ህዝቤ ሆይ ና

ህዝቤ ሆይ ና ይላል እግዚአብሔር
ወደ ቤትህ ግባ ከግርግር
ጥላ ልሁልንህ፣ ከጠራራው ፀሐይ ከጥፋት ውሽንፍር

ልጆችን ወለድሁ፣ አሳደግሁም
እነርሱ ግ ን እኔን አላወቊም
በሬ እንኳ የገዥውን ጋጣ አወቀ
ህዝቤ ግን ከአምላኩ ለምን ራቀ

ህዝቤ ሆይ ና ይላል እግዚአብሔር
ወደ ቤትህ ግባ ከግርግር
ጥላ ልሁልንህ፣ ከጠራራው ፀሐይ ከጥፋት ውሽንፍር

ጒድጓድን በብዛት መቆፈሩ
በውኃ ጥም እጦት መማረሩ
አይበቃችሁም ወይ መባከኑ
የህይወት ምንጭ ነኝ ወደ እኔ ኑ

ህዝቤ ሆይ ና ይላል እግዚአብሔር
ወደ ቤትህ ግባ ከግርግር
ጥላ ልሁልንህ፣ ከጠራራው ፀሐይ ከጥፋት ውሽንፍር

ለሆድህ አትገዛ እንደ ላሞች
በስብሰህ አትቀርም እንደ ዛፎች
እስትንፋስ አለብህ አንት የኔ ነህ
በመጨረሻው ቀን ትነሣለህ

ህዝቤ ሆይ ና ይላል እግዚአብሔር
ወደ ቤትህ ግባ ከግርግር
ጥላ ልሁልንህ፣ ከጠራራው ፀሐይ ከጥፋት ውሽንፍር

በትናንቱ ድምፄ እጣራለሁ
ዛሬም ቸርነቴን አሳያለሁ
የሚፀፀት ካለ እምራለሁ
ህዝቤ ሲጠፋብኝ እቀናለሁ

ህዝቤ ሆይ ና ይላል እግዚአብሔር
ወደ ቤትህ ግባ ከግርግር
ጥላ ልሁልንህ፣ ከጠራራው ፀሐይ ከጥፋት ውሽንፍር

ህዝቤ ሆይ ና ይላል እግዚአብሔር
ወደ ቤትህ ግባ ከግርግር
ጥላ ልሁልንህ፣ ከጠራራው ፀሐይ ከጥፋት ውሽንፍር

~ ተስፋዬ ገቢሶ። አብሮ ለመዘመር ይጫኑ