ሌ ላ  ፈ ተ ና  ወ ይ ስ  ጥ ሩ  አ ጋ ጣ ሚ

ብፁዕ አቡነ መርቆርዮስ የካቲት 25/2014 ዓ.ም. ማረፋቸውን ዋልታ ዘግቧል። ከሁለት ዓመት ተኲል በፊት "ቤተ ክህነት እና የዐቢይ ዕጣ" በሚል ርእስ በለጠፍነው ላይ እንዲህ ብለን ነበር፦ "አፄ ኃይለሥላሴ፣ ወታደራዊ ደርግ፣ እና ህወሓት/ኢሕአዴግ ሁለት ሁለት ፓትርያርክ ሾሙ። በዐቢይ ዘመን የሁለት ፓትርያርኮች ጥምረት ተጀመረ፤ ሁለት እራስ!! ሁለት እረኛ አንድ መንጋ ፍቺው ምን ይሆን? መጽሐፍ ግን “አንድ መንጋ ይሆናሉ፣ እረኛውም አንድ” ብሏል (የዮሐንስ ወንጌል 10፡16)። ሞት ለማንም አይቀርምና ከሁለቱ አባቶች አንደኛቸው ወይም ሁለቱ ተከታትለው ቢሞቱስ? የዐቢይ ዕጣ ምን ይሆን?"

ወቅቱ ብዙ ጸሎት እና ጥንቃቄ የሚጠይቅ ወቅት ነው። ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ከውስጥም ከውጭም ከክርስቶስ ዓላማና ሥራ ይልቅ በጊዜው ፖለቲካ ውስጥ ተዘፍቃለች። የእምነታቸውን ምንነት ለይተው የማያውቊ የግል አጀንዳቸውን ለማራመድ የሚጠቅማቸውን እያደረጉ፣ ሕዝቡን እያንገላቱ፣ ወደ ፍቅር ሳይሆን ወደ ጥላቻ እየነዱ ነው።

የዶ/ር ዐቢይ አሕመድ አመራር የሚፈተንበት ሰዓት ነው፤ አገርና የሕዝብ ዓይነት የገባበት ማጥ ሳያንስ ሌላ ከፊትለፊቱ ተደቅኖ ይጠብቀዋል። እንዴት ይሻገር ይሆን? 

merkorios