ጥ ያ ቄ  ሐ ሙ ስ

lionEth

* አንድ የቅርብ ወዳጅህ ግጥም እና ዜማ የመድረስ ተሰጥዖ እንዳለው ብዙ ጊዜ ይናገራል። አደባባይ ግን አውጥቶአቸው አያውቅም። የግጥምና ዜማ ጥረቱ ይሳካ አይሳካ እርግጠኛ መሆን ስላልቻለ ያንተን እውነተኛ አሳብ ማወቅ ይሻል። አንተም ግጥሞቹንና ዜማቸውን ስትሰማ ተሰጥዖ ይቅርና ሽታውም እንደሌለው ትገነዘባለህ። ይህንን ብትነግረው ስሜቱ ይጎዳል። ምን ታደርጋለህ? 

* ከጓደኛህ ጋር ምግብ ልትበሉ የታወቀ ሆቴል ቤት ገባችሁ። ስትጨርሱ ደረሰኝ ቀርቦልህ ሂሳቡን ከፈልክ። ከወጣችሁ በኋላ ደረሰኙን ስታይ ካዘዛችሁት መሓል አንደኛው ሳይመዘገብ ተረስቶ አልተከፈለም። ምን ታደርጋለህ? 

* ማታ ስልክ እደውልልሻለሁ ብለሽ ትደውያለሽ? ሳምንት መጥቼ አይሃለሁ ብለህ ሄደህ ታየዋለህ? እጸልይልሃለሁ ብለህ ትጸልይለታለህ? 

* ሰዎችን ታምናለህ? ሰዎችን ለማመን ምን ያህል ጊዜ ይፈጅብሃል? ሰዎች አንተን የሚያምኑህ ይመስልሃል? ሰዎች ቢያምኑህ ባያምኑህ ግድ አይሰጥህም? 

* ዘወትር በምታገኛቸው ሰዎች ሕይወት ላይ በጎ ተጽእኖ ያሳደርክ ይመስልሃል? በተገናኛችሁ ባጭር ጊዜ ውስጥ በአስተሳሰብህ ላይ ትልቅ ተጽእኖ ያደረገ ሰው ትዝ ይልሃል?