትመገቡበት ጊዜ፣ ሥራችሁን በምትጀምሩበት ጊዜ፣ እንዲሁም ማንኛውንም ነገር ለመሥራት በምታቅዱበት ጊዜ፣ እግዚአብሔር እንዲመራችሁና እንዲባርካችሁ በጸሎት ጠይቁት። በጸሎታችሁም መደምደሚያ ላይ ይህንን ሁሉ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንጠይቅሃለን ካላችሁ በኋላ “አሜን” ብላችሁ ደምድሙ። በተጨማሪም በጉልበታችሁ ተንበርክካችሁ ማጎንበስ ጥሩ ነው። ስትጸልዩም ዓይኖቻችሁን ትጨፍናላችሁ፣ ካሉን በኋላ ቡና አቀረቡልንና ከመጠጣታችን በፊት ለእኛ እንዳስተማሩን ሲጸልዩ ሰማናቸው። ወደ ቤታችን እንደ ገባን፣ የሆነውን ሁሉ ለመላው ቤተሰብ አስረዳንና እነርሱም በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲያምኑ አጥብቀን ገፋፋናቸው። ታላቅ ደስታም ተሰማን። በቤታችንም ውስጥ ሁሉ ነገር አዲስ መሰለ። እናቴ ቡና አፍልታ “እንጸልይ” አለችን።

 

አባቴም ደግሞ ተንበርክኮ ጸለየና ሁለታችንም ድምጻችንን ከፍ አድርገን፣ “አሜን” አልን። ቤተሰቡ በሙሉ ተደነቁና ምን እንደምናደርግና ወደ ማን እንደምንናገር ጠየቁን። እኛም የተቻለንን ያህል ልናስረዳቸው ሞከርን። እኛ የምንናገረውና የምንጸልየው ጌታ ኢየሱስ ወደሚባለውና የእግዚአብሔር ልጅ ወደ ሆነው፣ እንዲሁም ከሰማይ ወደ መጣው ነው። እርሱ ለኃጢአታችን ሲል ሞቷል፣ ከሞትም ተነሥቷል፤ ወደ ሰማይም ሄዷል፤ ነገር ግን ተመልሶ ይመጣል። የሚያምኑትንም ከእርሱ ጋር ወደ ሰማይ ይወስዳቸዋል። የማያምኑትን ደግሞ በእሳት ባሕር ውስጥ ያቃጥላቸዋል። እናንተም ደግሞ በእርሱ እመኑና ዳኑ ብለን ተናገርን። ወዲያውም አባቴ ተነሣና ሰይጣንን ያመልክ በነበረ ጊዜ ይጠቀምባቸው የነበሩትን ጥቃቅን ዕቃዎችና የተሰቀለውን ልብስ ጨምሮ ወሰደ። እነዚያ ዕቃዎች ሁሉም ወንበዴውን ገድሎ የወሰዳቸው ናቸው። ሁሉንም ሰብስቦ ዥው ባለ ገደል ውስጥ ከተታቸው። ዕቃዎቹ ስለ አሮጌው ሕይወቱ የሚያወሱ ነበሩና ሁሉንም አስወገዳቸው።

 

እናቴና በቤት ያሉት ልጆች በሙሉ ልባቸው በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ለማመን ከአንድ ወር በላይ አልወሰደባቸውም። እናቴንና የቀሩትን ልጆች በሙሉ በተለይ ያሳመናቸው ነገር ቢኖር በአባቴ ላይ ያዩት ትልቅ ለውጥ ነበር። አባቴ አስቀድሞ የነበረው ባሕርይ፣ አንድ ነገር ሲበላሽ በእናቴ ላይ ይጮህና ይቆጣ ነበር። ልጆቹ በሙሉ ይፈሩት ነበር። አሁን ግን ፍጹም ተለወጠና በጣም ደግ ሰው ሆነ። በእኔም የሚታየው ለውጥ ግልጽ ነበር። ለእናቴ ልጆች በሙሉ ጥሩ አልነበርኩም። ከቤት ውስጥም አንዳንድ ነገሮችን እሰርቅ ነበር፤ አሁን ግን በእውነት ተለወጥኩ። “እናንተ ቀድሞ ወገን አልነበራችሁም፤ አሁን ግን የእግዚአብሔር ወገን ናችሁ፤ እናንተ ምሕረት ያገኛችሁ አልነበራችሁም፤ አሁን ግን ምሕረትን አግኝታችኋል” ይላል። [1ኛ ጴጥሮስ 2፡10]

