ም  ና  ል  ባ  ት

horses

በአንድ ደሃ አገር የሚኖር ገበሬ ነበር። ገበሬው አንድ የሚያርስበትና ጭነት የሚያጓጉዝበት ፈረስ ነበረው። ከዚህ የተነሳ ባካባቢው እንደ ባለጸጋ ይታይ ነበር። አንድ ቀን ፈረሱ ጠፋበት። የሚያውቁት ሁሉ ሊያጽናኑት መጡ፣ “እንዲያው ምን ክፉ እድል ነው?” አሉ። ገበሬው ግን ፣ “ምናልባት” አለ እንጂ ሌላ አላለም። ከጥቂት ቀናት በኋላ የጠፋው ፈረስ ሁለት ዘላን ፈረሶች አጅበውት ከች አለ። ገበሬውን የሚያውቁት እንደ ቀድሞው መጥተው፣ “እንዴት መታደል ነው?” አሉ። ገበሬው አሁንም፣ “ምናልባት” አለ። በበነጋው የገበሬው ልጅ አንደኛውን ያልተገራ ፈረስ ሊጋልብ ወጣበት። ፈረሱ አሽቀንጥሮ ጣለው፤ ልጁም እግሩ ተሰበረ። “ምን ጉድ ነው፣ እንዴት የሚያሳዝን ነው?” አሉ። ገበሬው፣ “ምናልባት” አለ። በሳምንቱ ለብሔራዊ ውትድርና ምልመላ ሠፈር ለሠፈር አሠሳ ተጀመረ። ሌሎቹን ወጣቶች ሲወስዱ የገበሬውን ልጅ እግርህ ተሰብሯል አታስፈልግም ብለው ተውት። ወዳጆቹ መጥተው “እንዴት መታደል ነው?” አሉ።   ~

pic credit: kfor.com