ከ  ሁ  ሉ   ስ  ለ  ሚ  በ  ል  ጥ  ብ  ኝ

ሰው ይህንን ዓለም ሁሉ፣ ጠቅልሎ በእጁ ቢያደርግ

በእውቀቱም ቢበረታ፣ በሀብቱም ቢበለፅግ

ከቶ ምን ይጠቅመዋል፣ ፈጽሞ ነፍሱን ቢያጎድል

የሚያቃጥል ዲን ይሆናል፣ የርሱ የፍጻሜው ዕድል

ጌታ ለኔ ከሁሉ ስለሚበልጥብኝ

የነበረኝን ሁሉ ስለ እርሱ ተውኩኝ

የዓለም ክብር ረብ የሚመስለው

ዐይኔ ተከፍቶ ባምላኬ ብርሃን ሳየው

ከበስተኋላው እጅግ የከፋ ጒዳት ነበረው

ግርማውን አይቼዋለሁ፣ ኢየሱስ ተረት አይደለም

ጌታዬ ብዬ ስጠራው፣ ፍጹም አላፍርበትም

ለችግረኛ መጠጊያ፣ መሸሻ አምባ እርሱ ነው

ሁሉ በሁሉ ነው ለኔ፣ የሞትን ኃይል የሰበረው

ጌታ ለኔ ከሁሉ ስለሚበልጥብኝ

የነበረኝን ሁሉ ስለ እርሱ ተውኩኝ

የዓለም ክብር ረብ የሚመስለው

ዐይኔ ተከፍቶ ባምላኬ ብርሃን ሳየው

ከበስተኋላው እጅግ የከፋ ጒዳት ነበረው

እኔ የየሱስን ማህተም፣ በሕይወቴ ተሸክሜአለሁ

በቅዱስም አጠራሩ፣ በፍቅሩ ተስቤአለሁ

ሥጋን ከክፉ መሻቱ፣ ከምኞቱ ጋር ሠቅዬ

ልከተለው ቆርጫለሁ፣ በኢየሱስ ተማምዬ

ጌታ ለኔ ከሁሉ ስለሚበልጥብኝ

የነበረኝን ሁሉ ስለ እርሱ ተውኩኝ

የዓለም ክብር ረብ የሚመስለው

ዐይኔ ተከፍቶ ባምላኬ ብርሃን ሳየው

ከበስተኋላው እጅግ የከፋ ጒዳት ነበረው

~ ተስፋዬ ጋቢሶ | አብሮ ለመዘመር

* የዩቱቡ ቅጂ ግድፈት አለበት