 

ማሳሰቢያ፦ በዚህ ክፍል የሚከተሉትን ነጥቦች በጥሞና እናስተውል፦ የመዝሙርና የቃሉን ጥምረት። የአባትና የልጅ ፍቅር። ለእግዚአብሔር ቃል ያለውን ጥማትና አክብሮት። ለመማር ያለውን ፍላጎትና ምክንያት። ቃሉን ለማስተማር ያለውን ትሕትናና ቅንነት። የገቡትን ቃል ስለ መጠበቅ። ከግል ጥቅም ጋር ሳይያያዝ እግዚአብሔርና ሰውን ስለ ማገልገል።

 

ክርስቲያኖች ይዘምሩ የነበሩትን መዝሙሮች መዘመር ወደድን። አንድ ጊዜ ወደ አቶ ጉንታ ቤት ሄድንና አዲስ መዝሙር ተማርን። ወደ ቤታችን ስንመለስ በመንገዳችን ሁሉ እየዘመርን ስንሄድ፣ የመዝሙሩን ዋና ቃል እንደ ረሳን አስተዋልን። መዝሙሩን በሚገባ ለማወቅ ከነበረን ፍላጎት የተነሣ ተመልሰን ወደ አቶ ጉንታ ቤት ረዥም ጉዞ አደረግን። ወደ ቤቱ በደረስን ጊዜ ግን አቶ ጉንታ በከባድ እንቅልፍ ላይ ነበር። የመዝሙሩ ቃላት ተረስቶናልና እባክሽን ቀስቅሽልንና አንደ ጊዜ ዘምሮልን ቃሉን እንያዝ፣ እርሱም ተመልሶ ይተኛል ብለን ባለቤቱን ለመንናት። እርሷም ከእንቅልፉ ቀሰቀሰችልንና ተነሥቶ መዝሙሩን አዜመልን። ከዚያም አባቴ፣ ወንድሜና እኔ ወደ ቤታችን ተቻኮልን፤ በመንገዳችንም እየዘመርን ሄድን፤ ወደ ቤታችን በደረስንም ጊዜ መዝሙሩን በሚገባ መዘመር ችለን ነበር።

 

      ጌታችን ከሰማይ ወረደ

ከድንግል ማርያም ተወለደ

በመስቀል ላይ ሞተ፣ ሞትንም አሸነፈ

ኃጢአታችንን ተሸከመልን

ተነሣና ወደ ሰማይ ዐርጓል

ተመልሶ ይመጣል

ቅዱሳኑን ለመውሰድም አይዘገይም

 

አዲስ ባገኘነው እምነታችን ለማደግ ከእግዚአብሔር ቃል የበለጠ መማር እጅግ አስፈላጊያችን ነበር። ጎረቤታችን አቶ ጉንታም በታማኝነት አስተምረውናል። እኛም ውስብስብ የሆነውን የአማርኛ ፊደል መማር ጀመርን፤ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው በእነዚህ ፊደላት ስለ ነበር ነው። አባቴ ወደ እራሾ ቤት ሄጄ ፊደልን እንድማር ነገሮችን አመቻቸልኝ። አቶ እራሾ አስቀድሞ ማንበብ የቻለ ስለ ነበር፣ ለጌታ ካለው ፍቅር የተነሣ በፍቃደኝነት የምሥጋና መዝሙሮች ይዘምራል፣ ወንጌልን ይሰብካል፤ እንዲሁም ያለ ክፍያ የአማርኛ ፊደልን ያስተምራል። ለብዙ ቀናት ወደዚያ ስሄድ የምደርሰው ሌሎች ልጆች ተምረው ወደየቤታቸው ተበታትነው ነበር፤ ምክንያቱም ወደ ፊደል መማሪያ ቦታ ከመድረሴ በፊት የምሠራቸው ብዙ አሰልቺ ሥራዎች ስለነበሩብኝ ነው። ብዙ ሳንቆይ ማንበብ ቻልንና የእግዚአብሔርን ቃል የበለጠ እየተረዳን ሄድን። አባቴም በስተ እርጅናው ማንበብ እንደ ሌሎቹ ተማረ። እግዚአብሔርም ምን እንዳደረገልን፣ እርሱን ከሚከተሉትም ጌታ ምን እንደሚፈልግ ማወቅን በጣም እንራብ ነበር።

 

