ፍ ጥ ረ ት ሥ ር አ ት እ ያ ለ ው
ፍጥረት-ሕይወት ሥርአት እያለው
ሲሆን እንደሌለው
የማናስበው ሲበልጥ ከምናስበው
ማሰብ ወይንስ አለማሰብ ነው የሚሻለው?
ላለማሰብም እድል ስንሰጠው
ምን ላይ ነው ሃሳብ የሚንተራሰው?
ሲኖር እንደማይኖር የሚቆጥረው
ከምድራዊው ይልቅ ሰማያዊው የሚታሰበው
ያ ሰው ሁሉንም “እንዳሻው ... እንዳሻው ...
ሁሉም ያው ... ሁሉም ያው” እያለ
ፍስስ ማለትን ነው የሚሻው።
© 2020፣ መዝ. ኃ.