plant

ፍ  ጥ  ረ  ት   ሥ  ር  አ  ት   እ  ያ  ለ  ው

ፍጥረት-ሕይወት ሥርአት እያለው

ሲሆን እንደሌለው

የማናስበው ሲበልጥ ከምናስበው

ማሰብ ወይንስ አለማሰብ ነው የሚሻለው?

ላለማሰብም እድል ስንሰጠው

ምን ላይ ነው ሃሳብ የሚንተራሰው?

ሲኖር እንደማይኖር የሚቆጥረው

ከምድራዊው ይልቅ ሰማያዊው የሚታሰበው

ያ ሰው ሁሉንም “እንዳሻው ... እንዳሻው ...

ሁሉም ያው ... ሁሉም ያው” እያለ

ፍስስ ማለትን ነው የሚሻው።

© 2020፣ መዝ. ኃ.