እጓጓለሁ፣ እጓጓለሁ

አዲስ ሰማይንና አዲስ ምድርንም አየሁ፥ ፊተኛው ሰማይና ፊተኛይቱ ምድር አልፈዋልና፥ ባሕርም ወደ ፊት የለም። ቅድስቲቱም ከተማ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም፥ ለባልዋ እንደ ተሸለመች ሙሽራ ተዘጋጅታ፥ ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አየሁ። ታላቅም ድምፅ ከሰማይ። እነሆ፥ የእግዚአብሔር ድንኳን በሰዎች መካከል ነው ከእነርሱም ጋር ያድራል፥ እነርሱም ሕዝቡ ይሆናሉ እግዚአብሔርም እርሱ ራሱ ከእነርሱ ጋር ሆኖ አምላካቸው ይሆናል፤ እንባዎችንም ሁሉ ከዓይኖቻቸው ያብሳል፥ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ ኀዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ የቀደመው ሥርዓት አልፎአልና ብሎ ሲናገር ሰማሁ። በዙፋንም የተቀመጠው። እነሆ፥ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ አለ። ለእኔም። እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛዎች ናቸውና ጻፍ አለኝ። አለኝም። ተፈጽሞአል። አልፋና ዖሜጋ፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ። ለተጠማ ከሕይወት ውኃ ምንጭ እንዲያው እኔ እሰጣለሁ። ድል የሚነሣ ይህን ይወርሳል አምላክም እሆነዋለሁ እርሱም ልጅ ይሆነኛል። ራእይ 21፡1-7 እርሱንና የትንሣኤውን ኃይል እንዳውቅ፥ በመከራውም እንድካፈል፥ ወደ ሙታንም ትንሣኤ ልደርስ ቢሆንልኝ፥ በሞቱ እንድመስለው እመኛለሁ። ፊልጵስዩስ 3፡11

አ ን ዲ ት  ከ ተ ማ  አ የ ሁ

አንዲት ከተማ አየሁ

ማንም ያላያትን

ቊንጅናዋ ዕጹብ ድንቅ ነው

ሌሊት የለባትም

ብርሃኗ የሱስ ነው

ለዘላለም የሚያበራላት

እጓጓለሁ እጓጓለሁ

በዚያች ከተማ ውስጥ ለመኖር

እጓጓለሁ እጓጓለሁ

ከጌታ የሱሴ ጋር ለመኖር

ከከተማው መሓል

ከበጉ ዙፋን ሥር

የሚወጣ የሕይወት ውሃ አለ

ለሚጠጡት ሁሉ

ብርታትን ይሰጣል

ዳግመኛም መጠማት አይኖርም

እጓጓለሁ፣ እጓጓለሁ...

ከዚህ ዓለም ስለይ

ዘመኔን ጨርሼ

ችግሬና ሥቃዬ ቀርቶ

በዚያች ከተማ ውስጥ

ለሚነግሠው ንጉሥ

ለዘላለም እዘምራለሁ

እጓጓለሁ፣ እጓጓለሁ...

ዘማሪ፦ ወንድም ፀጋዬ ካብቲመር [ወደ ጌታ ሄዷል]

አብሮ ለመዘመር ይጫኑ | መዝሙሩን የጫኑ ሄኖክ፣ ኩኩ፣ ተባረኩ!