ከጥቂት ጊዜያት በኋላ አባቴና እናቴ ተጠመቁ። እኔም አብሬአቸው ለመጠመቅ ብፈልግም፣ እነርሱ ግን አንተ ገና ልጅ ነህ ብለው አገዱኝ። በደንብ ማንበብ ስትችል ያኔ ትጠመቃለህ አሉኝ። እኔም በጣም ተረብሼ እያለቀስኩ እጠመቅ ዘንድ ለመንኳቸው። ለማግባባት ግን አለመቻሌን በተረዳሁ ጊዜ፣ “ጌታ ሆይ፣ ቶሎ ለማንበብ እንድችል እርዳኝ። ለመጠመቅ እንድችል ብትረዳኝ በቀሪው የሕይወት ዘመኔ አገለግልሃለሁ” ብዬ ጸለይኩ።

 

ከአቶ እራሾ ጋር መማሬን ቀጠልኩኝ። ከእርሱም ጋር ከቦታ ወደ ቦታ መዘዋወር ጀመርኩኝ። በመጀመሪያ አብሬው እየሄድኩኝ እርሱ በሚሰብክበት ጊዜ እኔ በቅሎውን እጠብቅለት ነበር። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን በቅሎውን ሌሎች ክርስቲያኖች እየጠበቁ፣ እኔ ፊደል በማስቆጠር እረዳ ነበር። በኋላም ቁንጠሌ በአቶ ፍንጦ ቤት ቆይቼ እዚያ በምትገኘው ቤተ ክርስቲያን እሰብክና አስተምር ነበር። በጨራቂ አካባቢ ከአቶ እራሾ ጋር ስዘዋወር ብዙ ጊዜ በተለያዩ ስፍራዎች ወንጌልን ሰብኬአለሁ። ማንበብና መጻፍ እንደ ቻልኩ፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ብዙ ክፍሎችን ለማንበብ በቃሁ። ከዚያም እንድጠመቅ ተፈቀደልኝ። ይህ የሆነው በ1932 ዓ.ም. ሲሆን፣ ጋቼኖ በሚባለው ቦታ ሎላሞ ቦቄ እና ፉላሶ የሚባሉ፣ ከሁምቦ ቤተ ክርስቲያን መጥተው አጥምቀውኛል። ከተጠመቅሁ በኋላ ወደ ዋንቼ ፈጥኜ በመሄድ ደስታዬን ለወላጆቼ አካፈልኳቸው፤ እነርሱም ተደሰቱ። መታወቅ ያለበት በዘመኑ የተቀናጀ እውቀት (ትምህርት) ባልነበረበት በዚያ በኢትዮጵያ ክፍል ቤተ ክርስቲያን ራሷ ማንበብና መጻፍ ታስተምር ነበር። በዚህም ብዙ ወጣቶች ማንበብና መጻፍ ከመቻላቸውም በላይ፣ የአማርኛን ቋንቋ ለማወቅ ችለዋል። በእነዚያ ቀናት ቤተ ክርስቲያን ማደግ ጀመረች፤ ብዙ ወጣቶችና ጎልማሶችም ማንበብ ችለዋል። በአንድ እሑድ ከዋንቼ ቤተ ክርስቲያን 70 ሰዎች ተመርጠው ጥንድ ጥንድ እየሆኑ በ 4 አቅጣጫዎች ተላኩ። ለሚያገኙት ሁሉ በመንገድ ላይም ይሁን በቤት ውስጥ ወንጌልን መስበክ ነበረባቸው። ሲመለሱም ለእኛ ቤተ ክርስቲያን ዘገባቸውን ማቅረብ ነበረባቸው። አቶ ቶማ ቡሬ እና እኔ ወደ ሁምቦ ሄድን። የሐማሳን ወንዝ እንደ ተሻገርን፣ ሰዎች ተሰብስበው አገኘን። አግባብተናቸው፦ “ከእግዚአብሔር ቃል ልናስተምራችሁ ነው የመጣነው፣ ለመስማት ትፈልጋላችሁን?” አልናቸው።

 

