ራ እ ይ

ትንሽ ሕልም ልም የሆነች ጠብታ፣
ልቤ ላይ ተሰንቅራ፣ ቦታ አግኝታ፤
እንደ ዘበት እንደ ዋዛ፣
አእምሮዬን አስጨንቃ ሰቅዛ፤
ወደ ጐን ሰፋች፣ ተስፋፋች፣
እየተንገዋለለች፣ ስታሸኝ ሰነበተች፤
ውላ አድራም እየተለወጠች ተቀጣጥላ፣
በቅጥልጥላቱ ተመንድጋ በስላ፤
አለሁ ልትል ተከሽና፣
አረፈችው የሚዳበስ አካል ሆነችና፤
ብቅ ብላ ታደባባይ፣
ተሠርታ ስታልቅ እንድትታይ።

© በቀለ ብርሃኑ፣ 2009 ዓ.ም (2017)
የነፍሴ ዜማ፣ መንፈሳዊ የግጥም መድብል

bekele birhanu poems