በዚያን ጊዜም

አሕዛብ ሁሉ አንድ ሆነው

እግዚአብሔርን ያገለግሉት ዘንድ

ስሙን እንዲጠሩ

ንጹሐን ልሳን እመልስላቸዋለሁ

ከኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ የሚማልዱኝ፥

የተበተኑት ሴቶች ልጆቼ፥ ቍርባኔን ያመጡልኛል

በዚያን ጊዜ

እየታበዩ የሚፎክሩትን

ከመካከልሽ አወጣለሁና፥

አንቺም በቅዱስ ተራራዬ ዳግመኛ አትኰሪምና

በዚያ ቀን

በእኔ ላይ ተላልፈሽ በሠራሽው ሥራ ሁሉ አታፍሪም

በመካከልሽም የዋህና ትሑት ሕዝብን አስቀራለሁ

በእግዚአብሔርም ስም ይታመናሉ

የእስራኤል ቅሬታ ኃጢአትን አይሠሩም፥

ሐሰትንም አይናገሩም፥

በአፋቸውም ውስጥ ተንኰለኛ ምላስ አይገኝም

እነርሱም ይሰማራሉ፥ ይመሰጉማል፥ የሚያስፈራቸውም የለም

የጽዮን ልጅ ሆይ፥ ዘምሪ

እስራኤል ሆይ፥ እልል በል

የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥

በፍጹም ልብሽ ሐሤት አድርጊ

ደስም ይበልሽ

እግዚአብሔር ፍርድሽን አስወግዶአል፥

ጠላትሽንም ጥሎአል

የእስራኤል ንጉሥ እግዚአብሔር በመካከልሽ አለ፥

ከእንግዲህም ወዲህ

ክፉ ነገርን አታዪም

በዚያን ቀን

ለኢየሩሳሌም

ጽዮን ሆይ፥ አትፍሪ፥ እጆችሽም አይዛሉ

አምላክሽ እግዚአብሔር በመካከልሽ ታዳጊ ኃያል ነው

በደስታ በአንቺ ደስ ይለዋል፥

በፍቅሩም ያርፋል፥

በእልልታም በአንቺ ደስ ይለዋል ይባላል

ከጉባኤው ርቀው የሚያዝኑትን፥

ከአንቺም የሆኑትን እሰበስባለሁ

ስድብ እንደ ሸክም ከብዶባቸው ነበር

በዚያ ዘመን

እነሆ፥ ባስጨነቁሽ ሁሉ ላይ አደርግባቸዋለሁ

አንካሳይቱንም አድናለሁ፥

የተጣለችውንም እሰበስባታለሁ

ባፈሩባትም ምድር ሁሉ ላይ

ለምስጋናና ለከበረ ስም አደርጋቸዋለሁ

በዚያ ዘመን

አስገባችኋለሁ፥

በዚያም ዘመን

እሰበስባችኋለሁ

ምርኮአችሁንም በዓይናችሁ ፊት በመለስሁ ጊዜ

በምድር አሕዛብ ሁሉ መካከል ለከበረ ስምና ለምስጋና አደርጋችኋለሁ፥

ይላል እግዚአብሔር።

[ትንቢተ ሶፎንያስ 3:9-20]