ሰዎቹም ለመስማት ጓጉተው ነበርና እንድናስተምራቸው ጋበዙን። አቶ ቶማ ጸልዮ ከዘመረላቸው በኋላ እኔ ተነሣሁና ክርስቶስ ሰዎችን ከኃጢአታቸው ለማዳን እንዴት እንደ መጣ ከእግዚአብሔር ቃል አስተማርኳቸው። ትምህርቱን እንደ ጨረስኩ፣ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ግል አዳኝ አድርጎ ለመቀበል የሚሻ ከመካከላቸው እንዳለ ጠየቅሁኝ። ጥቂት ሰዎች እጆቻቸውን አነሡ፤ እኔም ሰይጣንን ክደው ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ግል አዳኛቸው አድርገው ለመቀበል የሚሹ ከመካከላቸው እንዳሉ ዳግመኛ ጠየቅሁኝ። ጥቂት ሰዎች እጆቻቸውን አነሡና ሰይጣንን ክደው ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ግል አዳኛቸው አድርገው እንዲቀበሉ በጸሎት መራናቸው። በቤታቸውም ውስጥ ለሰይጣን አምልኮ ያስቀመጡአቸውን ዕቃዎች እንዲያስወግዱ አስተማርናቸውና ከቤታቸው አውጥተው እንደሚጥሉም ቃል ገቡ። በየሳምንቱ እሑድ እየሄድን እንደምናስተምራቸው ነግረናቸው ጉዞአችንን ወደ ሌላ ቦታ አደረግን። የዚያን እሑድ ጉዞአችን ከተለያዩ ብዙ ቡድኖች ጋር እንድንገናኝ አድርጎናል። ማንቴ ኮቴ በሚባለው ቦታ ብዛት ያላቸው ሰዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው አገኘንና ከእግዚአብሔር ቃል ልናስተምራቸው እንደምንፈልግ ገልጸን ፈቃደኝነታቸውን ጠየቅናቸው። እነርሱም ፈቃደኝነታቸውን ገለጹልን። መዝሙር ከዘመርን በኋላ ስለ ደኅንነት ማስተማር ጀመርን። እግዚአብሔር ልጁን ስለ ኃጢአታቸው አሳልፎ እንደ ሰጠ፣ ነገር ግን ሁላችንም ኃጢአተኞች ነንና አዳኝ ያስፈልገናል ብለን የተቻለንን ያህል በግልጽ ካስተማርናቸው በኋላ፣ በየሳምንቱ እየመጣን እንደምንከታተላቸው ቃል ገባንላቸው። ከዚያም ከሌላ አካባቢ የተከናወነውን ሥራ ለመስማት ወደ ቤት አመራን። በዋንቼ ቤተ ክርስቲያን የቀሩት አማኞች ቀኑን ሙሉ እየጸለዩልን ነበር። ከሰዓት በኋላ ክርስቲያኖቹ ወንጌልን ለመስበክ ለሄዱት 70 ሰዎች ምግብና ቡና በማዘጋጀት ሥራ በዝቶባቸው ዋሉ።

 

በምሽት ተልከው የሄዱት ሰዎች የሚያሰሟቸውን ዘገባ ለማዳመጥ ሁሉም ተሰበሰቡ። ብዙ ሰዎች ቃሉን ሰምተው በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ። ሰይጣንንም ክደው ንስሐ ገቡ። እንዴት ያለ ደስታ ጊዜ ነበር? በመጨረሻም፣ ቡናችንን ጠጥተን ሁላችንም ወደየቤታችን ሄድን። በሚቀጥሉት ቀናት፣ አቶ ቶማ እና እኔ በሁምቦ፣ በኮቴና በሌሎችም አያሌ ቦታዎች ቤተ ክርስቲያንን መሠረትን። በማቴዎስ 28፡ 18-29፣ “ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ፣ እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው። እነሆ፣ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ” ያለውን ቃል ለመታዘዝ አጋጣሚ አግኝተን ነበር።           March 2009

Read 602029 times Last modified on Sunday, 13 November 2011 21:48

161101 comments

  • Comment Link EdwardSilip Thursday, 16 April 2026 03:59 posted by EdwardSilip

    В Воронеже услуга «нарколог на дом» востребована прежде всего тогда, когда состояние развивается быстро, а запас сил у пациента почти исчерпан. После нескольких дней употребления человеку бывает трудно даже выйти из квартиры: сохраняются слабость, дрожь, бессонница, тошнота, скачки давления, потливость, раздражительность и ощущение, что без новой дозы алкоголя легче уже не станет. Именно в этот момент домашний выезд специалиста помогает разорвать опасный цикл. Наркологическая помощь начинается там, где человек находится, а не там, куда он в идеале должен был бы доехать.
    Получить дополнительные сведения - http://www.domen.ru

