የኔ ዕፅ ኢየሱስ ነው!

ayana

ክፍል አንድ። ነሐሴ 6/2008 ዓ.ም። አልማዝ አያና። ኢትዮጵያዊት። ሪዮ ብራዚል። አሊምፒክስ። 10,000 ሜትር። 29 ደቂቃ 17 ሴኮንድ 45 ሚሊሴኮንድ። አንደኛ። ወርቅ። አልማዝ ወርቅ። አዲስ የዓለም ሬኮርድ። 

ክፍል ሁለት። ሳራ ላቲ። ስዊድናዊት። ሪዮ ብራዚል። ኦሊምፒክስ። 10,000 ሜትር። አስራ ሁለተኛ። “አልማዝ ንጹሕ አትመስለኝም። ብዙ ልምድ ሳይኖራት እንዴት ፈጣን ሬኮርድ ማስመዝገብ ቻለች? ዕፅ ወስዳ መሆን አለበት። በዚህ ላይ ፈገግታ አላየንባትም።”

ክፍል ሦስት። “አልማዝ፣ ለሳራ ምን መልስ ይዘሻል?”

ክፍል አራት። [ባስተርጓሚ] መልሴ ቀጥተኛ ነው። አንደኛ፣ ለዚህ ውድድር ስዘጋጅ ነው የከረምኩት። ሁለተኛ፣ ወደ ጌታ ጸልዬአለሁ፤ ጌታም የለመንኩትን ሰጥቶኛል። ሦስተኛ፣ የኔ ዕፅ ኢየሱስ ነው፤ ምክንያቱ ይኸው ነው።”

[መደምደሚያ፦ የሳራ ላቲ ክስ የኢየሱስን ስም በዓለም ሁሉ አስጠራ። ምክንያቱ ይኸው ነው!]

photo credit: runnersworld.com