red rose2

የ ሕ ይ ወ ት  ም ሥ ጢ ር  ቋ ጠ ሮ

አረንጉዋዴ ቸብቸቦ ውስጥ
የጽጌረዳ እምቡጥ
የወዳፍዋን ቋጠሮ
            ሙጥሙጥ
በትንሹ ብቅ አድርጋ
ስታጒዋጒዋ
ስታጒዋጒዋ
ድብቅ ውበት።
እናይ ይሆን ፈንድታ
ስትቀይጥ ተቅላልታ
            ቀለሙን
አረንጉዋዴነቱን።
ፍንዱ ተስጣቶላት
የውስጥ ሀብት
ዑደትዋ፣ ቅላትዋ
ተደራርቦውም እንጂ
የቀያይ ጆሮችዋ።
ማርያም ማርያም የምለው
ለውበት ልደት ነው፦
ለጽጌረዳዎች ውበት፤
ለሰው ልጆች ውበት፤
ለሕይወት ውበት
            ድብቅ፤
የፍልቅቅ ፍልቅቅ
እንደጽጌረዳዋ ፈንድቶት
ተስጣቶት
እንዲያፍካካን
ሕይወታችንን ለውጦት።

~ ሰይፉ መታፈሪያ ፍሬው
“የተስፋ እግር ብረት” ገጽ 10-11
መስከረም 1969 ዓ.ም.፣ ብ/ሰ/ማ/ቤት፣ አ.አ.