የ የ ሱ ስ  ፍ ቅ ር  ግ ድ  ይ ለ ና ል

የጌታችንን ቃል፣ መልእክቱንም ይዘን
ለሕዝብ ለማስታወቅ፣ በምድር እንዞራለን
ሞት ብንቀምስ በሥጋ፣ በነፍስ ሕይወት አለን
እኛስ ከትግላችን፣ መች እንላላለን

በተራራ ላይ ያለችን ከተማ
መሸሸግ እንደማይቻል
ሕይወታችንን ሁሉ ለመመሥከር
የየሱስ (የጌታ) (የመስቀል) ፍቅር ግድ ይለናል

የሠራዊት ኮቴ መች ያስፈራራናል
የእምነት ባለቤቶች ኢየሱስ አርጎናል
በደም ተገዝተናል፣ ለርሱም ታትመናል
የየሱስ ሠራዊት በምርጫ ሆነናል

ሌሎች በሠልፋቸው፣ እኛም ባምላካችን
በኃይል ሁሉ ጌታ፣ ነው ትምክሕታችን
ኮሳሶች ብንመስል፣ ፅኑ አዝማች ስላለን
ጒዞአችንን በድል እንደመድማለን

~ ዘማሪ አዲሱ ወርቊ | የመዝሙሩና የዜማው ደራሲ፦ ለገሰ ወትሮ | አብሮ ለመዘመር

Credit: Mulu Wongel Network