himcrucified

ት ም ክ ሕ ቴ  የ ሱ ስ  ነ ው  አ ል ኩ ኝ

ውበትን ሲረግፍ አያለሁ

ሃብትንም ከንቱ ብያለሁ

ገናናውን ወድቆ እያየሁኝ

ትምክሕቴ የሱስ ነው አልኩኝ፤

ረብ የለው ሥጋን መመካት

ከሰውም አንዳችን መሻት

ትንሽ ሰው ግን ካምላክ ጋራ

ትልቅ ነኝ ስሜ ሲጠራ፤

ለራሴ እኔ እንዳልበጀሁ

እውነት ነው ይህን አውቃለሁ

ድጋፍክን አንድ አግኝቻለሁ

ኢየሱስ ስምህን ይዣለሁ፤

ማን እኔን እንዳንተ ደርሶ

ሊያጽናናኝ እንባዬን አብሶ

ጽኑ ነው ልቤ ባንተ ላይ

ምያለሁ ሌላውን ላላይ፤

ነፍሴ ሆይ ሃሴት ይሙላብሽ

ትካዜሽ ተወገደልሽ

የምድሩ ቀሪ ነውና

ትምክሕትሽ በጌታ ይጽና።

~ ታምራት ወልባ | አብሮ ለመዘመር

ወ/ ታምራት ወልባ፣ በ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. አግኘን።