ዋ ና ው  ቊ ም ነ ገ ሩ  የ መ ጨ ረ ሻ ው  ‘ለ ት

ዛሬ ባለሁበት ብዙ እናገራለሁ

መናገር ቀላል ነው ብዙ ቃል ‘ገባለሁ

ጌታዬ ግን ዛሬ ስትመረምር ልቤን

ምን ያህል ቊምነገር ታገኝብኝ ይሆን?

ዋናው ቊምነገሩ የመጨረሻው ‘ለት

ለክፉም ለደጉም ዋጋ ‘ሚሰጥበት

“ታማኝ በጎ” መባል ድልን መቀዳጀት

ያ ነው ቊምነገሩ መጨረሻው ሰዓት

እየተናገርኩት እየመሰከርኩ

ሳልፈራህ በድፍረት እፊትህ እየማልኩ

…  ምን ይመስል ይሆን

ምን ያህል ቊምነገር ይገኝብኝ ይሆን

ዋናው ቊምነገሩ የመጨረሻው ‘ለት

ለክፉም ለደጉም ዋጋ ‘ሚሰጥበት

“ታማኝ በጎ” መባል ድልን መቀዳጀት

ያ ነው ቊምነገሩ መጨረሻው ሰዓት

በመልካም ጊዜማ ማንም ክርስቲያን ነው

መለያ ሲመጣ ወንፊቱ እስኪለየው

አደራ ጌታ ሆይ ስማኝ ልመናዬን

ከቅዱሳንህ ጋር አርግልኝ ዕጣዬን

ዋናው ቊምነገሩ የመጨረሻው ‘ለት

ለክፉም ለደጉም ዋጋ ‘ሚሰጥበት

“ታማኝ በጎ!” መባል ድልን መቀዳጀት

ያ ነው ቊምነገሩ መጨረሻው ሰዓት

“ታማኝ በጎ” መባል ድልን መቀዳጀት

ያ ነው ቊምነገሩ መጨረሻው ሰዓት

~ አስቴር ተፈራ | አብሮ ለመዘመር