creationMezArt

~ ነፍስ መዝራትና መንቃት ገና በትንሽነት

ግ ጥ ሞ ች  ግ ጥ ም ጥ ሞ ች

ሃሳብ ሲበራከት፥ ሲከብድ፥ ለመግለጽ ሲያስቸግር፥

ቋንቋም አልበቃ ሲል፥ በአፍ የሚነገር፥

ቢነገሩም፥ ተነግረው፥ ተነግረው ለማያልቁ ግትልትል ሃሳቦች፥

ጉራማይሌ ስሜቶች፥ “እንግዲህ በቃ!” የሚሉ፥ ስንኞች፥

“በቃ! ይኸው ነው ባጭሩ” የሚሉ፥ አጫጭር ቃሎች፥

የነገር መቋጥሮች፥ መተከዢያ ትዝታዎች፥

የሃሳብ ጭማቂዎች፥ የቅርቡን አጉሊዎች፥

የጥንቱን አስታዋሾች፥ ጊዜን ደምሳሾች፥ ፈጣን ባቡሮች፥

ቅዠትም ቢመስሉ፥ እውነታዎች፥

የሰማዩና የምድሩ ንኪኪዎች፥ ተስፋዎች፥ ልዩ መስተዋቶች፥

የእንባ ማድረቂያዎች፥ የናፍቆት አስታጋሾች፥

የፍቅር መግለጪያዎች፥ ማስተማሪያና ማወደሻ ቅኔዎች፥

መደሰቺያ ዘፈኖችና መዝሙሮች፥

መጸለያ ቅዳሴዎች።  

Copyright 2019 | Mez1