  • Comment Link Elmerexcef Thursday, 16 April 2026 03:58 posted by Elmerexcef

    Как отмечает врач-нарколог Сергей Иванов: "Самое главное преимущество капельницы с медицинским контролем — это точная диагностика состояния пациента перед началом процедуры и возможность корректировать лечение в процессе, что делает её гораздо более безопасной и эффективной по сравнению с самостоятельными методами."
    Детальнее - капельница от похмелья нижний новгород

  • Comment Link Richardcethy Thursday, 16 April 2026 03:57 posted by Richardcethy

    Запрос на выезд врача связан не только с классическим запоем. На практике домашняя помощь нужна в разных ситуациях, когда организму уже трудно компенсировать последствия употребления, а откладывание визита увеличивает риск осложнений.
    Получить больше информации - вызов нарколога на дом в воронеже

  • Comment Link Jeffreygek Thursday, 16 April 2026 03:52 posted by Jeffreygek

    Когда такие симптомы становятся ярко выраженными, важно не откладывать вызов нарколога. В противном случае токсическое воздействие алкоголя может повлиять на другие органы, такие как печень, почки и сердце, что приведёт к более серьёзным последствиям. Врач на дому проведет экстренную помощь, обеспечит безопасность и поможет избежать ухудшения состояния.
    Подробнее тут - капельница от похмелья на дом в самаре

  • Comment Link NormanGon Thursday, 16 April 2026 03:51 posted by NormanGon

    Решение о госпитализации в наркологический стационар часто становится необходимым в случаях, когда пациент не может справиться с зависимостью самостоятельно, а также когда домашние условия лечения оказываются недостаточными. Стационарное лечение дает пациенту возможность находиться под круглосуточным наблюдением специалистов, что особенно важно при острых состояниях и абстинентных синдромах. В случае запоя может быть предложена помощь нарколога, а также выезд на дом для неотложного вмешательства и стабилизации состояния пациента.
    Детальнее - лечение в наркологическом стационаре

  • Comment Link FloydBug Thursday, 16 April 2026 03:41 posted by FloydBug

    Капельница от похмелья в Самаре с выездом на дом, восстановлением водного баланса и медицинской помощью в наркологической клинике «Частный медик 24»
    Получить больше информации - капельница от похмелья цена самара

  • Comment Link VirgilWhill Thursday, 16 April 2026 03:24 posted by VirgilWhill

    Комплексное лечение в наркологическом стационаре включает несколько последовательных этапов, каждый из которых направлен на решение конкретных задач. Начальный этап включает в себя медицинское вмешательство, направленное на устранение токсинов из организма, и стабилизацию общего состояния пациента. Далее начинается реабилитация, которая помогает закрепить достигнутые результаты и восстановить психоэмоциональное состояние пациента. Для выбора подходящего стационара стоит ознакомиться с отзывами и дополнительной информацией о клинике, а также уточнить, в каком районе города она расположена.
    Изучить вопрос глубже - частный наркологический стационар

  • Comment Link MichaelHon Thursday, 16 April 2026 03:21 posted by MichaelHon

    Капельница от похмелья — это один из наиболее эффективных методов экстренной медицинской помощи, который позволяет быстро снять симптомы алкогольной интоксикации и восстановить организм после злоупотребления алкоголем. В наркологической клинике «Частный медик 24» в Самаре мы предоставляем услугу выезда нарколога на дом и капельной терапии для пациентов, испытывающих тяжёлые симптомы похмелья. Это удобный способ получить необходимую помощь без лишнего стресса, сохраняя анонимность и комфорт пациента.
    Выяснить больше - капельница от похмелья на дом в самаре

  • Comment Link BrendanSmuri Thursday, 16 April 2026 03:18 posted by BrendanSmuri

    Каждый элемент программы направлен на создание комплексного подхода к лечению зависимости, обеспечивая помощь не только на физическом, но и на эмоциональном уровне. Индивидуальная программа реабилитации позволяет выстроить эффективную терапию, которая соответствует конкретным потребностям пациента.
    Подробнее тут - клиника реабилитации алкоголиков город

  • Comment Link BnnrBeind Thursday, 16 April 2026 03:14 posted by BnnrBeind

    how to take tadalafil [url=https://goodtadaffil.com/ ]tadalafil 20mg price[/url] tadalafil 5mg

Leave a comment

Make sure you enter all the required information, indicated by an asterisk (*). HTML code is not allowed.